የተቃውሞ ጥሪው ለእነ ማን ነው?ዓላማውስ?


ከሰሞኑ በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተቃውሞ እንዲነሳ ጥሪ እየተደረገ ስለመሆኑ እየተነገረ ነው ለመሆኑ የተቃውሞ ጥሪው ለእነ ማን ነው? ጥሪውን በማስተላለፍ ላይ የሚገኙ ወገኖችስ እነ ማን ናቸው? ወደ ኋላ ላይ የራሴን ግምት ለመግለፅ እሞክራለሁ
ጥሪው ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ቡራዩ ከተማና አካባቢዋ በአፋን ኦሮሞና በአማርኛ ቋንቋ ተፅፎ የተበተነ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎችም ተለጥፎ መገኘቱን የአይን እማኞች ሲናገሩ ተሰምቷል
የጥሪው ዋና መልዕክት ለተቃውሞ ተነሱ! የሚል ሲሆን የክላሽ ምስልም በተበተነው ወረቀት ላይ እንደሚታይ ተነግሯል ለመሆኑ ጥሪው ለእነ ማን ይሆን? ጥሪው የተላላፈው ለኦሮሞ ሕዝብ ነው ሊባል የሚችል አይመስለኝም ምክንያቱም የኦሮሞ ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ምላሽ በማግኘት ላይ ስለሚገኝ በአሁኑ ወቅት ኦሮሞ  ለተቃውሞ ይነሳሳል የሚል እምነት የለኝም
ከኦሮሞ ጋር በመኖር ላይ የሚገኙ ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችም አሁን የማኛውንም ኃይል የተቃውሞ ጥሪ ተቀብለው ሆ ብለው የሚወጡበት ሁኔታ እንደሌለ ይታወቃል ምክንያቱም ልክ እንደ ኦሮሞ ሕዝብ ሁሉ ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦችም ሰላም ፈላጊ ናቸውና
እነ “ጭር ሲል አልድም” መቼስ ምን ይሳናቸዋል? ጥቅማቸው የሚጠበቀው ሰላም ሲደፈርስ ስለመሆኑ ጠንቅቀው ያውቃሉና ጥቅማቸውን ለማስከበርና ቀጣይ ለማድረግ ምንም ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይሉ ያለፈው ሂደታቸው ምስክር ነው
የራሴ ግምት!
ከዚህ እኩይ ጥሪ ጋር በተያያዘ የራሴን ግምት ባስቀምጥ ማን ምን ይለኛል? ማንም ምንም እንደማይለኝ አውቃለሁ ስለዚህ ግምቴ ግልፅ ነው ብዬ አስባለሁ ግምቴ የተሳሳተ ነው ከተባለም የሚያርመኝን ወገን በደስታ እቀበላለሁ
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ሰላም እንዲሰፍን በማድረግ ላይ ያሉት ጥረት ይታወቃል፤ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰላም እንዲሰፍን የማይፈልጉና ሰላም ሲሰፍን ጥቅማቸው የሚነካባቸው ኃይሎችና በጠቅላይ ሚኒስትሩ መመረጥ ቆፈን የያዛቸው ያኮረፉ ግለሰቦች የጥሪው ባለቤቶች ሊሆኑ ይችላሉ ጥቅሙ ሲነካበት አርፎ መቀጥ የሚችል የለምና

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman