የአገራችን ሚዲያዎች ጉዳይ


የወያኔ ሽማግሌ አመራሮች የሰሩትን ሰርተው ወደ መቀሌ ገብተው ከተሸሸጉ ወዲህ  20 ያህል አዲስ የህትመት እና የብሮድካስት ሚዲያዎችፈጥረው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ይነገራል።ከሃገር ውጪ የነበሩ መገናኛ  ብዙሃን ጭምር ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ ሆኗል፤ይህም የሚዲያው ምህዳር እየሰፋ ስለመሆኑ ማሳያ ነው።
የህትመትም ሆኑ የብሮድካስት ሚዲያዎች በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው በነፃነት መስራት መቻላቸው ለህዝቡና ለአገሪቱ መልካም ቢሆንም አንዳንድ የህትመትም ሆኑ የብሮድካስት ሚዲያዎች የሚሰሩበት ሁኔታ የተገኘውን ነፃነት ወደኋላ የሚመልስ እንደሆነ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል
በአሁኑ ወቅት ለከት አጥተው እንደፈለጉ በመሆን ላይ የሚገኙ ሚዲያዎችን ስመለከት በ1985 ዓ.ም የነበረው የሚዲያ ሁኔታና በቅርቡ ኢ ኤንኤን(ENN) በተባለው ሚዲያ ላይ የተወሰደው እርምጃ ትዝ ይለኛል
ኢህአዴግ በ1983 ዓ.ም አገሪቱን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ የሰላምና መረጋጋት ኮሚቴም የስራ ድርሻውን ከተወጣ በኋላ በተለይም የህትመት ሚዲያዎች እንደ አሸን ፈልተው አይተናል፤በወቅቱ ከሴቶች መብት ጋር የሚጋጩ ዘገባዎች በመሰራጨታቸው ምክንያት ሴቶች እህቶቻችን ለተቃውሞ አደባባይ መውጣታቸውንም አስታውሳለሁ
በዚያን ወቅት እጅግ ተበራክተው የአንባቢያንን ቀልብ የሳቡ ሚዲያዎች በነበረባቸው ችግር ምክንያት ገበያውን መቋቋም ባለመቻልና በሌሎችም ምክንያቶች ለመጥፋት ተገድደዋል።
አሁን ያለውን የአገራችን ሚዲያዎች ዘገባ ስመለከት ሳነብና ሳዳምጥ  በፊት የነበረው ሁኔታ ተመልሶ ይመጣ ይሆን የሚል ስጋት አለኝ።እኔ እንደ አንድ ግለሰብ ይህ ስጋት ቢሰማኝም አንዳንድ ብሮድካስተሮችና የሚዲያ ባለቤቶች ግን የእኔን ያህል ስጋት እንደሌላቸው በመሰራጨት ላይ ከሚገኙ ኃላፊነት የጎደላቸው ዘገባዎች መገንዘብ ይቻላል
ኢ ኤንኤን(ENN) በተባለው ሚዲያ በተወሰደበት እርምጃ የተዘጋው ከተለያዩ ተቋማት በሚደረግለት የህዝብ ገንዘብ አፍራሽ ስራዎች ላይ በመሰማራቱና ድጋፍ የሚያደርጉለት ተቋማት እረፉ በመባላቸው ይመሰለኛል።አሁን በመንግስትና በግል ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ እየሰሩ የሚገኙ ሚዲያዎችም ቀይ መስመር ጥሰው ከሄዱ የENN እጣ ፈንታ የሚደርሳቸው ይመስለኛል።መንግስት  ለሚዲያ ነፃነት መከበር የገባውን ቃል ለማክበር ሲል ብቻ ትዕግስቱን ቢያሰፋም እንኳ አድማጭ ተመልካቹና አንባቢው አንቅሮ ይተፋቸዋል አይናችሁ ለአፈር ብሎ ዶጋመድ እንዲሆኑ ሊያደርግ ይችላል
ይህ ሁኔታ ከመከሰቱ በፊት ብርቱ ጥንቃቄ በማድረግ መስራት ህዝብና አገርን ማገልገል የሁሉም ሚዲያዎች ኃላፊነትና ግዴታ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman