የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የአገር ሽማግሌዎች በአዲስ አበባ ይገኛሉ
ዛሬ ከታማኝ
ምንጭ ለማረጋገጥ እንደቻልኩት ከሁሉም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጎሳዎች የተውጣጡ የአገር ሽማግሌዎች ወደ አዲስ አበባ መጥተዋል
በቁጥር
100 የሚደርሱ የአገር ሽማግሌዎች ወደ አዲስ አበባ የመጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳር በቅርቡ የሰጡትን ሹመት በመቃወምና በጉዳዩ
ላይ ከፌዴራል መንግስት ጋር ለመወያየት እንደሆነ ታውቋል
የኢትዮጵያ
ሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሃመድ በቅርቡ ባደረጉት ሹም ሽር የራሳቸውን ጎሳ አባላትና የሚቀርቧቸውን ሰዎች ብቻ
ወደ ተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ማምጣታቸውና ይህም የሌሎች ጎሳ አባላትና የክልሉን ሕዝብ ሰሞኑን እንዳስቆጣ ሲነገር ቆይቷል
የክልሉ
የአገር ሽማግሌዎች አዲስ አበባ ውስጥ በሆቴል የሚገኙ ሲሆን የዕለት በዕለት የሆቴል ወጪ በመሰቃየት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል
ቀደም
ሲል የአቶ አብዲ አስተዳደር አንድ ሚሊየን ገደማ ኦሮሞዎች ከጂጂጋና አካባቢዋ እንዲሁም ከሶማሌ ክልልና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች
በአሳቃቂ ሁኔታ እንዲፈናቀሉ በማድረጉ ሲወቀስ የቆየ ሲሆን ይህም የሆነው የሌሎች ኃይሎችን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል የተደረገ እንጂ
የኦሮሞና የሶማሌ ክልል ሕዝብ እርስ በርሱ በመጠላላቱ እንዳልሆነ እስከ አሁን በመነገር ላይ ይገኛል
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ