ኦህዴድ በዞንና በከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በድርጅት ፅ/ቤቶች አዳዲስ አመራሮች መመደቡን ዛሬ ይፋ አደረገ
ኦህዴድ በዞንና በከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በድርጅት ፅ/ቤቶች አዳዲስ አመራሮች መመደቡን ዛሬ ይፋ አደረገ
በጨፌ ኦሮሚያ አብላጫ ወንበር በመያዝ የኦሮሚያ ክልልን በመምራት ላይ የሚገኘው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) በዞን እና በከተማ አስተዳደሮች ደረጃ አዳዲስ የአመራር ምደባ ማድረጉን የድርጅቱ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ገለፁ።
አቶ አዲሱ፥ ኦህዴድ በህዝቡ ዘንድ የቅሬታ ምንጭ የሆኑ ችግሮችን ለመቅረፍ ጠንክሮ በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል።
ኦህዴድ ከመልካም አስተዳደር፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ እና ከልማት ስራዎች መጓተት ጋር
ተያይዘው የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታትና የህግ የበላይነትን ለማስከበር እንዲሁም የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ወደ አዲስ ምእራፍ ማሸጋገር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ያምናል ብለዋል አቶ አዲሱ።
ስለዚህ ድርጅቱ በሁሉም ደረጃ የክልሉን መንግስት የማስፈፀም አቅም በየጊዜው እየፈተሸ ማስተካከያ ማድረግ እና ማጠናከር አስፈላጊ ነው ብለዋል።
በዚሁ መሰረት ኦህዴድ ሰሞኑን ባካሄዴው ግምገማ ላይ በመመስረት የአዳዲስ አመራር ምደባ አድርጓል ያሉት አቶ አዲሱ፥ በዞን እና በከተማ አስተዳደር በቀበሌ ደረጃ እየተደረገ ያለው የአመራር ምደባ ማስተካከያም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታውቀዋል።
ማስተካከያውን ተከትሎ በተካሄደው የአዳዲስ የአመራር ምደባ መሰረትም፦
የክልሉ መንግስት የሰጣቸው ሹመቶች
አቶ ሲራጅ አብዱልጀባር- የባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
አቶ ሮባ ቶልጬ ሳፋይ- የጉጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
አቶ ዴንጎ ቦሩ ቆሲ- የቦረና ዞን ዋና አስተዳዳሪ
አቶ ገመቺስ ጉታ ጆቴ- የሆሮ ጉዱሩ ወላጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
አቶ ገመቺስ ተመስገን- የምስራቅ ወለጋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ
ወ/ሮ አለምፀሃይ ሽፈራው- የቢሾፍቶ ከተማ ከንቲባ
ወ/ሮ ካባ መብራቱ- የወሊሶ ከተማ ከንቲባ
ወ/ሮ ቢቂልቱ ከተማ በቀለ - የአምቦ ከተማ ከንቲባ
አቶ ሚኤሳ ኤሌማ- የሻሸመኔ ከተማ ምክትል ከንቲባ
አቶ ተሾመ ጂፋር- የሞጆ ከተማ ምክትል ከንቲባ
አቶ በዳዳ መርጋ- የጅማ ከተማ ምክትል ከንቲባ
አቶ ነቢ ጉታ- የባቱ ከተማ ምክትል ከንቲባ
አቶ ደሳለኝ ኦልቀባ- የሆሮ ጉዱሩ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ
ኦህዴድ የሰጣቸው ሹመቶች
አቶ ተፈሪ ንጋቱ- የአሰላ ከተማ የኦህዴድ ጽህፈት ቤት ሀላፊ
አቶ ሀሚድ ቱርሲ- የሻሸመኔ ከተማ የኦህዴድ ጽህፈት ቤት ሀላፊ
አቶ ሰንበታ አደባ- የነቀምቴ ከተማ የኦህዴድ ጽህፈት ቤት ሀላፊ
ወ/ሮ ጣይቱ ያሚ- የሞጆ ከተማ የኦህዴድ አደረጃጀት ጽህፈት ቤት ሀላፊ
አቶ ፀጋዬ ተክለሀና- የሞጆ ከተማ የኦህዴድ የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ
አቶ ደባ አመንቴ- የቡራዮ ከተማ የኦህዴድ የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ
አቶ ድሪባ መኮንን- የሱሉልታ ከተማ የኦህዴድ የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ
አቶ ገነሞ ያቺሲ- የቢሻን ጉራቻ ከተማ የኦህዴድ የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ
አቶ እንዳሻው ብርሃኑ- የባሌ ዞን የኦህዴድ ጽህፈት ቤት ሀላፊ
አቶ ገዛኸኝ ከበደ- የምእራብ ሸዋ ዞን የኦህዴድ ጽህፈት ቤት ሀላፊ
አቶ ታደሰ ወገኔ- የሰሜን ሸዋ ዞን የኦህዴድ ጽህፈት ቤት ሀላፊ
ወ/ሮ መዲና ከድር- የአርሲ ዞን የከተማ ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ
አቶ ብርሃኑ ኤባ የምስራቅ ወለጋ ዞን የከተማ ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ
የአዳዲስ አመራር ምደባው የምሁራን፣ የወጣቶች እና የሴቶችን ተሳትፎ ግምት ውስጥ በማስገባት የተካሄደ መሆኑን አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል።
የአመራር ምደባው ላይ ክትትል የሚደረግ መሆኑን የገለፁት አቶ አዲሱ፥ በሚደረገው ክትትል ጉድለት በሚታይባቸው ስፍራዎች ላይ የሚደረገው የአመራር ማስተካከያ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ