ሰፊውን ሕዝብ ያስደሰተው ለውጥ ከግቡ እንዲደርስ እንሰራለን!
ለውጡ የመጣው ለሁሉም ነው የለውጡ ተጠቃሚ ያልሆነ አንድም ወገን የለም።ሆኖም ለውጡ መጣብን አንጂ
አልመጣልንም ያሉ ቡድኖች በእጅ አዙር ሰላም እንዳይኖር ብርቱ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ እየተስተዋለ ነው።
የለውጡ ተቃዋሚ ቡድኖች መፍጨርጨር በከንቱ መላላጥ ካልሆነ በስተቀር የትም እንደማያደርሳቸው ይታወቃል፤ለውጡ
የእግር እሳት የሆነባቸው ቡድኖች እስከ አሁን በቅጥረኞች ተጠቅመው በተለይም በድንበር አካባቢዎች ህዝቦችን በማጋጨት ጉዳት እንዲደርስ
አድርገዋል።
በምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች፤አንዲሁም በሶማሌ ክልልና በኦሮሚያ የድንበር አካባቢዎችና በተለያዩ
ኪስ ቦታዎች ግጭት ተነስቶ ዜጎች ከመኖሪያ አካባቢዎች አንዲፈናቀሉ ማድረግ የቻሉ ቡድኖች አገርን የመበጥበጥ ዓላማቸው ከግብ መድረስ
አንደማይችል ሊገነዘቡ ይገባል።
የአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ለውጡን ይፈልጉታል ይንከባከቡታልም፤ለውጡ እንዲቀለበስባቸው
አይሹም በህዝቦች እንቢተኝነት የመጣው ተወዳጅ ለውጥ በስፖንሰር ሊቀለበስ እንደማይችልም ሰፊው ህዝብ ለውጡን እየመራ ያለው ኃይል
ከህዝብ ጋር ተቀናጅቶ በቁርጠኝነት እየወሰደ ባለው እርምጃ ብቻ ተገንዝቦ የቡድኖችን መፍጨርጨር በትዝብት በመከታተል ላይ ይገኛል።
ለውጡን አምርሮ የጠላው ቡድን ወደፊት
መረጃ ተሰብስቦ መጠየቄ አይቀርም በሚል እሳቤ የተስፋ መቁረጥ እርምጃ እያስወሰደ አንደሚገኝ መገንዘብ ያስፈጋል፤ዜጎችን ማጋጨትና
መኖሪያ ቤቶች አንዲቃጠሉ ማድረግ ተስፋ በቆረጠ ቡድን የሚፈፀም እኩይ ድርጊት አንደሆነ በግልፅ ይታወቃል
በይቅርታ ተደምረን የአገራችንን ዕድገት በጋራ እናስቀጥል የሚለውን ጥሪ ከምንም ሳይቆጥሩ ገሸሽ
ያደረጉ ቡድኖች ቀናቸው እንደጨለመ ማወቅ ይጠበቅባቸዋል፤ምክንያቱም ህዝብ ተቆጥቷል ከተቆጣ ህዝብ ፊት መቆም አይቻልም!
ለውጡን እየመራ ያለው ኃይል በዚህ
የህዝብ ቁጣ በአግባቡ ሊጠቀም ይገባል፤በእርግጥ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በቅርቡ ግጭቶች ወደ ተከሰቱባቸው አካባቢዎች መርማሪ ቡድን በመላክ ተጠያቂዎችን ለሕግ ለማቅረብ፤ምርመራ በመካሄድ ላይ መሆኑን አስታወቋል።ይህን ማስታወቅ ብቻ በቂ አይሆንም ችግሮቹ በተከሰቱባቸው አካባቢዎች ሲኖሩ የነበሩ ዜጎች ሁኔታዎቹን በአግባቡ እንዲናገሩና
አንዲያጋልጡ ማድረግ ያስፈልጋል፤ለዚህም ምቹ ሁኔታ ሊፈጠር ይገባል።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ትናንት በጽሑፍ ባወጣው መግለጫ እንዳለው የሚካሄደው ምርመራ «ጠንካራ» ነው ብሏል ይህ መልካም ነገር ነው። ጠቅላይ አቃቤ ሕግ « በሕገ ወጥ እና ስርዓተ አልበኝነት እንዲሁም በወንጀል ድርጊቶች የተሳተፉ እና የድርጊቱም ዋነኛ ጠንሳሾች እና ተዋናዮች»ያላቸውን ለሕግ የማቅረቡ ሥራም እየተከናወነ መሆኑን ውጤቱንም ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።ከተፈጠረው አስከፊ ችግር አንፃር ይህ በአስቸኳይ ነው መከናወን ያለበት ዘና የሚያስብል ጊዜ የለም።
ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በመግለጫው በተደራጁ የኢኮኖሚ አሻጥር ሙስናና ሌብነት እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተሳተፉትን ቡድኖችና ግለሰቦች ለሕግ ማቅረብ ተጠናክሮ የሚቀጥል ተግባር መሆኑን አረጋግጧል።
በህግ የሚጠየቁ አካላት ህግ ፊት
መቅረብ አንዲችሉ ህብረተሰቡ የበኩሉን እገዛ ማድረግ ይጠበቅበታል ጉዳዩን የሚከታተለው የመንግስት አካል ስራውን በተረጋጋ ሁኔታ
ማከናወን አንዲችል ጊዜ መስጠትና በማጋለጥ ስራ በብቃት መሳተፍ ያስፈልጋል።
የመንግስት አካላት ህገወጦችን ለህግ
አቅርበው ተጠያቂ ማድረግ የሚችሉት ሁሉም ዜጋ ሲተባበርና ተገቢውን መረጃ በቅነንት መስጠት ሲችል ነው።
የለውጡ አደናቃፊ ቡድን ራሱን ለማትረፍ
እንደለመደው የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ወደፊትም መፍጨርጨሩ አይቀርም፤ከለውጡ ተጠቃሚ የሆነው ወገን ደግሞ በሰከነ ሁኔታና በጥበብ
መንቀሳቀስ ይጠበቅበታል የሞተ ቡድን አልሞትኩም አለሁ ለማለትና ስጋት ለመፍጠር መንቀሳቀሱ የማይቀር መሆኑን በመገንዘብ ሰፊው ህዘብ
የደገፈው ለውጥ ከግቡ እንዲደርስ ሌት ተቀን በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ