በኤፊ ሰውነት
ስለ አገር ግንባታ ስናወራ መቼም ሁላችንም ወደየራሳችን ሁኔታ ጎትተን መውሰዳችን አይቀሬ ነው፡፡ ማንነታችን ቤታችን በሆነ የጋራ ጉዳይ ላይ ደግሞ ሁሌም ቢሆን የተሻለ ማሰብና ያንን ለማሳካት መጣር አንድ የወደፊቱን መተለም የሚችል ዜጋ ስብዕና ነው፡፡ አገር አገር ሆና እንድትቆም የእኔ ሚና ምን ነበር? አሁንስ ሚናዬን እየተወጣሁ ነው ወይ? ወደ ፊትስ ምን ማድረግ አለብኝ የሚል ጤናማ የእለት ተእለት አስተሳሰብ ሁሉም ሰው ቢኖረው የተሻለ አገር የመገንባት እድሉ ሰፊ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም፡፡ ምክንያቱም አገር ሁሉም ሰው በልኩ በሚያውለው ትንሽ የምትመስል አስተዋፅዖ ልክ ይገነባልና፡፡
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ጆን-ኦፍ ኬኔዲ ‘'ሃገሬ ምን አደረገችልኝ ሳይሆን ምን አደረኩላት ብልህ ጠይቅ፡፡'' የሚለውን ተፅእኖ ፈጣሪ ንግግር ይሄን ሃሳብ ለማጠናከር ጥሩ መንደርደሪያ ይሆናል፡፡ በእርግጥ አገር መኩሪያ መጠሪያ ጭምር ነው፡፡ ግን አገር ዜጎቿ ቢደገፉባት፤ ሌሎችም ለመደገፍ ተስፋ ቢያደርጉ ምቾት የምትነሳ ሳይሆን ምቾትን የምታሰፋ አገር መሆን የምትችለው ዜጎቿ ያችን አገር ለመስራት በሚያደርጉት ጥረት ልክ ነው፡፡
በዓለማችን የአገራት እድገት ታሪክ እንደአገር ያለውጣ ውረድ ምቹ በሆነ ሁኔታ ውስጥ አልፎ በሁለንተናዊ መልኩ የገነነ አገር ለመሆነ የበቃ የለም፡፡ በትውልድ ቅብብሎሽ ለአገራቸው በከፈሉት ዋጋ ልክ ነው ዛሬ የዓለማችን ሃብታም አገራት ከራሳቸው አልፈው ሌሎች ለመኖር ተስፋ የሚያደርጓቸው አገር ለመሆን የበቁት፡፡
በአገር ግንባታ ሂደት ውስጥ እያንዳንዱ ግለሰብ የሚወጣው ሚና ተደምሮ ትልቅ አገርን ይፈጥራል፡፡ እኔ ባደርግ ባላደርግ የሚል እሳቤ በአገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ቦታ የለውም፡፡ ይልቁንም የእኔ ትንሽ አስተዋፅዖ ሌሎች ከሚያበረክቱት ትንሽ አስተዋፅዖ ጋር ስትደመር ብዙ ዋጋ አላት የሚል እምነት መያዝ ያስፈልጋል፡፡
ምኞት ያለተግባራዊ እንቅስቃሴ ባዶ ናት፡፡ ሰው የሚመኘውን ማግኘት የሚችለው ለሚመኘው ነገር ተመስጥዖ ሲኖረውና ያንን ለማሳካት ሲጥር ነው፡፡ እኛም እንደ አገር ሰላማዊ ዴሞክራሲያዊና መከባበር የሰፈነባት፤ ሁሉም በፍቅር የሚኖርባት አገር የማየት ፍላጎታችን የሚሳካው እያንዳንዳችን ይህ እውን እንዲሆን በምናበረክተው አስተዋፅዖ ልክ ነው፡፡
አገራችን የብዙ ሺህ ዘመናት ታሪክ ያላት አገር መሆኗ የዓለም እውነታ ነው፡፡ በእነዚህ ዓመታት በትውልድ ጥንካሬ አንዴ ስታንፀባርቅ እንዴ ስትደበዝዝ ዛሬ ላይ ደርሳለች፡፡ የአገራችን የዘመናት ታሪክ ሁሉም አንገት የሚያስደፉ አይደሉም፡፡ ብዙ ቀና ብለን እንደኢትዮጵያዊ በኩራት የምንናገርላቸው ድንቅ ታሪኮች ባለቤት እንድትሆን ያደረጓት ልጆች የነበሯት አገር ናት፡፡ በመልካምም ይሁን በመጥፎ የምናስታውሳቸው የአገራችን የኋላም ይሁን አሁን እየሆኑ ያሉ ሁነቶች ሁሉም ትውልድ በራሱ መንገድ እንዲፈጠሩ ያደረጋቸው ናቸው፡፡
ይህ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ስላለው የአገራችን ሁኔታ ማንሳቱ አገራችንን ወደፊት ማሻገር የሚቻል ስብዕና መላበስ እንድንችል ምን ማድረግ አለብን የሚል ጥያቄ ራሳችንን መጠየቅ እንድንችል ያግዘናል፡፡
አገራችን የሰላም መደፍረስና አለመረጋጋት በተደጋጋሚ እየተስተዋለባት ነው። የዜጎች ህይወት በቀላሉ የሚጠፋበት ሁኔታ አየተስተዋለ የዜጎች ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ የመስራትና ሀብት የማፍራት ህገ መንግስታዊ መብታቸው አደጋ ላይ የወደቀበት ሁኔታ ተከስቷል። አገራችን በሁለንተናዊ መስክ ገና ብዙ መስራት የሚጠበቅብን ተደራራቢ ችግሮች ያሉባት አገር ናት፡፡ ህዝባችን የልማት የሰላም ጥያቄው በአግባቡ እንደሚለስለት ይፈልጋል፡፡ ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት ደግሞ ይሄንን ተግባራዊ ማድረግ የሚችልበትን ሁኔታ ለመፍጠር የተለያዩ ተግባራትን እየከወነ ይገኛል፡፡ ኢህአዴግ መንግስት ሆኖ በመራባቸው ዓመታት የተፈጠሩ ዘርፈ ብዙ ጉድለቶች ተስተካክለው ህዝቡ የሚፈልገውን የለውጥ ሁኔታ ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ ነው፡፡ የጎበጠውን ለማቃናት፣ የተበላሸውን ለማስወገድ መንግስት በሚታትርበት በዚህ የለውጥ ሂደት ውስጥ ደግሞ አሁንም ችግሮች መታየታቸው አላበቃም፡፡ ሰዎች መሞታቸው አላቆመም፡፡ ስደትና መፈናቀልም እንዲሁ፡፡ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ ሙከራዎች አሉ፡፡ እነዚህና መሰል ሁኔታዎች ደግሞ አንቃሳቃሾችም ተንቀሳቃሾችም ኢትዮጵያውያን ነን፡፡
አንዳንዶቻችን ጊዜ ይፍታው በሚል ብሂል በግለሰብ ደረጃ ሚናችንን አሳንሶ በማየት መስራት የሚገባንን ስራ ከመስራት ራሳችንን ቆጥበን እንገኛለን፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ጭራሽ ሰላም ለማደፍረስ ቀን ከሌሊት ሲታትር ይስተዋላል፡፡ ይህ ፅንፍ የያዘ አካል ከለውጥ ሂደቱ ጋር ማስታረቅ ባይቻልም ነገር ግን ቢያንስ ሰላሙን የሚፈልገው አብዛኛው ህዝብ በየአካባቢው ነቅቶ መጠበቅ የሚገባው ይሆናል፡፡ ከሁሉም መንገዶች ሰላማዊ ሁኔታን ተከትሎ መጓዝ የተሻለውና ብቸኛው አማራጭ መሆን ይገባዋል፡፡
ለንግግር ቦታ የሚሰጥ ከፀብ ይልቅ ፍቅርን የሚያስቀድም ትውልድ መሆን እንደሚገባ ከቤት ጀምሮ በየአካባቢው ያለው ወጣት እንዲገነዘበው መሰራት አለበት፡፡ አንድ ሰው አጠገቡ ያለው ሰው ላይ ተፅእኖ መፍጠር ከቻለና ትክክለኛውን የመታገያ መንገድ ማሳየት ከቻለ ሌላውም በዛው ልክ እየሰራ በድምር የግለሰቦች ሚና አገራዊ ለውጥ መምጣት ይችላል፡፡
ሰላም ከእጅ ከወጣ በቀላሉ መመለስ እንደሚቸግር ያለፍንባቸው ሁለትና ሶስት ዓመታት ማሳያዎች ናቸው፡፡ አለፍ ሲል ደግሞ የሌሎች አገራት ተሞክሮን ማየት ግድ ይላል፡፡ ለመረበሽም የማትመች አገር ወደመሆን መሸጋገርም እንዳለ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ አገር አፍርሶ ምን ላይ መቆም ይቻላል፡፡ ለመቃወምም ለመደገፍም ለመመኘትም ነገን ለማየትም አገር ያስፈልጋል፡፡ የአገርን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር እየፈፀሙ ነገ የሚባል ነገር የለም፡፡ ነገ ታሪክ ብቻ ሆኖ ይቀራል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ሰው በሚያደርገው አስተዋፅዖ ልክ አገር እንደ አገር መቆም ትችላለችና ሁሉም ለአገር ሰላም ይትጋ፡፡
መቼም ለእኛ ኢትዮጵያውያን ስለ ሰላም አስፈላጊነት መናገር ጉንጭ ማልፋት ነው የሚሆነው። ሰላማችንን ተነጥቀን ዓመታትን አሳልፈን እናውቃለን፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ዘላቂነት ላለው ልማት ዋስትና ላለው ዴሞክራሲ ከባድ መስዋዕትነት የከፈለበት ሁኔታም የቅርብ ዘመናት ታሪካችን ነው፡፡ በመሆኑም አሁንም እኔ በግሌ ሰላማዊ ሁኔታ እንዲፈጠር ምን አበርክቶት ነበረኝ የሚል ጥያቄ ሁሉም ራሱን መጠየቅ ይገባዋል፡፡ ሰላም፡፡
source:EPRDF Officila

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman