ከመንግስት በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት በጸጥታ ሀይሎች ትጥቅ የማስፈታት ስራ እየተከናወነ ነው

በሞያሌ ከተማ በተደራጀና በህቡእ ዝግጅት በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ደርሷል።
ከመንግስት በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት በጸጥታ ሀይሎች ትጥቅ የማስፈታት ስራ እየተከናወነ ነው
በሞያሌ ከተማ በተደራጀ ሁኔታ በተከሰተውና ህብረተሰቡን ኢላማ ባደረገ ግጭት የሰው ህይወት መጥፋቱ እና የመቁሰል አደጋ መድረሱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፓስት ሴክሬታሪያት አስታወቀ።
ኮማንድ ፖስቱ በመግላጫው ሚያዚያ 28 ቀን 2010 በሞያሌ ከተማ በተደራጀና በህቡእ ዝግጅት በተደረገበት የጥፋት ተልዕኮ በሁለት ጎራዎች የታጠቁ ኃይሎች መካከል ማህበረሰብን ዒላማ ያደረገ በመጠኑም ሰፋ ያለ ግጭት ተከስቶ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ደርሷል።
ተከስቶ የነበረው ግጭት የፀጥታ ሀይሉ የተቆጣጠረው ሲሆን፥ በዚህ ጥቃት የተሳተፉ እና ድርጊቱን የመሩ ሀይሎችን በመለየት በቁጥጥር ስር ለማዋልም ጥረት እየተደረ መሆኑን ነው ኮማንድ ፓስቱ ያስታወቀው።
በተጨማሪም በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በስፋት እየተካሄደ ሲሆን፥ በሚያዚያ ወር ብቻ 142 ክላሽ፣ 88 ሽጉጥ፣ 11 የእጅ ቦምቦች እና 17 ኋላቀር መሳሪያዎች ከበርካታ ተተኳሾች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።
ኮማንድ ፖስቱም በሞያሌ ከተማ የተከሰተው ችግር ከህገ-ወጥ መሳሪያ ጋር ተያይዞ የተከሰተ መሆኑ ነው ያስታወቀው።
በዚህም በሞያሌ ከተማ ከመንግስት በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት በጸጥታ ሀይሎች ትጥቅ የማስፈታት ስራ እየተከናወነ ሲሆን፥ በሌሎች ጥናት በተደረገባቸው አካባቢዎች ትጥቅ የማስፈታቱ ሂደት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።
ሰዎችም ለራስ እና አካባቢን ለመጠበቅ የሚይዙትን ህጋዊ መሳሪያዎች ለግጭት እና ለህገ-ወጥ ድርጊቶች መጠቀም የለባቸውም ሲል ኮማንድ ፖስቱ አሳስቧል

Source:FBC(Fana Broadcasting Corporate)

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman