የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሹም ሽር
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ የተጀመረውን ተሃድሶ አጠናክሮ በመቀጠል የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚነት ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማሸጋገር የጀመረውን ትግል በማጠናከር ግስጋሴውን ቀጥሏል
በዚሁ መሰረት በአሁኑ ወቅት የተደረሰበትን የትግል ምዕራፍ ከግምት በማስገባ የአመራር ምደባን በድጋሚ አድርጓል፤ይህ የአመራር ምደባ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩ ዋና ዋና ነጥቦችን መሰረት በማድረግ የተፈፀመ ነው
1ኛ የመንግስትን የማስፈፀም አቅም በማጠናከር የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ማስወገድ፤ስለዚህ ብቃትና ከፍተኛ ቁርጠኝነት ያለው አመራር በተለያየ ደረጃ መመደብ በክልል ደረጃ በመከናወን ላይ ያለውን ተሃድሶ አጠናሮ መቀጠል ነው
2ኛ.ክልሉ በፌዴራል ደረጃ ያለውን የአመራር ድርሻ በከፍተኛ ብቃት ለመወጣት ከክልል ለፌዴራል መንግስት የሚደረገውን የአመራር አስተዋፅኦ ከግምት ያስገባ ነው
3ኛ.ሴቶች፤ወጣቶችና ምሁራን በአመራር ውስጥ ያላቸውን ድርሻ ለማጠናከር ታስቦ የተከናወነ ምደባ ነው በድጋሚ የተካሄደው የአመራር ምደባ በሁሉም ደረጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል በዚሁ መሰረት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘረው ሹመት ተሰጥቷል
1.ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር
2.ዶክተር ግርማ አመንቴ የኦሮሚያ ከተሞችና ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ
3.ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅ/ቤት ኃላፊ
4.አቶ አዲሱ አረጋ በኦህዴዴ ማዕከላዊ ፅ/ቤት የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ኃላፊ
5.አቶ ከፍያለው አያና በኦህዴድ ማዕከላዊ ፅ/ቤት የከተማ ፖለቲካ አደረጃጀት ኃለፊ
6.ዶክተር ነገሪ ሌንጮ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ
7.አቶ አሰግድ ጌታቸው የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ኃለፊ
8.ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የኦሮሚያ ገቢዎች ባለስልጣን ኃለፊ
9.ዶክተር ምልኬሳ ሚደጋ የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
10.ዶክተር አለሙ ስሜ የኦሮሚያ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ
11.አቶ ሲሳይ ገመቹ የኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ልማትና ማስፋፊያ ኤጄንሲ ዳይሬክተር
12.ወይዘሮ ሃቢባ ሲራጅ የለገ ጣፎ ለገ ዳዲ ከንቲባ
13.ወይዘሮ እልፍነሽ በዬቻ ገለታ የአዳማ ከተማ ከንቲባ
14.ወይዘሮ ዘይነባ አደም የአሰላ ከተማ ከንቲባ
15.አቶ መሃመድ ከማል የምዕራብ አርሲ ዞን አስተዳዳሪ
16.አቶ ለሊሳ ዋቅወያ የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ
17.አቶ ጫሊ ቤኛ የቡራዩ ከተማ ምክትል ከንቲባ
18.አቶ ደስታ ቡኩሉ የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ
19.አቶ ከባ ሁንዴ የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ
20.አቶ አሰፋ ኩምሳ የኦሮሚያ ዲዛይንና ውሃ ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ኃላፊ
21.አቶ አበራ ቡኖ የምዕራብ ጉጂ ዞን አስተዳዳሪ
22.አቶ ነብዩ ደብሱ የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ
23.አቶ ቦጋለ ሹማ የነቀምቴ ከተማ ከንቲባ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ