ኢትዮጵያ እንደ ወትሮው የዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን በስኬት የማስተናገድ ልምዷን አጠናክራ ትቀጥላለች




17ኛው ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
የበርካታ ሀገራት ተወካዮች የሚሳተፉበት ይህ ጉባዔ በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ መካሄዱ የኢትዮጵያን ገፅታ ለመገንባትና ለዲፕሎማሲው መስክ ልዩ ትርጉም አለው።
ኢትዮጵያ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ስሟን ለማጠልሸት ሲጥሩ የነበሩትን አካላት አሳፍራና የተደቀነባትን ፈተና ቀልብሳ ይህንን ዓለምአቀፍ ጉባኤ ማስተናገዷ በፅኑ መሠረት ላይ የቆመ ማንነት ያላት ሀገር ለመሆኗ ማሳያ ነው።
ይህ ጉባኤ በኢትዮጵያ እንዳይካሄድ ከፍተኛ ዘመቻዎች ቢካሄዱም በጠንካራ የዲፕሎማሲ ሥራ እና በበሳል አመራር የኢትዮጵያን የአዘጋጅነት ሚና ለማስጠበቅ እና ጉባኤውንም በስኬት ለማስጀመር ተችሏል።
ኢትዮጵያ ከጊዜያዊ ችግሮች በላይ የሆነች ባለብዙ ተስፋ ሀገር መሆኗን የዓለም አቀፍ ጉባዔው ታዳሚዎች በተጨባጭ የሚመለከቱበት እና የሚመሰክሩበት አጋጣሚንም ይፈጥራል።
የተለያዩ ሀገራት ጠቃሚ ልምዶች የሚቀርቡበት በመሆኑም በኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ላይ ለተሰማሩ አካላት እና ሥራ ፈጣሪዎች ምቹ የልምድ ልውውጥ እና የትስስር መድረክ ነው።
በመሆኑም በዚህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ የሚታደሙትን እንግዶች በተለመደው ኢትዮጵያዊ የእንግዳ አቀባበል ባህል በማስተናገድ ሁሉም ዜጋ የሀገሩ አምባሳደርነቱን ማስመስከር ይጠበቅበታል።
ጉባኤው ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታ ሂደት ለማገዝ የሚያስችል በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለስኬቱ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል።
ኅዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman