ልጥፎች

ከኤፕሪል, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሙሉ የካብኔ አባላት ዝርዝር ( አዲስ አና ነባር ሚንስትሮች)

ምስል
1- ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር 2- ወርቁነህ ገበየሁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር 3- ሞቱማ መቃሳ የመከላከያ ሚኒስትር 4- ታዚስ ቾፋ የህዝብ አገልግሎት እና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር 5-ዶክተር አብረሃም ተከስተ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር 6- ከበደ ጫኔ የፌዴራል ጉዳዮች እና የአርብቶ አደርአካባቢዎችልማት ሚኒስትር 7- መላኩ አልበል የንግድ ሚኒስትሩ 8- ኡባ መሀመድ የኮሙኒኬሽንና ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር 9- አምባቸው መኮንን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር 10- ሂሩት ወልደማሪያም የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር 11- ሽፈራሁ ሸጉጤ የግብርናና እንስሳት ሀብት ሚኒስትር 12- ጌታሁን መኩሪያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር 13- ሲራጅ ፈርጌሳ ትራንስፖርት ሚኒስትር 14- ጃንጠራር አባይ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር 15- አስሻ መሐመድ የግንባታ ሚኒስትር 16- ስለሽ በቀለ የውሃ , የአትክልት እና የኤሌክትሪክ ስራ ሚኒስትር 17- መለሰ አለሙ የማዕድን ሚኒስቴር , የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር 18- ገመዶ ጋሌ የአካባቢ ጥበቃ , ደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር 19- ጥላዬ ጌጤ የትምህርት ሚኒስትር 20- ይናገር ደሴ የብሔራዊ እቅድ ኮሚሽን 21- አሚር አማን . የጤና ጥበቃ ሚኒስትር 22- ተሾመ ቶጋ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር 23 - ብርሃኑ ፀጋዬ ጠቅላ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በጎንደር ያደረጉት ሙሉ ንግግር

ምስል
የአብሮነትና የዘመናዊነት ተምሳሌት፤ የመካከለኛው ዘመን ስልጣኔ መሰረት እና የህዝባችን የከፍታ መሰላል፤ የባህል እና ውብ እሴቶቻቸችን ማህተም፤ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ጌጥ እና የትጉሀን ልጆች እናት፣ የኢትዮጵያችን የታሪክ አውድማ እና የኩሩ ህዝብ ምድር፣ የዛሬያችን መሰረት ትላንት በተጣለባት ድንቅ ከተማ ጎንደር ተገኝቼ መልዕክት ማስተላለፍ በመቻሌ የተሰማኝን ልባዊ ክብር ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጎንደር ጉልህ ድረሻ አላት፡፡ ጠቢባን ልጆችዋ በኪነ ሕንፃ የላቀ እርምጃቸው ዛሬም ድረስ የምንደመምበትን የፋሲል ቤተ-መንግስት አንፀው እንዳቆዩልን ሁሉ አብሮነትን ባካተተ ዝማኔ የመንግስት መቀመጫ ቀደምት ታሪክ አኑረዋል፡፡ ሊቃውንቶቿ አማርኛን ከንግግር ወደ ጽሁፍ ቋንቋነት ያሸጋገሩ ብቻም ሳይሆኑ አሻራቸው ዘመንና ትውልድን በተሻገሩ ስራዎች ህያው ሆነው ይኖራሉ፡፡ ጎንደር ከጃንተከል ጥላዋ ስር በዘመን ሀዲድ ላይ እያኖረች የመጣችው የመነጋገር፣ የመከራከር፣ የመወያየት፣ የመደማመጥ፣ የመቀራረብ፣ የመተሳሰብ እና ያለመናወጥ፤ የአብሮነት ካብ፣ የድንቅና ረቂቅ ባህል ለዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ባህል መዳበር ያለው አንድምታ ከፍተኛ ነው፡፡ ክቡራትና ክቡራን ለሀገራችሁ እና ለህዝባችሁ የምታሳዩት ፍቅር፤ ለቃላችሁ የምትሰጡት ክብር እና በሀገር አንድነት ላይ ያላችሁን ፅኑ አቋም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በውል ይረዳዋል፣ ያከብረዋል፡፡ እንኳንስ ጎንደር ከምድሯ- ከጥቁር አፈሯ ላይ ሆናችሁ ይቅር እና የህይወት እጣፈንታ ሰው ሀገር አድርሷችሁ እንኳን ወገናችሁን፣ ሀገራችሁን፣ እና ትላንታችሁን የማትረሱ እንደሆናችሁ እናውቃለን፡፡ በባህሪና በሁኔታ ቢለያዩም ቅሉ በየዘመናቱ እና በየመንግስታቱ የሚገጥሟችሁን ፈተናዎች የምትሻገሩበት ትእግስት፣ ወ

ለቁልፍ የመንግሥት ተቋማት ተጨማሪ ሹመቶች

ምስል
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የካቢኔ ሽግሽግ ካደረጉ በኋላ ለቁልፍ የመንግሥት ተቋማት ተጨማሪ ሹመቶችን ሰጥተዋል። በዚሁ መሰረትም ለስድስት ዓመታት የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ሆነው የሰሩትን አቶ አባዱላ ገመዳን በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሆነው ተሹመዋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል የነበሩት አቶ አሰፋ አብዩ ከቦታቸው ተነስተው አቶ ያሬድ ዘሪሁን ኮሚሽነር ጄነራል ሆነው ቦታውን ተረክበዋል። ባለፈው ሳምንት የሥራ መልቀቂያቸውን እንዳቀረቡ በተነገረላቸው ሜጀር ጄነራል ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ ምትክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተተክተዋል። ዶ/ር በቀለ ቡላዶ የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በመሆን ባለፈው ሳምንት የሥራ መልቀቂያቸውን እንዳቀረቡ የተነገረላቸውን የሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ቦታ ተረክበዋል። ዶ/ር በቀለ ኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ሲሰሩ ቆይተዋል። ወ/ሮ ደሚቱ ሀምቢሳ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር። በተጨማሪም ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ። አቶ ሞገስ ባልቻ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የጥናትና ፐብሊኬሽን ዘርፍ አስተባባሪ። አቶ አህመድ አብተው በሚኒስትር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር። አቶ ዓለምነው መኮንን በሚኒስትር ማዕረግ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንት።

ዛሬ ሹመታቸው በተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ የፀደቀላቸው ሚኒስትሮች

ምስል
1. አቶ ሽፈራው ሽጉጤ - የግብርናና እንሰሳት ሀብት ሚኒስትር 2. አቶ ሲራጅ ፌጌሳ - የትራንስፖርት ሚኒስትር 3. ዶክተር ሂሩት ወልደማሪያም - የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር 4. አምባሳደር ተሾመ ቶጋ - የመንግስት ልማት ድርጅት ሚኒስትር 5. አቶ ኡመር ሁሴን - በሚኒስትር ማእረግ የኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር 6. ወ / ሮ ኡባ መሀመድ - የመገናኛ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር 7. ዶ / ር አምባቸው መኮንን - የኢንዱስትሩ ሚኒስትር 8. አቶ ሞቱማ መቃሳ - የሀገር መከላከያ ሚኒስትር 9. ወ / ሮ ፎዚያ አሚን - ባህልና ቱሪዝም 10. አቶ አህመድ ሺዴ - በሚኒስትር ማእረግ የመንግስት ኮሙዪኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር 11. አቶ ጃንጥላ አባይ - የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር 12. አቶ መለሰ ዓለሙ - የማእድንና ኢነርጂ ሚኒስትር 13. አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ - ጠቅላይ አቃቤ ህግ 14. ወ / ሮ ያለም ፀጋዬ - የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ሚኒስትር 15. አቶ መላኩ አለበል - የንግድ ሚኒስትር 16. ዶ / ር አሚር አማን - የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በጠቅላይ ሚኒስትሩ በእጩነት ከቀረቡት የካቢኔ አባላት መካከል 10 አዳዲስ አባላት ሲሁኑ፥ ስድስቱ ወደ ሌላ የሚኒስትርነት ቦታ የተዘዋወሩ ናቸው።