ከኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የኦህዴድ መኃከላዊ ኮሚቴ በካሄደው ጥልቅ ግምገማ የድርጅቱ ታህድሶ በፅኑ መሠረት ላይ ማኖር እና ድርጅቱን በጥልቅ በማደስ ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገር ውቅታዊ ጉዳይ በመሆኑ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ከምንጊዜም በበለጠ አካሄድ አዲስ ድል ለማስመዝገብ ቁርጠኛና ዝግጁ መሆኑን በመገለፅ በተለየ መንፈስ ውይይት በማድረጉ የግምገማ መድረኩን ወቅታዊ ወሳኝ የትል መድረክ ብሎ በመሰየም በካሄድወ ውይይት ታሪካዊ ስምምነት ላይ መድረሱን ይፋ አድርጓል፡፡

...
በዚሁ መሠርት የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከመስከረም 4-10/2009 ዓ.ም በአዳማ ባካሄድው ጥልቅ የታሃድሶ ግምገማ የድርጅቱን የ15 ዓመታት የስኬት ጉዞ እና ያጋጠሙ ተግዳሮት አብይ ምክንያቶችበመገመገም የወደፊት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡
...
ባለፉት 15 ዓመታት ከሁሉም በላይ ከድርጅቱ ስኬቶች መካከል በኋላ ቀረነት እና በድህነት ላይ በተካሄደው ዘመቻ የኦሮሚያ ክልል የገጠሩና የከተማ አከባቢ ብሩህ ተስፋ እንዲለመልም ማድረግ ተችሏል፡፡
በግብርናና በገጠር ልማት እስትራቴጂ ምርት ምርታማነትን በማሳደግ፣ የግብርና ኤክስቴንሽን በማስፋፋት፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም በማሻሻል፣ የሀገሪቱ እና የህዝቡ ጠላት የሆነ ድህነትን በመቀነስ አርሶአደሩ ኑሮውን እንዲያሻሽል የተኬደው ርቀትም አብይ ማሳያ ነው፡፡ ለዚህ ደሞ ዋና ምስክር ተጠቃሚ መሆን የቻለው የኦሮሞ ህዝብ ነው፡፡
...
በዚህ አጋጣሚ ድርጅቱ ለተገኘው ስኬት ለአርሶ እና አርብቶ አደሩ እንዲሁም ለግብርና ባለሙያዎች ትልቅ አድናቆት እና ምስጋና እንዳለው ያረጋግጣል፡፡
የአርብቶ አደሩን አካባቢ ልማት በተመለከተ የአርብቶ አደሩን ሕይዎት ለማሻሻል ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት አርብቶ አደሩ የመሠረት ልማት አውታሮች፣ የትምህርት፣ የጤና፣ የመጠጥ ውኃ፣ የእንስሳት የገበያ ትስስር፣ የእንስሳቶች የጤናና የኤክስቴንሸን አገልግሎት እንዲያገኝ በተደረገው ጥረትም ተስፋ ሰጪና አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል፡፡
...
ገጠሩን የኦሮሚያ ክልል ከኋላ ቀርነት ለማለቀቅ በሰው ሀብት ልማት ላይ በተሰራው ስራ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከቀያቸው ሳይርቁ የትህምርት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በተሰጠ ትኩረትም የተገኘው ውጤት አኩሪ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ህዝብ ጠላት የነበረው ኋላ ቀረነት እጁን እንዲሰጥና ሁሉም የኦሮሞ ህዝብ ተምሮና ሰልጥኖ በየቤቱ ማየት ተችሏል፡፡
...
ኦህዴድም ይህንን ድል ለማስመዘገብ ከባለድርሻ አካላት ከባለሙያዎች እና ከመምህራን ጋር በቅንጅት መስራት በመቻሉ ስለሆነ ለተገኘው ውጤት ላቅ ያለ ምስጋና አለው፡፡
ገጠሩ የኦሮሚያ አካባቢ ከተለያዩ በሽታዎች እና ብክለት ለማፅዳት በሽታን አስቀድሞ በመከላከል የጤና ፖሊሲ ጤናማ ህብረተሰብ ለማፍራት በተደረገው ጥረት ትልቅ ለውጥ ከማምጣት ባሻገር የምዕተ አመቱን የልማት ግቦች እንዲሳኩ አስተዋጾም አበርክቷል፡፡ በተለይ ለእናቶች ህጻናት ጤና አጠባበቅ፣ ተላላፊ በሽታዎችን ለመቆጣጠር በተዘረጋው አሰራር የተሻለ ውጤት ማምጣት ተችሏል፡፡
በዚህም የድርጅቱ የአመራርነት ሚና እንደተጠበቀ ሆኖ የሰፊው ህብረተሰብ፣ የጤና ባለሙያዎች እና የባለድርሻ አካላት ተስትፎ ከፍተኛ የነበረ በመሆኑ የሚያስመሰግን ተግባር ነው፡፡
...
በሁሉም ረገድ የሚከናወኑ የልማት እንቅስቃሴዎች መሠረት እንዲኖራቸውና በመሠረተ ልማት ዝርጋታ የመንገድ፣ የመጠጥ ውኃ፣ የኤሌክትሪካል ኃይል አቅርቦት የቴሌኮም ማስፋፋት በአንድ ክፍለ ዘመን ተሰርቶ በማይታወቅ መልኩ እንዲስፋፋ የተደረገ ሲሆን የህብረተሰቡ የእድገት ማነቆዎች እንዲቀረፉና አሁንም የህዝቡ የልማት ፍላጎት በየጊዜው እያደገ የመጣ መሆኑን ድርጅቱ በሚገባ ይረዳል በዚህ ረገድ የፕሮጀክቶች መጓተት በተደራሽነት እና ጥራት በኩል ውስንነቶች ያሉ ቢሆንም የተከናወነው ተግባር በየትኛውም መስፈርት የሀገርቱን የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ታሪክ የቀየረ መሆኑን አይደለም የሀገሪቱ ህዝብ አለም ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡
ድርጅቱ በዚህ ረገድ በተመዘገበው ትልቅ ድል ኩራት ይሰማዋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለዘርፉ ባለድርሻዎች እና ባለሙያዎች አድናቆቱን ይገልፃል፡፡
...
በከተማ ልማት እና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ድርጅቱ ያከናወናቸው ስራዎች ከግብርና ገጠር ልማት አንጻር ዘግየት ብለው የተጀመሩና 1997 ዓ.ም ወዲህ ተጠናክሮ የቀጠሉ ሲሆን በዘርፉ በተሰሩ ስራዎችም የከተማና የገጠሩ ነዋሪዎችን በማስተሳሰር፣ ዘላቂ ልማት እንዲኖር፣ ከተማን ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እና የኢንዱስትሪ ማዕከል እንዲሆን ውጤታማ የሆኑ ትላልቅ ስራ ተሰርቷል፡፡ በተለይ በከተማው በስፋት የሚስተዋለውን ስራ አጥነትና ድህነትን በመናድ የስራ ባህል እንዲጎለብት ስራ የማይነቅ ዜጋ ለማፍራት የቁጠባ ባህል ለማዳበር የጥቃቅን አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት የተመዘገበ ነው፡፡
...
በዚህም በራሱ የሚተማመን ሰርቶ በድካሙ ሀብት የሚያፈራና ለልማታዊ ባለሀብትነት መሠረት የሚሆኑ ዜጎችን ለማፈራት በተከናወነው ተግባር ተስፋ ሰጪ ውጤት የተመዘገበ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች እና ወጣቶችም የዚህ እድል ተጠቃሚ መሆናቸው የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት እድገትና ፍትሃዊነት በትክክለኛ ተሰፋ ሰጪ አቅጣጫ ላይ መሆኑ ተርጋግጧል ፡፡ ለዚህ ስኬትም ድርጅቱ ለባለድርሻ አካላት በሙሉ ትልቅ አድናቆት አንዳለው ይገልፃል ፡፡
...
በገዢ መደቦች ተገፍቶና ተቀብሮ የነበረው የኦሮሞ ህዝብ ታሪክና ባህል ኦህዴድ በከፈለው አኩሪ መስዋዕት ባለፉት 25 ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ አንገት ቀና ያስባለ ድል ማጎናጸፍ መቻሉን ሲገልፅ ለዘላለም በኩራት የሚኖርበት ታሪክ በድርጅቱ የተገኘ ድል መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡
...
በዚህም አፋን ኦሮሞ የመንግስት የሥራ ቋንቋ የጥናትና ምርምር፣ የሣይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የሚዲያ ቋንቋ ማድረግ መቻል ትልቁ ማሳያ ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ ተደብቆ ከነበረበት ይፋ እንዲወጣ በአፈ ታሪክ ሳይሆን በፅሁፍ ለትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ ተችሏል፡፡ምቹ መደላደልም ተፈጥሯል፡፡
...
ከዚህ ባሻገር ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ቁርኝት ያላቸውና ልዩ ትርጉም ያላቸውን ታሪካዊ ስፍራዎችን ልዩ ትኩረት በመስጠትና በማልማት ድርጅቱ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ታሪካዊ ሃውልት ማቆም ችሏል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ለታሪኩ ቀጣይነት የኦሮሞ አገር ሽማግሌዎች ምሁራንና የድሉ ባለቤት የሆነው አዲሱ ትውልድ ትልቅ ደስታና ስኬት ነው ብሎ ያማናል፡፡
...
ኦህዴድ ለሌሎችም ምሳሌ የሚሆንና አዲስ ካስመዘገባቸው ታሪኮች ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የክልሉ ሚዲያ በማቋቋም የኦሮሞን አንድነት የኦሮሞን ታሪክና ቋንቋን በማሳደግ ህዝቡ ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኝ ከመላው ሀገሪቱ ጋር እንዲገናኝና ከአለም ጋር እንዲተሳሰር ህዝቡን ለማህበራዊና ልማት ስራዎች ተነሳሽነት እንዲኖረው የልምድ ልውውጥ እንዲያደርግ ልማታዊ ተልዕኮ ያለውን ሚዲያ መስርቶ መስራት መቻል ትልቅ ስኬት መሆኑም ሊታወቅ ይገባል፡፡ለዚህ ትልቅ ድል አስታዋዕፆ ላበረከቱ የሚዲያና ኮሙኒኬሸን ባለሙያዎች ኦህዴድ ትልቅ ክብር እንዳለው ይገልፃል፡፡
...
አህዴድ የስራውን ስኬት ሁሌም ሲገመግም ያለፈውን የስራ መነሻና ባስመዘገበው ውጤት ተኩራርቶ እራሱን ለማመፃደቅ ሳይሆን ውጤቶቹ ያላቸው ትርጉም እና ሚስጥር ለወደፊት ትግሉ ያላቸውን አስታዋዕፆ ከግምት ለማስገባት ከገጠሙ ውስንነቶችን ትምህር በመውሰድ ለቀጣይ ምዕራፍ ራሱን ለማዘጋጅት ባህሉ መሆኑንም ያስገነዝባል፡፡ መቼም ቢሆን የድሎቻችንን መነሻ ስንገመግም ትክክለኛ አቅጣጫ እና ግልፅ በመሆን መጀመሪያውና መጨረሻው የህዝቡን ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይዘን ቁርጠኛ እና በባለቤትናት በመታገል መስዋዕት መሆን የሚችል አባል አፍርተንና በዲሞክራሲያዊ መርህና ባህል በየጊዜው ችግሮችን ለይቶ ለማስተካከል ዝግጁ በመሆን ጭምር የሚያጋጥመንን እንቅፋት በሙሉ በጊዜ ማስተካከል መሆኑን ተርድተናል፡፡
...
ከሁሉም በላይ ደግሞ የልማትና የዲሞክራሲ አቅጣጫውን የራሱ አድርጎ የድርጅቱን ባህሪ በመረዳት በጥንካሬም ሆን በድክመታችን ጊዜ እንደ ልጆቹ በመገሰፅና በመምከር አሳድጎና ስልጣኑን በመስጠት መቼም ቢሆን ጥቅሙ እንዲከበርለት በድርጅቱ ላይ እምነቱን በመጣልና ተስፋ በማድረግ ኃላፊነቱን ለሰጠው ህዝብ ድርጅቱ ሙሉ እምነት አለው፡፡ ላለፉት 15 ዓመታት ባካሄድነው ትግል ያጋጠሙን ችግሮች በስራ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች እንጂ የአቅጣጫ ችግር ያለመሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡
...
ከዚህ ችግር በመማርና በማስተካከል የህዳሴውን ምዕራፍ በድል መሠረት ለማስያዝ ስምምነት ላይ ደርሰናል፡፡ ዋነኛው ችግሮች ናቸው ብለን ከለየናቸው መካከል የህዝባዊ ወገንተኝነት ላይ ያለ አመለካከትና አብዮታዊ ዴሞክራሲ መሠረት በማድረግ በየደረጃ እያደገ የመጣው ከራስ ወዳድነት የተነሳ ስልጣን የህዝብን ማገልገያ መሣሪያ መሆኑን በመዘንጋት ከህዝብ በፊት ራስን መለወጥ የህዝብ አገልግሎት የተጓደለ በመምጣቱ በአስቸኳይ እነዚህን ችግሮች በማስተካከል ወደ ህዝባችን ልንመለስ ይገባል በሚል አቋም የትግላችንን ቃል እናድሳለን፡፡
...
የኦሮሞ ህዝብ ያለቡን ድክመቶችና ያስመዘገብናቸው ድሎች በማመዛዘን እውቅና በመስጠት ያሉትን ችግሮችን ጊዜ ሳናባክን እንድንቀርፍለት እንደሚሻ እንገነዘባልን፡፡
ከዚህ ቀደም የነበረንን ህዝባዊ ወገንተኝነት ስናጓድል ቅሬታና ኩርፊያ እንዳለው በተለየ ሁኔታ ስላሳየ የህዝቡን ቅሬታ ለመቅረፍ ለመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን በነቃ የህዝቡ ተሳትፎ እንደምንመልሰው ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡
...
በሌላ በኩል የመልካም አስተዳደር ችግሮችና በገጠርና በከተማ ያለው የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ በሁሉት አቅጣጫ ተመልክተናል የመጀመሪያ እየጨመረ የመጣው የህዝቡ የመለወጥና የመልማት ፍላጎት ካጋጠመን የማስፈጸም አቅም ወስንነት በሚፈለገው መጠን ሟሟላት አልተቻለም ፡፡ በዚህም ህዝቡ ቅሬታ ቢኖረውም የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር በኛ ትግልና የህዝቡ ታሳትፎ ችግሮችን እንደምንቀርፍ በመገንዘብ ህዝቡ በትዕግስት እንዲጠብቀን በከፍተኛ አክብሮት እንጠይቃለን፡፡
በዉስጥ አፈፃፀም ችግሮች ለጋጠመው የመልካም አስተዳደር እጦት ሕዝባችንን በክብር ይቅርታ ጠይቀን በከፍተኛ የዉስጥ ትግል እና የሕዝቡ ድጋፍ ሠርተን ሕዝቡን ለመካስ ቃል እንገባለን፡፡
...
በዉስጥ ችግራችንና እንከኖቻችን የተነሳ የገጠሙ ችግሮችን በመጠቀም በክልሉ ፀረ-ሰላም ሀይሎች ባናፈሱት አሉባልታ የፀጥታ ችግር ምክንያት ለጠፋዉ የሰዉ ሕይወት እና ንብረት ውድመት የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለፅን የጥፋት ሃይሎች ስረዓቱን ከመሠረቱ ለመናድና ድሎቻችንን ወደ ኋላ ለመመለስ ያደረጉት መፍጨርጨር ባለበት ቦታ እንዲቆምና ችግሮቻችንን እንደ ተለመደዉ በውይይት መፍታት እንዳለብን ለህዝባችን ጥሪ እናቀርባለን::
የጥፋት ሀይሎች አገርንና ስርዐቱን ለመናድ ያላቸዉን ተልዕኮ እንደተለመደው ትግሉ የሚጠይቀው መስዋዕትነት በመክፈል የምንታገል ሲሆን ለዚሁ የተለመደውን የኦሮሞ ሕዝብ ድገፍ እንጠይቃለን ፡፡
...
የፀረ-ሰላም ሃይሎችም በአቋራጭ በብጥብጥ ስልጣን ለመያዝ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ መቼም ሊሳካ እንደማይችል ተረድተዉ ከአሸባሪነትና ብጥብጥ ስራቸዉ እንዲታቀቡ በድጋሚ ማሣሠብ እንወዳለን፡፡

...
1ኛ- ድርጅታችን ከየትኛዉም ውጫዊ ችግር በማስቀደም በመጀመሪያ ውስጣዊ ችግሮቹን በጥልቀት በመመርመርና በማጥራት ድርጅታችንን በማጠናከርና ወደ ሕዝባዊ ወገንተኝነት በመመለስ ትግሉን በማቀጣጠል ለኦሮሞ ሕዝብ ጥቅምና መብት ልክ እንደትላንቱ በቆራጥነት ለመታገል ዝግጁ መሆናችችንን እናረጋግጣለን፡፡
...
2ኛ- ድርጅታችን ኦህዴድ ስልጣን የህብረተሰባችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጫ መሳሪያ መሆኑን ከመገንዘቡ የተነሳ የህዳሴያችንን ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንዲያስችለን ለህዘቡ ያለውን ወገንተኝነት እራስ ላይ አስከመወሰን ድረስ ለመግለፅ የድርጅታችን ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው በራሳቸው ፍቃድ ለመውረድ ለማዕከላዊ ኮሚቴው ጥቃያቄ በማቅረብ የድርጅቱ ሊቀመንበርና ምክትል ለቀመንበር ያቀረቡትን ጥያቄ ማዕከላዊ ኮሜቴው ውሳኔያቸውን በታላቅ አፅንዖት አይቶ በመወሰንና በአመራርነታቸው የነበራቸውን ተሳትፎ ግምት ውስጥ በማስገባት አንድ እርከን ዝቅ በማድረግ የድርጅቱ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው እንዲቀጥሉ ወስኗል፡፡
በምትካቸውም አዲስ የድርጅቱ ሊቀ-መንበርና ምክትል ሊቀመንበር ተተክቷል፡፡
...
3ኛ- በተጨማሪ በአመራርነታችን ክፍተት የመጡ ችግሮችን በጥልቀት በመመርመር የድርጅቱንና የመንግስትን ጠንካራ መዋቅር በማረጋገጥ የትግሉ ምዕራፍ የሚጠይቀውን አመራርነት ለመስጠት የህብረተሰባችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዝግጁነታችንን እንገልጻለን፡፡
...
4ኛ- የህብረተሳባችንን የእለት ተእለት ኑሮ ጠፍንጎ የያዙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት የችግሮቹን ምንነት በየደረጃው ለመፍታት ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራ ይሆናል፡፡የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ድርጊትን ያለምንም ምህረት ድል በማድረግ ለህዳሴያችን ጉዞ ስኬት እልህ አስጨራሽ ትግል እናደርጋልን፡፡ ለዚህም የእናንተን የተለመደውን ርብርብ እንሻለን፡፡
...
5ኛ- የህዳሴያችንን ጉዞ በአንድ ሌሊት ከዳር ማድረስ አዳጋች መሆኑ እውን ነው፡፡የህዳሴው ጉዞ በሂደትና ቀጣይነት ባለው መልኩ ከታሰበበት የሚደርስ መሆኑ ይታመናል፡፡ በመሆኑም በጥልቀት ለመታደስ በአመራሩ፣ በሰፊው አባላትና በህዝቡ ዘንድ ደርሶ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ያለ አንዳች እርፍት እንደምንሰራና ለህዳሴያችን ስኬት የሁላችንም ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ዛሬም እንደትናንቱ በእኔነት ስሜት እንድትረባረቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
...
6ኛ- አንድነታችን በማጠናከር ተጠቃሚነታችንን እንደምናረጋግጠው ሁሉ ከአገራችንና ጎረቤቶች ሕዝቦች ጋር በወንድማማችና መቻቻል ቅርርብ በመከባበር ልክ እንደ ትናንቱ ዛሬም ክንዳችንን አጠናክረን በድሕነትና ኋላ ቀርነት ላይ የጀመርነውን ትግል አጠናክረን በማስቀጠል ለአገርቱ የሕዳሴ ጉዞ ስኬት የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን፡፡
...
7ኛ- የሕዝቡንና የዴሞክራሲ ተቋማትን ግንባታና አደራጃጀት በማጠንከር በሁሉም ዘርፍ የሕዝቡን ተሣትፎ በተደራጀ መልኩ በማረጋገጥ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታውን መሬት በማስያዝ እያሣደግን ለመሔድ የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት ለመስራ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡
...
8ኛ- አገራችን የደረሰችበትን አገራዊ እድገት መሠረት የሕዝብ ልማት ስራችን በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መቷል፡፡ ይሁን እንጅ በክልላችን የተማረው ኃይልና ወጣቱ በሚፈለገው መልኩ ተጠቃሚ መሆን ባለመቻሉ ወጣቱና ቤተሠቦቻቸው ትክክለኛ ጥያቄ በመጠየቃቸው ድርጅታችን በከፍተኛ የተጠያቂነት መንፈስ እና ሙሉ እምነት በመቀበል ችግሩን ለመቅረፍ መስራት እንደጀመርነው በትኩረት በስፋት እንደምንሰራበት እና መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት እንደምንችል በሙሉ እምነት እንገልፃለን፡፡ በዚሁ የክልላችን ወጣቶች የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡
...
9ኛ- ድርጅታችን ከሕዝባዊ ወገንተኝነቱ የተነሳ አርሶአደሩ በተደጋጋሚ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች በተለይም በልማት ምክንያት ከመሬታቸው እንዲነሱ የተደረጉ አርሶ አደሮችን ጉዳይ በጥልቀት በመመርመር ተጠቃሚነታቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ለማረጋገጥ በጠንካራ አደረጃጀትና አሰራ በመደገፍ ከዚህ ቀደም በአፈፃፀም ይታዩ የነበሩ ችግሮችን ከመሰረቱ በማጥፋት ተጠቃሚነታቸውን እናረጋግጣለን፡፡
...
10ኛ- በድንበር አካባቢ በተለያዩ ጊዜያት የሚያጋጥመውን ግጭት በልዩ ትኩረትና ቆራጥነት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካት ጋ በመሆን ለመፍታ የምንሰራ መሆኑን በመግለፅ ሕብረተሰባችን ችግሮች ሲያጋጥሙ በሰላማዊና በተረጋጋ መንገድ ለማፍታት ርብርብ ማድረግ እንዳለበት ጥሪያችን እናቀርባለን፡፡
...
11ኛ- ሰላም ለሁሉም መሰረት መሆኑን ከሕብረተሰባችን በላይ የሚያውቅ አለ ብሎ መውሰድ አይቻልም፡፡ ከምንም በላይ ያሉበትን ችግሮች ትኩረት ሰጥቶ በማየት ለችግሩ እልባት ለመስጠት ብሎም ተጠቃሚ ለመሆን ወሳኙ ጉዳይ ሰላም ነው፡፡
ድርጅታችን ኦህዴድ ሁሌም ትልቁ ጠላታችን ድህነት ነው ብሎ ያምናል፡፡ ከዚህ በዘለለ በሰላማችንና ልማታችን ላይ እንቅፋት የሚሆኑት የጥፋት ኃይሎች ናቸው፡፡ ከዚህም ሌላ ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል በመናድ ስልጣንን በአቋራጭ ለመያዝ ለሚፈልጉ ኃይሎች ሕብረተሰባችን እንደማይፈቅድላቸው በተጨባጭ አረጋግጧል፡፡ ስለዚህ ሕብረተሰባችን በሁሉም ደረጃ ትልቅ መስዋዕትነት በመክፈል በግንባር ቀደምትነት የአካባቢውን ሰላም ለማስከበር ላደረገው ርብርብ ታላቅ ክብር እናቀርብላቸዋለን፡፡
ከዚህም በኋላ ለኑሯችን መሰረት የሆነው ሰላም እንዳይደፈርስ ሕብረተሰባችን አሁን ያደረገውን ትልቅ ተሳትፎ ተጠናክሮ በመቀጠል የጀመርነው ልማታችን ከዳር እንዲደርስ ከሕብረተሰባችን ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን ለመስራት ያለንን ዝግጁነት በግለፅ አሁንም ለሕብረተሰባችን ዳግም ጥሪያን እናስተላልፋለን፡፡
...
12ኛ- የአካባቢያችንን ሰላም ማረጋገጥ ወሳኝ እንደሆነ ሁሉ የሕግ የበላይነት መስፈንም ለዜጎቻን ኑሮ ትልቁ ዋስትና ነው፡፡ በመሆኑ ለዚሁ ስራ ስኬት የሰፊው ሕብረተሰባችን፤ የፍትህ አካትና የፀጥታ አካት ድርሻ ወሳኝ ነው፡፡ እጅ ለእጅ ተያይዘን የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሁሉም ዜጋ ያለአንዳች ሥጋት የተጀመሩ የልማት፤ የዴሞክራሲ ስርዓተር ግንባታ ስራዎችን ከዳር ማድረስ እንዳለበት ጥሪያችንን እንቀርባለን፡፡
...
በመጨረሻ የሕዳሴ ጉዟችን እንዲሳካ በማድጉ ረገድ ከምንም በላይ መዋቅሮቻን በትልቅ ዝግጁነት እንዲተገብሩና እንዲያስተገብሩ እንዱሁም ሕብረተሰቡ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ተሳትፎውን ማጠናከር እንዳለበት ጥሪ እናቀርባለን፡፡
የሕዳሴያችን ጉዞ እንዲሳካና የሕብረተሰባችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እውን እንዲሆን ርብርብ ማድረግ እንዳለባችሁ ታላቅ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
...
የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ
መስከረም 11/2009
ዓ.ም

አዳማ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa