ለወጣቶች...
ለወጣቶች...
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቀጣዩ የኃላፊነት ጊዜያቸው ለወጣቶች #የስራ_እድል_ፈጠራ ልዩ ትኩረት እሰጣለሁ ብለዋል።
ቱሪዝምና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ደግሞ ላቀዱት የስራ እድል ፈጠራ ዋነኛ ሞተር ሆኖ ያገለግላል ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት "ከመጋቢት እስከ መጋቢት የለውጥ መርሃ ግብር" በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ 1ኛ ዓመት የለውጥ ጉዞ በሚሊኒየም አዳራሽ ትናንት በተከበረበት ወቅት ነው።
ዝግጅቱን የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንቶች፣ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ እንዲሁም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ግለሰቦች ታድመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ተቀዛቅዞ የነበረውን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ባለፉት ሰባት ወራት ብቻ በተለያዩ ዘዴዎች 13 ቢሊዮን ዶላር ማሰባሰብ ተችሏል።
በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት በርካታ ባለኃብቶች እቃ ከውጭ ለማስገባት ተቸግረው እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "ችግሩን ለማቃለል ከተሰበሰበው ገንዘብ ውስጥ 8 ቢሊዮን ዶላሩን ለግሉ ዘርፍ አውለናዋል" ብለዋል።
በቀጣይ የኃላፊነት ጊዜያቸውም የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በማጎልበት ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጡም ተናግረዋል።
እቅዳቸውን እውን ለማድረግም ከመላው ህዝብ ጋር በመተባበር ሰላምን እንደሚያሰፍኑም ጠቁመዋል።
የአነስተኛ መስኖ ፕሮጀክቶችን በመጠቀም በገጠር የሚኖሩ ወጣቶችን ወደ አምራችነት ለመቀየር እንደሚሰሩም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።
ቱሪዝም ለስራ እድል ፈጠራ ያለውን አቅም መጠቀምም የቀሪ ኃላፊነት ጊዜያቸው የትኩረት መስክ መሆኑን ገልጸዋል።
ከቱሪዝም የሚገኘውን ገቢ ከፍ ለማድረግ ይረዳ ዘንድም ከመጭው መስከረም ጀምሮ ታላቁ ቤተመንግስት ለጎብኝዎች ክፍት ይሆናል ነው ያሉት።
በቅርቡ ይፋ ከሆነው ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት ውስጥ አንድ አራተኛ የሚሆነው መስከረም 2013 ዓ. ም ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ እንደሚሰራም አክለዋል።
Via ENA

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ