በቻይና መንግሥት የታሰረችውን ኢትዮጵያዊት ጓደኛ

በቻይና መንግሥት የታሰረችውን ኢትዮጵያዊት ጓደኛ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አዋላት

የናዝራዊት አብሮ አደግና የቅርብ ጓደኛዋ እንደሆነች የሚነገርላት ወ/ሪት ሥምረት ካህሳይ በቁጥጥር ሥር የዋለችው፣ ሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2011 ዓ.ም. በፌዴራል ፖሊስ መሆኑ ታውቋል፡፡ ሥምረት በቁጥጥር ሥር የዋለችው ሰለሞን ፀጋዬ ከሚባል ጓደኛዋ ጋር መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ሥምረት ለአብሮ አደጓና ጓደኛዋ መታሰር ምክንያት የሆነችው፣ ከሦስት ወራት በፊት ናዝራዊት ወደ ቻይና ስትሄድ እዚያ ለምታውቃቸው ሰዎች ሻምፖ እንድትሰጥላት በሰጠቻት መያዣ ዕቃ ውስጥ፣ ኮኬን የተባለውን አደንዛዥ ዕፅ በመክተት በመስጠቷ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡
ሥምረት ከጓደኛዋ ጋር አብረው ወደ ቻይና ለመሄድ እየተዘጋጁ ሳሉ የቤተሰብ አባል ሞቶባት መሄድ ባለመቻሏ ከብራዚል የመጣ ሻምፖ እንደሆነ ነግራት፣ ቻይና  ለምታውቋቸው ሰዎች እንድትሰጥላት በመስጠት እሷ ሳትሄድ መቅረቷም ተጠቁሟል፡፡ ናዝራዊት ቻይና ስትደርስ በተደረገ ፍተሻ ኮኬን የተሰኘውን አደንዛዥ ዕፅ ይዛ በመገኘቷ በቁጥጥር ሥር ውላ ክሷን እየተጠባበቀች ነው፡፡

 ድርጊቱን አውቃና ሆን ብላ የፈጸመችው ሳይሆን፣ ጓደኛዋ በፈጠረችው ስህተት መሆኑን ቤተሰቦቿና በርካታ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ መንገዶች ለቻይና መንግሥት ለማሳወቅ እየጣሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካይነት ጉዳዩን ለማጣራ ጥረት እያደረገ መሆኑን፣ ቻይና በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዲፕሎማቶችም እንድትጎበኝ እያደረገ መሆኑን መግለጹም ይታወሳል፡፡
ሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2011 ዓ.ም. የናዝራዊትን ጓደኛ የፌዴራል ፖሊስ ከጓደኛዋ አቶ ሰለሞን ፀጋዬ ጋር በቁጥጥር ሥር ሲያውላቸው፣ በአቶ ሰሎሞን ቤት ከብራዚል ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ወደ ቻይና ለመላክ የተዘጋጀ አደንዛዥ ዕፅ መገኘቱም ተገልጿል፡፡
በመሆኑም በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የተቋቋመ የምርመራ ቡድን ከብራዚል ተነስቶ በኢትዮጵያ ወደ ቻይና ከሚጓጓዘው አደንዛዥ ዕፅ ሽያጭና የሚገኘውን የገንዘብ ዝውውርን ጨምሮ፣ ሌሎች ወንጀሎችንም የማጣራት ሥራ መጀመሩ ተጠቁሟል፡፡ ናዝራዊት በቻይና መንግሥት በተያዘች ወቅት፣ እዚህ ደግሞ ፖሊስ ሳምራዊትን በቁጥጥር ሥር አውሎ በዋስ መልቀቁ ይታወሳል፡፡

Source:Reporter

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman