“ጅብ በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል”
አይ ጁኔዲ ሳዶ? “ጅብ በማይታወቅበት
አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል”
አቶ ጁኔዲ ሳዶ ከየት ብቅ አለ?
በአንድ ወቅት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር በመሆን የኦሮሚያን ሕዝብ አገልግሏል፤በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት
መዋቅር ውስጥም የሳይንስና ቴክኖሎጂ፤የሲቪል ሰርቪስ እንዲሁም የመገናኛና ትራንስፖርት ሚኒስትር ሆኖ ሰርቷል በኦሮሚያ ክልል በቢሮ
ደረጃ የኦሮሚያ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ሆኖም አገልግሏል በወቅቱ በቅንነት ለሰጠው አገልግሎት ክብር ይገባዋል አክባሪው
ነኝ
ከአራት አመታት በፊት ስልጣኑን
ተጠቅሞ በኢትዮጵያ የእስልምና አክራሪነት እንዲስፋፋ በሕቡዕ ባደረገው እንቅስቃሴ(ባለቤቱ ሃቢባ ከሰኡዲ አረቢያ ኤምባሲ በሺህ የሚቆጠር
ቁርአን መፅሃፍ ስታወጣ ተይዛ መታሰሯ ትዝ ይሏል) ምክንያት ተጋልጦና ተገምግሞ ከስልጣን ከተባረረ በኋላ ደግሞ እምጥ ይግባ ስምጥ
ሳይታወቅ ቆይቶ የሰኡዲ አረቢያ ወይም የአሜሪካ መንግስት ጥገኝት እንዳገኘ በወቅቱ ከመገናኛ ብዙሃን ተነግሯል።ጥያቄው ጁኔዲ ሳዶ አሁን ከየት ብቅ አለ?
አቶ ጁኔዲ ፈረንጆች እንዲረዱት
ይመስላል በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ አትኩሮ የኋላ ሁኔታዎችን በማስታወስ በኢንግሊዝኛ ቋንቋ እይታውን ይፋ አድርጓል “The
current turmoil has come as no surprise”ይለናል አቶ ጁንዲ ሳዶ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሚታየው ግጭት
ብርቅ አይደለም አያስደንቀውም እንደ አዲስም አይመለከተውም።
ይሁንና አሁን አንዳንድ ችግሮች
የተከሰቱት በተለይም በኦሮሚያ የታዩት ችግሮች ምንጭ አቶ ጁንዲ ኦሮሚያን ሲያስተዳድር በነበረበት ወቅት መሰረት ይዘው የቆዩ መሆናቸው
ሊታወቅ ይገባል ኪራይ ሰብሳቢነት፤የሃይማኖት አክራሪነት፤አስመሳይነት፤ከባቢያዊነት የወንዜ ልጅ ችግሮች መሰረት ተጥሎላቸው መፋፋት
የቻሉት በአቶ ጁንዲ ዘመነ ስልጣን እንደሆነ ግልፅ ነው የኦሮሚያ ዋና ከተማ ከፊንፊኔ ወደ አዳማ እንዲሆን በማድረግ ውጥንቀጡ የወጣ
አካሄድ እንዲከሰት ያደረገውም የአቶ ጁኔዲ ውሳኔ እንደሆነ ሊታወስ ይገባል
ታዲያ አቶ ጁኔዲ ካለበት ተነስቶ
የተለመደውን የትግሬ የበላይነት አለ አሁንም ያው ነው የሚለውን ዘፈን ለመዝፈን ለምን አማረው?ጁኔዲ የቀለም አብዮቱ የኋላ አጋዥ
ከሆነም ግልፅ ማድረግ አለበት
የኢትዮጵያ የህዳሴ ጉዞ ወደ
ኋላ የማይመለስ መሆኑ በዳግም ጥልቅ ተሃድሶ ይረጋገጣል፤አቶ ጁኔዲ ወደ ኪራይ ሰብሳቢነቱ መመለስ የምትችልበት በር ተከርችሟል መቼም
ሊከፈት አይችልም በኦነግ ርዝራዦች መፍጨርጨርም ኦሮሚያ በጠባቡ ኃይል ስር የምትተዳደርበት ሁኔታ በፍፁም የለም
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ