"አለባብሰው ቢያርሱ...." እንዳይሆን!




ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ይፋ ያደረጉት የፀረ ሙስና ዘመቻ(እሳቸው ሌባ ማለት ይሻላል ይላሉ) ከዚህ ጋር የሚያያዘውን ያለፈውን ሁኔታ አስታወሰኝ
በሽወዳና በማስመሰል በተሞላው የኢህአዴግ ዘመንም በተለያዩ ወቅቶች የፀረ ሌብነት ዘመቻዎች ተጀምረው የሚቋረጡበት የሚዳፈኑበት ሁኔታ እንደነበረ አይተን፤ሰምተን ታዘበናል በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ወቅት በሙስናና ብልሹ አሰራሮች ላይ በአገር አቀፍ ደረጃ በባለሙያዎች የተካሄደው ጥናት ለሕዝብ ይፋ ተደርጎ ዝርዝሩን ሰምተን ወይ ጉድ ብለን ነበር
የአሁኑ ዘመቻ በፈራ ተባ እንደማይሆን እንደ ዜጋ ተስፋ አደርጋለሁ በመንግስት በኩል ስራውን የሚመሩ ጠንካራ ሰዎች ያሉበት ኮሚቴ በማቋቋም ቁርጠኝነቱ እንዳለ በይፋ ተረጋግጧል፤የሕዝብ ድጋፍም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይታመናል
በሙሰኞች/ሌቦች ምክንያት ለእንግልት ኑሮ የተጋለጠው የኢትዮጵያ ሕዝብ የመንግስትን ድጋፍና ቁርጠኝነት እንኳን አገኘ እንጂ ሌቦችን አደብ ማስገዛት ያውቅበታል
ለማንኛውም በሙስና ክንዱን ያፈረጠመው ኃይል ራሱን ለማትረፍ መንፈራገጡ የማይቀር ነው ለዚህ ደግሞ የገነባው አቅም ያግዘዋል በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ማለት የሚቻል ቢሆንም “ሆድ ይፍጀው” ብሎ ማለፍ ይሻላል አሁን “ፈረሱም ይኸው ሜዳውም ይኸው” ተብሏልና የመንግስትና ሕዝብ ጠንካራ ቅንጅት በሚያስፈልግበት ወቅት ላይ እንገኛለን፤ሥራው "አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ"ዓይነት ነገር እንዳይሆን ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል! ኢትዮጵያዬ ችግርሽ ብዙ ነው፤ እንደተለመደው ከችግሮችሽ በላይ እንድትሆኚ ፈጣሪ ይርዳሽ!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa