ካናዳ ለስምምነቱ ተፈጻሚነት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት -ሜላኒ ጆሊ



ጥቅምት 24 ቀን 2015
ካናዳ ለሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን የካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜላኒ ጆሊ ገለጹ።
ትናንት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሓት መካከል የተደረገውን ስምምነት የካናዳ መንግስት እንደሚያደንቅ ገልጸው ስምምነቱ በኢትዮጵያ ሰላም እና ደህንነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ለተደረገው የሰላም ሂደት መሳካት ህብረቱን ጨምሮ በሂደቱ ተሳታፊ ለሆኑ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
ሚኒስትሯ ለሰላም ስምምነቱ መሳካት የካናዳ መንግስት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆኑንም ገልጸዋል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Dh.D.U.O irratti duuluun hin danda’amu!!!