ለቁልፍ የመንግሥት ተቋማት ተጨማሪ ሹመቶች

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የካቢኔ ሽግሽግ ካደረጉ በኋላ ለቁልፍ የመንግሥት ተቋማት ተጨማሪ ሹመቶችን ሰጥተዋል።
በዚሁ መሰረትም ለስድስት ዓመታት የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ሆነው የሰሩትን አቶ አባዱላ ገመዳን በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሆነው ተሹመዋል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል የነበሩት አቶ አሰፋ አብዩ ከቦታቸው ተነስተው አቶ ያሬድ ዘሪሁን ኮሚሽነር ጄነራል ሆነው ቦታውን ተረክበዋል።
ባለፈው ሳምንት የሥራ መልቀቂያቸውን እንዳቀረቡ በተነገረላቸው ሜጀር ጄነራል ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ ምትክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተተክተዋል።
ዶ/ር በቀለ ቡላዶ የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በመሆን ባለፈው ሳምንት የሥራ መልቀቂያቸውን እንዳቀረቡ የተነገረላቸውን የሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ቦታ ተረክበዋል። ዶ/ር በቀለ ኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ሲሰሩ ቆይተዋል።
ወ/ሮ ደሚቱ ሀምቢሳ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር።
በተጨማሪም ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ።
አቶ ሞገስ ባልቻ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የጥናትና ፐብሊኬሽን ዘርፍ አስተባባሪ።
አቶ አህመድ አብተው በሚኒስትር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር።
አቶ ዓለምነው መኮንን በሚኒስትር ማዕረግ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንት።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman