የኦዲፒን የምስረታ በዓል ስናከብር ለአዳዲስ ድል እየተዘጋጀን መሆን አለበት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ

ፊንፊኔ መጋቢት 17/2011(ቶለዋቅ ዋሪ) የኦዲፒን 29ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ስናከብር ለአዳዲስ ድል እየተዘጋጀን መሆን አለበት አሉ የኦዲፒ ሊቀ መንበር እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ።
የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) 29ኛ የምስረታ በዓል እና የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በመድረኩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የኦዲፒ ሊቀ መንበርና የኤፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፥ የኦዲፒን የምስረታ በዓል ስናከብር ለአዳዲስ ድል እና ገድል እየተዘጋጀን መሆን አለበት ብለዋል።
ኦዲፒ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የሚኮሩባት፣ የሚሰራበት እና የማይሸማቀቁበት ኢትዮጵያን ለመፍጠር በቁርጠኝነት ይሰራልም ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አክለውም፥ ከአዲስ አበባ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ሀሳቦች አዲስ አበባ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ባህር ዳር፣ መቐለ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ ነቀምት ሂዶ እንደሚሰራውና የኔ ናቸው እንደሚለው ሁሉ አዲስ አበባም ተመሳሳይ ነች፤ የሁሉም ኢትዮጵያውያን መኖሪያ ነች ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከራሷ ዜጎች በዘለለ ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የምትበቃ በመሆኗ ይህንን ከግምት ማስገባት መልካም ነው ሲሉም ገልፀዋል።
የኦዲፒ አላማ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በእኩል ድምጽ በነጻነት የሚኖሩባትን ሀገር መፍጠር ነው፤ በዚህ ረገድም ከሁሉም ጋር ለመስራት ቁርጠኛ ነው ብለዋል።
ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፉት መልእክትም መለያየትን የሚሰብኩ አስተያየቶችን ወደ ጎን በመተው በጋራ መቆም አለብን ሲሉም ተናግረዋል።

ለኦዲፒ አባላት ባስተላለፉት መልክት ደግሞ፥ ኦዲፒ በማንኛውም ሁኔታ ድምፆች መታፈን የለባቸውም የሚለውን አላማ ይዞ መነሳቱ መዘንጋት እንደሌለባቸው አስገንዝበዋል።
ማንኛውም ሀሳብ የሚንሸራሸርበት ኢትዮጵያን መፍጠር የትግላችን ውጤት መሆኑንም መገንዘብ አለብን ሲሉም ተናግረዋል።
አሁን ካለንበት የለውጥ ሂደት ጋር በተያያዘ የተለያዩ አስደንጋጭ ሀሳቦችን ልትሰሙ ትችላላችሁ፤ እነዚህን ከመደናገጥ ይልቅ የተሻለውን ሀሳብ በመውሰድ ሌላውን ወደጎን መጣል አለበን ብለዋል።
አሁን የጀመርነውን ድል ማንም ወደ ኋላ አይመልሰውም ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ለእህት ድርጅቶች ባስተላለፉት መልክትም በተጠናከረ እና በወንድማመችነት መንፈስ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ እናሸጋግር ብለዋል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman