ብልጭ ብሎ የደበዘዘ ደስታ!



የፊንፊኔ/አዲስ አበባ ቀላል ባቡር ግንባታ ተጠናቅቆ ስራውን የጀመረው ከዛሬ ሰባት ዓመታት በፊት ነበር፤በወቅቱ የነበረው የባለስለጣናት ሽር ጉድና የህዝቡ ደስታ በአጠቃላይ የነበረው ሁኔታ ትዝ ይለኛል
የባቡሩ መንገድ ተመረቀ በሁለት አቅጣጫዎችም የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ጀመረ ከአያት ጦር ኃይሎችና ከቃሊቲ በመርካቶ ፒያሳ ድረስ በየዕለቱ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ማጓጓዝ ጀመረ ደስ ይላል! በትራንስፖርት ችግር ለእግልት የተዳረጉ የፊንፊኔ/አዲስ አበባ ነዋሪዎች እርካታ በቀላሉ የሚታይ አልነበረም
አሳዛኙና ተስፋ የሚያስቆርጠው ጉዳይ ቀስ በቀስ መጣ አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ባቡሮች የፉርጎ እጥረት አጋጠማቸው ተባለ በሁለቱ መስመሮች አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ባቡሮች ግን ልክ እንደ አዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ ሰው በሰው ላይ ተጠባብቆ እያሳፈሩ ስራቸውን እንዲቀጥሉ ተደረገ
እነርሱም ከጊዜ በኋላ ወገቤን አሉ እየተመናመኑ ሄዱ መለዋወጫ የለም መጠገን አይቻልም ተባለ በጣም ያሳዝናል!እፎይታ ተሰምቶት የነበረው ተሳፋሪ አዘነ አጉረመረመና ዝም አለ
በወቅቱ የነበሩ አመራሮችም እንዲቀየሩ ተደረገ፤በቦታው ብዙ ሰዎች ለአመራርነት መቀያየራቸውን አውቃለሁ ምክንያቱ ለሕዝብ አይነገርም ሚስጢር ሊሆን ይችላል ከሕዝብ ዓይን ሊደበቅ የሚችል ምንም ነገር እንደሌለ ግን ይታወቃል አሁን ባለው ሁኔታ የፊንፊኔ/አዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ተቋም ባለቤት የለውም እየተባለ ነው እከሌ ተረክቦ ያስተዳድረው ሲባል ማን ያጨማለቀውን እኔ እረከባለሁ?ዘወር በል!ተብሏል አሉ
የፊንፊኔ/አዲስ አበባ ነዋሪ አሁንም በትራንስፖርት አገልግሎት እጦት እየተሰቃየ ነው ጠዋትና ምሽት ላይ ብቻ የነበረው የትራንስፖርት ሰልፍ ቀን ላይም እየታየ ነው(አንዱ የቀድሞ ኢህአዴግ ባለስለጣን በአንድ ወቅት ሰው ምን ሆኖ ነው የሚሰለፈው? አለ አሉ) የወቅቱ ባለስልጣን እርሱ ተመችቶት ስለነበር የሰው ችግር ስላለገባው ሊሆን ይችላል እንዲህ ዓይነቱን የፌዝ ንግግር የተናገረው፤
በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ በየወቅቱ የሚመጡ የስራ ኃላፊዎች ችግሩን ተረድተው መስራት የቻሉ አይመስልም፤ዘርፉ ከታች እስከ ላይ በሙስና(ሌብነት) የተጨማለቀ መሆኑ ይነገራል ከአሽከርካሪዎች ጀምሮ በዘርፉ ውሰጥ የሚፈፀመውን ሌብነት የሚያማርሩ እንዳሉ ሰምቻለሁ፤አመታትን እያስቆጠረ ያለው የፊንፊኔ/አዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግር ዘላቂ መፍትሄ ያገኝ ይሆን? ዕድሜ ከሰጠን የምናየው ይሆናል

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa