የኢትዮጵያ ሕዝቦች የደስታ ሳምንት!


ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባለፈው ሰኞ መጋቢት 24 2010 ዓ.ም በተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ተሰይመው ቃለ መሃላ ከፈፀሙ በኋላ ባሰሙት ሁሉን አቀፍ ንግግር ላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ገንቢ አስተያየታቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ
ዜጎች ቀጣይ ስራዎች ላይ በማትኮር ነፃ ሆነው በመስጠት ላይ የሚገኙት አስተያየቶች ለተተኪው አመራር ቀጣይ ስራዎችና ውሳኔ መሰረት ሆኖ እንደሚያገለግል ይታመናል

ሁሉም ሰው በዚህ ሳምንት ለምን ተደሰትክ? ተብሎ ቢጠየቅ እንደየራሱ ምልከታ የተለያዩ አስተያየቶችን ሊሰጥ እንደሚችል መገመት ይቻላል፤በእኔ እምነት በአገር ወስጥም ሆነ በውጭ የሚገኘው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ፈካ ባለ ስሜት በመናገር ላይ የሚገኘው የሁሉም ነገር መሰረት የሆነው ሰላም በመውረዱ ነው፤ወደፊትም ሰላማችን ይብዛልን!
ባለፉት ሶስት አመታት በተለይም ባለፉት ጥቂት ወራት ሰላም በመደፍረሱ ምክንያት በሁላችንም ላይ የተፈጠረው ስጋት ተወግዶ ስለ እንድነት፤ስለ ወደፊት ተስፋና መፃኢ ዕድላችን መናገርና ሃሳብ መለዋወጥ ጀምረናል፤ይህ መልካም ነገር ነው መልካሙ ነገር ለሁላችን ይብዛልን!
እንደዜጋ የምንመኘው ሁሉም ነገር ተሳክቶ ደስታችን ዘላቂ መሆን የሚችለው ከአዲሱ አመራር ጎን ተሰልፈን በየተሰማራንበት የስራ ዘርፍ ሁሉ ግዴታና ኃላፊነታችንን ስንወጣ ብቻ እንደሆነ መገንዘብ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው
ከአሁን በኋላ የተለያዩ ምክንያችን በመደርደር የመጓተት አካሄዶችን ማስወገድ ይጠበቅብናል ይህን ለማለት የቻልኩት በሰሞኑ የአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች የታዘብኳቸው ነገሮች በመኖራቸው ነው
“አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከጋራ አመራር ውጭ ምንም ነገር ላይ መወሰን አይችሉም” ማለት ምን ማለት ነው?በጋራ አመራር ውሳኔ የሚሰጥባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሁሉ የኢትዮጵያ ሕዝቦችና ሕገ መንግስቱ በሰጣቸው ስልጣን መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየትኛውም የህዝቦች ተጠቃሚነት  ጉዳይ ላይ መወሰን እንደሚችሉ ማመን መቻል ተገቢ ነው
ይህን ማመንና መቀበል የማይፈልግ ዜጋ፤ግለሰቦችና አካላት በሙሉ ለውጡን እንደማይፈልጉና የለውጡ አደናቃፊዎች ስለሆኑ ለኢትዮጵያ አገራችን ገናና ስም መመለስ ብርቱ ጉጉት ያለን ዜጎች ሁሉ በንቃት ተከታትለን የተሳሳተው ወገን ወደ ትክክለኛው አካሄድ እንዲመለስ ማድረግ ይጠበቅብናል
ይህ ሲሆን በዚህ ሳምንት በተለያየ መንገድ በአንደበታችን ያንፀባረቅነው የደስታ ስሜት እጥፍ ድርብ ሆኖ ቀጣይ ይሆንልናል፤አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በታሪካዊ ንግግራቸው እንደረጋገጡት በጋራ አገራችን የትኛውም ጉዳይ ላይ በማበር አንድ ሆነን በጋራ ስንቆም የማናሸንፈው ችግር አይኖርም

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman