ከዳያስፖራችን የምንሻው
የኦሮሚያ
ተወላጅ ዳያሰፖራዎችን ጨምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ በውጭ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያውያን በጣት በሚቆጠሩ ጥቂት ቀናት
ውስጥ የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታዎች እንዲረዱ ጥረት ተደርጓል።
በየደረጃው
የሚገኙ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላትም አገር የሰጠቻቸውን ተልዕኮ በብቃት ተወጥተዋል ማለት ይቻላል።
ሆኖም
በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ወደ አገር የመጡ ዳያስፖራዎቻችን ሁሉንም የኢትዮጵያ ለውጦች ተመልክተው ተገንዝበዋል ማለት አይቻልም፤ምክንያቱም
ሁሉም ነገር በፍጥነትና ከጊዜ ጋር በመሽቀዳደም የተከናወነ መሆኑ ይታወቃልና።
“ከቀዳዳ
ይሻላል ጨምዳዳ እንዲሉ”ዳያስፖራው በአገሩ ጉዳዮች ላይ የተሟላ ግንዛቤ እንዲኖረው የተደረገው ብርቱ ጥረት የሚናቅ አይደለም።በነገራችን
ላይ ይህን አኩሪ ጥረት የሚያጣጥሉና ውሃ ሲቸልሱ የሚውሉ ወገኖች በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ እንዳሉ ሊታወቅ ይገባል።
እዚህ
አፍራሽ ኃይሎች ተልዕኮአቸውን እየተወጡ ነውና የሚያመጡት ምንም ነገር ስለሌለ እነርሱን ተዋቸው፤የበሬ ወለደ ወሬአቸውን ከመንዛት
መቼም ቢሆን አይቆጠቡምና።
አሁን
ዳያስፖራው ይነስም ይብዛ ስለ አገሩ ተጨባጩን ነገር አይቶ ተረድቷል ማለት ይቻላል።ከአሁን በኃላ ከዳያስፖራው የምንሻው:-
1.ለማንም ኪራይ ሰብሳቢ ሳይንበረከክ በአገሩ
ላይ ሰርቶ ራሱን በመጥቀም አገሩን መጥቀም
2.በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለሚገኙ የአፍራሽ
ኃይሎች ወሬና አሉባልታ አለመንበርከክ
3.በውጭ ለሚገኙ ፅንፈኛ ዳያስፖራዎች ተጨባጩን
የኢትዮጵያ ሁኔታ በማስረዳት አደብ እንዲገዙ ማድረግ።
5. ከመልካም
አስተዳደርና ሙስና ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በውቅቱ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ማሳወቅና ለሚዲያዎች ማጋለጥ ይጠበቅበታል።
ዳያስፖራችን
በመጪው ጊዜ ይህን በቁርጠኝነት ከፈፀመ የኢትዮጵችን ዕድገት ቀጥሎ ከአሳፋሪ ድህነታችን ተመንጥቀን የምንወጣበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ