አስደማሚና ገራሚ ሙዚቃዊ ድራማ



ነገሩ የሆነው ትናንት የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(ኦህዴድ) 8ኛ መደበኛ ጉባኤውን ደማቅ በሆነ ስነ ስርዓት አዳማ በሚገኛው አባ ገዳ አዳራሽ ሲጀመር ነው።ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ የጉባኤው ተሳታፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች በአዳራሹ ተሰባስበው በምቹው መቀመጫ ላይ ተቀምጠዋል።


የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ በከር ሻሌ የጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ ኃላፊነቱን ሰጥቷቸው ነው መሰል የጉባኤውን ፕሮግራሞች ያስተዋውቃሉ።በአስተዋዋቂው ትዕዛዝ መሰረት ጉዳዩ የሚመለከታቸው የድርጅቱ ባለስልጣናት በተለይም የኦህዴድ ሊቀመንበር አቶ ሙክታር ከድርና የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ ተራ በተራ በጉባኤው ሂደትና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ንግግር አሰሙ።

ቀጠሉ የመድረክ አስተዋዋቂው አቶ በከር ሻሌ፤”ቀጥሎ የቢፍቱ ኦሮሚያ ኪነት ቡድን ያዘጋጀውን ሙዚቃዊ ድራማ ያቀርብልናል”አሉ።በተቀመጠው የፕሮግራም ቅደም ተከተል መሰረት የቢፍቱ ኦሮሚያ ኪነት ቡድን የተዘጋጀበትን ሙዚቃዊ ድራማ ማቅረብ ጀመረ።

የሙዚቃዊ ድራማው አጠቃላይ መልዕክት በገዳ ስርዓት ወቅት የኦሮሞ ብሄር እንዴት ሲተዳደር እንደነበር ሂደቱን በማሳየት፤ከዚያም ከአፄ ሚኒሊክ ጀምሮ እስከ አፄ ኃይለስላሴ ቀጥሎም እስከ ደርግ ስርዓት ድረስ የኦሮሞ ብሄር የደረሰበት አስከፊ ጭቆና ምን እንደሚመስል በዝርዝር ያሳያል።

ከአምባገነኑ የደርግ ስርዓት መወገድ በኃላ ደግሞ የኦሮሞ ብሄር ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ጋር በመተባበር ለክልሉና  ለኢትዮጵያ ዕድገት ቀጣይነት እያደረገ ስላለው ጥረትና በመመዝገብ ላይ የሚገኙ ተጨባጭ ውጤቶችም በሙዚቃዊ ድራማው ትኩረት ተሰጥቷቸዋል።

በአስደማሚው ሙዚቃዊ ድራማ ምክንያት በአዳራሹ ውስጥ ከነበሩ ሰዎች ስሜቱ ያልተነካ አለ ማለት አይቻልም።አንዳንዶቹ እንባቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው ሲያለቅሱና እንባቸው እንደ ውሃ ፊታቸው ላይ ሲፈስ ታይተዋል። የኦህዴድ ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙክታር ከድር፤የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሯ ወይዘሮ ደሚቱ ሃንቢሳ እና ሌሎች የጉባኤው ተሳታፊዎች በግላጭ እንባቸው ኮለል ብሎ ከፊታቸው ሲወርድ በኦሮሚያ ቴሊቪዥን ታይተዋል።

እንግዲህ ይህ ሊሆን የቻለው በቢፍቱ ኦሮሚያ ኪነት ቡድን ሙዚቃዊ ድራማ ነው።የዚህ ፅሁፍ አቅራቢም በሙዚቃዊ ድራማው ይዘቶችና መልዕክቶች ልቡ ተነክቶ አንብቷል።የሙዚቀዊ ድራማው ዋና ዋና መልዕክቶች

  • የገዳ ስረዓት አስተዳደርና ዴሞክራሲያዊነቱ
  •  ሚኒሊክ የገዳ ስርዓት እንዲጠፋ ያደረሰው በደልና የተጠቀመባቸው ስልቶች
  • የአኖሌና ጨለንቆ አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች
  • የወንዶች ብልትና የሴቶች ጡት በአሰቃቂ ሁኔታ ስለመቆረጡ
  • የአፄዎቹ ስርዓት ኦሮሞ በኢኮኖሚው ተጠቃሚ እንዳይሆን ያደረሰው በደል
  • የ1960ዎቹ ፀረ አምባገነን ገዥዎች ሕዝባዊ ትግልና የመሬት ላራሹ ሕዝባዊ ንቅናቄ
  • የደርግ ብሄራዊ ውትድርና አገልግሎትና ውጥንቅጡ
  • የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም የመጨረሻ ጊዜ መፈራገጥና አገር ጥሎ መጥፋት
  • ኢህአዴግ አገሪቱን መቆጣጠሩና ከዚያን ጊዜ ወዲህ እስከ አሁን ያለው ሂደት አንድም ነገር ሳይዛነፍ ቀርቦበታል።
በሙዚቃዊ ድራማው ላይ ወደ ዘጠና ሰው ያህል ተሳትፏል።ወደፊትም የኦሮሞን ታሪክ ባህልና ቀንቋ ለማሳደግ እንዲህ አይነት ስራዎች እጅግ በጣም በጣም ያስፈልጋሉና ጉዳዩ ሚመለከተው አካል ቸል ሊለው አይገባም።ብራቮ ቢፍቱ ኦሮሚያዎች እደጉ ተመንደጉ የጎልማሳ ምርቃቴ ነው፤በቸር እንሰንብት።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman