ሕገ መንግስቱ በዘመቻ አይቀየርም!

ፊንፊኔ ሚያዝያ 17/2011(ቶለዋቅ ዋሪ) በደፈናው ሕገ መንግስቱ ይቀየር ማለት አንዴት ይቻላል? ቀደም ሲል ሕገ መንግስቱ ሕገ አራዊት ነው ተብሎ ነበር ሕገ መንግስቱ ሊሻሻል ይችላል መሻሻልም አለበት ሕገ መንግስቱ ይቀየር የሚለው ዘመቻ ግን የሚያግባባ አይደለም ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ሕገ መንግስቱን ማክበርና ማስከበር የሁሉም ዜጎች ግዴታ ነውና
ሕገ መንግሰት ዝም ብሎ በዘመቻና በጫጫታ መቀየር የሚችል ቢሆን ኖሮማ ለበርካታ አመታት የተለያዩ ኃይሎች ብርቱ ጥረት ሲያደርጉ አይተናል ታዝበናል በዘመቻ በሰላማዊ ሰልፍና በጩኸት ሕገ መንግስት ይቀየር ማለት ፀረ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ነው
ፀረ ዴሞክራሲዊ አካሄድ ደግሞ ተቀባይነት የለውም ጎጂ ነው ማንም ሊጠቀምበት አይችልም ሕገ መንግስቱ አሁን ኢትዮጵያ ከደረሰችብት የዕድገት ደረጃ ጋር አይሄድም መሻሻል ይገባዋል ብሎ መከራከር ተገቢ ነው እሱም የራሱ አካሄድ አለውⵆ
መባል ያለበት ሕገ መንግስት ይቀየር ሳይሆን ሕገ መንግስታችን ለብዙ አመታት አገልግሏል አሁን ዘመን ተለውጧል የህዝቡ የግንዛቤ ደረጃም ተለውጧል የተለያዩ ፍላጎቶችም አሉ ስለዚህ ሁሉም ህዝብ ተሳታፊ ሆኖበት ህገ መንግስቱ በውይይት ይሻሻል ነው
በደፈናው ሕገ መንግስቱ ስለ ብሄር ትኩረት አድርጓልና ይቀየር ይደምሰስ ማለት አንዴት ተቀባይነት ሊኖረው አንደሚችል የሚያውቁት ዘመቻውን ለማካሄድ ያቀዱ ኃይሎች ብቻ ናቸው፤አብዛኛው የአገሪቱ ሕዝብ ግን ይህን ፅንፍ የወጣ አካሄድ በፍፁም ሊቀበል አንደማይችል መረዳት አለመቻል ከእኔ አውቅልሃለሁ የቆየ በሽታ የሚመነጭ ነው
መታወቅ ያለበት ቁምነገር ሕገ መንግስቱ የኢህአዴግ ሕገ መንግስት አይደለም ሕገ መንግስቱ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ንብረት ነው ኢህአዴግን በጭፍን መጥላት ይቻላል ዴሞክራሲያዊ መብት ነው ኢህአዴግ ነው ያወጣው በሚል ምክንያት ሕገ መንግስቱን መጥላት ከመጥላትም አልፎ በጉልበት ይቀየር ብሎ መንቀሳቀስን ጊዜው አይፈቅድምⵆ”ጎሰኝነት በህግ ይታገድ” ብለው መንቀስቀስ የጀመሩ ኃይሎች ቆም ብለው ቢያስቡ ይጠቀማሉ አንጂ አይጎዱምⵆ #Ethiopia #Oromia#Constitution

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa