ልጥፎች

ከኤፕሪል, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ሕገ መንግስቱ በዘመቻ አይቀየርም!

ምስል
ፊንፊኔ ሚያዝያ 17/2011(ቶለዋቅ ዋሪ) በደፈናው ሕገ መንግስቱ ይቀየር ማለት አንዴት ይቻላል? ቀደም ሲል ሕገ መንግስቱ ሕገ አራዊት ነው ተብሎ ነበር ሕገ መንግስቱ ሊሻሻል ይችላል መሻሻልም አለበት ሕገ መንግስቱ ይቀየር የሚለው ዘመቻ ግን የሚያግባባ አይደለም ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ሕገ መንግስቱን ማክበርና ማስከበር የሁሉም ዜጎች ግዴታ ነውና ሕገ መንግሰት ዝም ብሎ በዘመቻና በጫጫታ መቀየር የሚችል ቢሆን ኖሮማ ለበርካታ አመታት የተለያዩ ኃይሎች ብርቱ ጥረት ሲያደርጉ አይተናል ታዝበናል በዘመቻ በሰላማዊ ሰልፍና በጩኸት ሕገ መንግስት ይቀየር ማለት ፀረ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ነው ፀረ ዴሞክራሲዊ አካሄድ ደግሞ ተቀባይነት የለውም ጎጂ ነው ማንም ሊጠቀምበት አይችልም ሕገ መንግስቱ አሁን ኢትዮጵያ ከደረሰችብት የዕድ ገት ደረጃ ጋር አይሄድም መሻሻል ይገባዋል ብሎ መከራከር ተገቢ ነው እሱም የራሱ አካሄድ አለውⵆ መባል ያለበት ሕገ መንግስት ይቀየር ሳይሆን ሕገ መንግስታችን ለብዙ አመታት አገልግሏል አሁን ዘመን ተለውጧል የህዝቡ የግንዛቤ ደረጃም ተለውጧል የተለያዩ ፍላጎቶችም አሉ ስለዚህ ሁሉም ህዝብ ተሳታፊ ሆኖበት ህገ መንግስቱ በውይይት ይሻሻል ነው በደፈናው ሕገ መንግስቱ ስለ ብሄር ትኩረት አድርጓልና ይቀየር ይደምሰስ ማለት አንዴት ተቀባይነት ሊኖረው አንደሚችል የሚያውቁት ዘመቻውን ለማካሄድ ያቀዱ ኃይሎች ብቻ ናቸው፤አብዛኛው የአገሪቱ ሕዝብ ግን ይህን ፅንፍ የወጣ አካሄድ በፍፁም ሊቀበል አንደማይችል መረዳት አለመቻል ከእኔ አውቅልሃለሁ የቆየ በሽታ የሚመነጭ ነው መታወቅ ያለበት ቁምነገር ሕገ መንግስቱ የኢህአዴግ ሕገ መንግስት አይደለም ሕገ መንግስቱ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ንብረት ነው ኢህአዴግን በጭፍን መጥላት ይቻላል ዴ

የቡርቃ ዝምታ እና አዲሱ አረጋ

ምስል
ሂስ አንድን መጽሀፍ በሚገባ የተረዳ፣ የመረመረ እና ጠልቆም የፈተሸ ግለሰብ መጽሃፉን በሚገባ ካጠናው በኋላ የራሱን አተያይ ወይም ሂስ ከመጽሐፉ በሚያነሳቸው ነጥቦች እያስረገጠ ሂሱን አጉልቶ በማሳየትና ምክረ - ሃሳብ ወይም የድምዳሜ ነጥቦችን በማስቀመጥ የውይይት በር የሚከፍትበት አካዳሚያዊ ተግባር ነው። ሂሱን ለታዳሚ የሚያቀርብ ከሆነ ደግሞ ታዳሚን በሚመጥን መልኩ የደረሰበትን ሃሳብ አጉልቶ በማሳየት የራሱን የድምዳሜ ነጥቦች በዝርዝር በመተንተን ማቅረብና ማስረዳትም ነው። አቶ አዲሱ አረጋ የቡርቃ ዝምታ በተሰኘው የተስፋዬ ገብረ አብ መጽሀፍ ላይ ያቀረበውን ጥናታዊ ሂስ የመታደም እድል ካገኙት ውስጥ አንዱ ነኝ፡፡ ከሂስ ቀረባው በኋላ እዚህም እዚያም የሚሰሙት ኮሸታዎች እና ወደ ጽሁፍ አቅራቢው የሚሰነዘሩት ያላዋቂ ትንተናዎች ይህችን ጽሁፍ እንድጽፍ አነሳስተውኛል፡፡ የጽሁፌ አቢይ ትኩረት የጸሀፊዎቹን እይታ ማረቅ አይደለም፤ በፍጹም፡፡ ምክንየቱም የአብዛኛዎቹ ( ምናልባትም የሁሉም ) የፌስቡክ መንደር ልሂቃን ትኩረት እና እውነት የኦሮሞ ታሪክ ወይም የኦሮሙማ ፍቅር ሳይሆን የፍቅረ ንዋይ እና የጭር ሰል አልወድም ልክፍት እንደሆነ ከእርግጠኝነትም በላይ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ማሳያ አንድ አዲሱ አረጋ ሂስ ያቀረበበት መጽሀፍ ልቦለድ እንጂ የኦሮሞ ህዝብ የታሪከ ሰነድ አይደለም፡፡ የጯሂዎቹ አይን እና ልብ እስከተከፈተ ድረስ ይህንን ማረጋገጥ የሚያስቸሉ እልፍ ሰበቦችን መዘርዘር ይቻላል፡፡ የታላቁን ህዝብ ታላቅ ታ