የማዕድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴርን ለትዝብት ያጋለጡ ዘገባዎች



ሚኒስቴሩ በራሱ መንገድ ከኬሚካል አንፃር ናሙናዎችን ወስዶ አውሮፓ ድረስ በመላክ አስጠንቷል
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሶስተኛ ወገን በመሆን በዚህ ሂደት መሳተፉንም ነው -የማእድን ነዳጅና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ቴድሮስ ገብረእግዚአብሄር ያስታወቁት።
ዘገባዎቹን ያንብቡ

የማዕድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ለሜድሮክ ጎልድ በለገ ደንቢ የወርቅ ማእድን ማውጣት ፍቃድ እድሳት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን እንደሚያይ ገለፀ።
ከፍቃድ እድሳቱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ውዥንብር ለመፍታት ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑን ነው የማእድን ነዳጅና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ቴድሮስ ገብረእግዚአብሄር የተናገሩት።
እንደ አቶ ቴድሮስ ገለጻ፥ ለሜድሮክ ጎልድ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ለገ ደንቢ የወርቅ ማእድን ልማት የፍቃድ እድሳት መደረጉን ተከትሎ የተፈጠረው ችግር ለአካባቢው ነዋሪዎች መረጃ ከመስጠት አንፃር የተፈጠረ ክፍተት አለ።
ለሜድሮክ ጎልድ የፍቃድ እድሳቱ ከመደረጉ በፊት ኩባንያው የራሱን የአካባቢ ጥበቃ ኦዲት ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያቀረበ መሆኑንም አቶ ቴድሮስ ገልፀዋል።
ሚኒስቴሩም በራሱ መንገድ ከኬሚካል አንፃር ናሙናዎችን ወስዶ አውሮፓ ድረስ በመላክ አስጠንቷል ብለዋል።
ከዚህ ባለፈም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሶስተኛ ወገን በመሆን በዚህ ሂደት መሳተፉንም ነው ሚኒስቴር ዴታው ያስታወቁት።
ለሜድሮክ ጎልድ 10 ዓመት የተደረገው የፍቃድ እድሳትም በዚህ መረጃ ላይ ተመስርቶ የተሰጠ መሆኑን ነው ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ቴድሮስ የተናገሩት።
ከዚህ ውጭ ፍቃዱን ተከትሎ የተፈጠሩ ችግሮችን ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር ውይይት እየተደረገበት ሲሆን፥ በውይይቱ ሂደት የሚኖሩ ግኝቶች ካሉ ሚኒስቴሩ ያየዋል ብለዋል።
ሜድሮክ ጎልድ ላለፉት 20 ዓመታት በአካባቢው ላይ የወርቅ ማእድን ሲያወጣ የቆየ ሲሆን፥ ከዘርፉም በየዓመቱ 200 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ሲያስገኝ ቆይቷል ይለናል አንድ የፋና ብሮድካስቲነገ ኮረፖሬት ጋዜጠኛ ከአንድ ሳምንት በፊት ለአየር ያበቃው ዘገባ፤ፋና ይህን ዘገባ ለአየር ሲያበቃ ተደረጉ የተባሉትን ጥናቶችን ማሳየት አለመቻሉ ራሱንም ለትዝብት የዳረገው ይመስለኛል
ትናንት ደግሞ ፋናን ጨምሮ ሌሎች ሚዲያዎች ከሚኒስቴሩ አገኘን ብለው ቀጣዩን ዘገባ ለሕዝብ አደረሱ እንዲህ ይላል
የሚድሮክ ጎልድ የለገደምቢ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ፍቃድ ከዛሬ ጀምሮ መታገዱን የኢፌዴሪ የማዕድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ በኦሮሚያ ክልል ጉጅ ዞን ሚድሮክ ጎልድ በለገደምቢ በሚያካሂደው የወርቅ ማዕድን ልማት ስራ ላይ የአካባቢው ነዋሪ፥ የኩባንያው የምርት ሂደት የአካባቢ ብክለት እያስከተለ ነው የሚል ቅሬታ ማንሳቱን ተከትሎ ነው ፍቃዱን ያገደው።
በገለልተኛ አካል ጥልቀት ያለው ጥናት እስከሚጠና ድረስ የኩባንያው ወርቅ የማምረት ስራው መታገዱንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ጥናቱ በገለልተኛ አካል ከፌደራል እስከ ቀበሌ ያሉ አመራሮችን እና ባለ ድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ እንደሚካሄድ፥ የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ባጫ ፋጂ ተናግረዋል።
የኩባንያው ወርቅ የማምረት ሂደት መቀጠል ያለመቀጠል ሂደትም በጥናቱ ውጤት ላይ የተመሰረተ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
አዲስ ጥናት ሲሰራም የጥናቱ ወሰን ከዚህ በፊት ከተደረገው እንዲሰፋ እንደሚደረግ ጠቅሰው፥ የሚወሰዱ ናሙናዎች ቁጥርም ከፍ ይደረጋል ብለዋል።
የነበረው አዋጅ የሚድሮክ ጎልድ የለገደምቢ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ፍቃድ እድሳት እንዲደረግ እንደሚፈቅድ ያነሱት ዳይሬክተሩ፥ የኩባንያው የወርቅ አመራረት ሂደት በአካባቢው ችግር እየፈጠረ መሆኑን ሚኒስቴሩ እንዳመነበት አንስተዋል።
ይህን ተከትሎም የኩባንያው የወርቅ ማዕድን ማውጣት ፍቃድ ከዛሬ ጀምሮ መታገዱን አስረድተዋል።
አሁን የተወሰደው እርምጃም ለህዝቡ ጥያቄ ምላሽ ይሆናል ብለው እንደሚያምኑም ገልጸዋል።
ከሚድሮክ ጎልድ የለገደምቢ የወርቅ ማዕድን ጋር በተያያዘ በገለልተኛ አካል የሚደረገው የጥናት ሂደትም ዛሬ ተጀምሯል።
የጥናቱ አጠቃላይ ውጤት ምን ያክል ጊዜ እንደሚወስድና መ እንደሚጠናቀቅ ግን የተባለ ነገር የለም።
መቼም ቢሆን ሕዝብ አሸናፊ ነው!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman