የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(ኦህዴድ) የዳግም ጥልቅ ተሃድሶ

 የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(ኦህዴድ) የዳግም ጥልቅ ተሃድሶውን የሊቀመናብርት ለውጥ በማድረግ ጀመረ


በዚሁ መሰረት የድርጅቱ ሊቀመንብር አቶ ሙክታር ከድርና ምክትል ሊቀመንበሯ ወይዘሮ አስቴር ማሞ ለዳግም ተሃድሶ ስኬት በፈቃዳቸው እንደለቀቁ የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በከር ሻሌ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል

ሰሞኑን የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(ኦህዴድ) ማዕከላዊ ኮሚቴ የ15 ዓመታትን የተሃድሶ እንቅስቃሴ ሲገመግም የቆየ ሲሆን በተነሱት ሊቀመናብርት ምትክ አቶ ለማ መገርሳ የኦህዴድ ሊቀመንበር፤ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ እንደተመረጡ አቶ በከር ሻሌ ማምሻውን ለኦሮሚያ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል



በከፍተኛ አመራር ደረጃ የተጀመረው ጥልቅ ተሃድሶ ተቀጣጥሎ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በመጠናከር የሚቀጥል በመሆኑ የኦሮሞ ሕዝብ እንደከዚህ በፊቱ ከኦህዴድ ጎን በመሰለፍ ትግሉን እንዲያጠናክር የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጥሪውን አቅርቧል

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa