አዲሱ የጀዋር ቃለ መጠይቅ የሴራው ፖለቲካ አንድ አካል!
ጀዋር መሃመድ በመንግስት ውሳኔ ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ ለብዙ ጊዜ ዝምታውን መርጦ እንደቆየ ይታወቃልⵆበማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ጀዋር ለምን ዝም አለ?በሚል ብዙዎች ሲጠያየቁ እንደቆዩና ይህም ከሰዎች እስከ እናቱ ደርሶ እንደ ነበር ጀዋር ገልፆልናልⵆ
በበኩሌ
ጀዋር ዝምታውን መርጦ ‘ዝም’ ማለቱ ከስድስት ወር በላይ ለህዝብም ለራሱም እፎይታ ሰጥቷል የሚል እምነት አለኝ ስለዚህ ጥሩና
ጠቃሚ ውሳኔ ነበር ማለት ይቻላል፤አሁን እፎይታውን ለማደፍረስ ብቅ ተብሏል ይህ ነው ተለሳልሶ የመምጣት እውነቱⵆ
ጀዋር
ከሰሞኑ ኡቡንቱ ለሚባሉ ዩቱበሮች የሰጠው ቃለ መጠይቅ በብዙ ውሸት የተሞላ ነው፤ጀዋር ፊት ለፊት የዋሻቸውን ጥቂት ነጥቦች ብቻ
ለማሳያ ላንሳⵆ
1ኛ
አፌኮ ቅድመ ሁኔታ አስቀመጠ እንጂ ካለፈው ምርጫው ልውጣ ብሎ አልወሰነም፤2ኛ ህወሃት ተገፍቷል የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፤ከዚህ
የበለጠ መዘርዘር አልፈልግም እንጂ ጀዋር በዚህ ቃለ መጠይቅ ብዙ ነገሮችን ሸምጥጦ ዋሽቷል ለምን ይዋሻል?
እርሱ
አባልና አመራር የሆነበት ኦፌኮ የሚባለው ፓርቲ በ6ኛው አገራዊ ምርጫ አልሳተፍም ብሎ የወሰነው በግልፅ አቋም ነው፤ይህ የኦፌኮ
አሳዛኝና በምርጫ አልሳተፍም ውሳኔ የመጣው በሴራ ነውⵆይህም ህወሃትን በመደገፍና ከህዝብ ጠላት ጋር ውግንና በመፍጠር
የመጣ ውሳኔ ነው፤ጉዳዩ ያለፈና የሞተ ነውⵆወደ ኋላ ሄዶ ማንሳት የተፈለገው ኦፌኮ ተገፍቶ ነው በምርጫው
ያልተሳተፈው የሚል ጭቅጭቅ ለመፍጠርና በአመራሮቹ አስር ቦታ መርገጥ ምክንያት እጅግ በጣም የሟሸሸውን የኦፌኮ ተቀባይነት ለማንሰራራት
ታስቦ የመጣ ነጥብ ነውⵆ
ይህ
ሰው “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እጅጉን ተጎድቷል፤ጦርነቱን ማቆም ያስፈልጋል ጦርነቱ ካልቆመ የውጭ ድጋፍ የሚገኝበት ሁኔታ የለም” ብሏል
ይህ ምክረ ሃሳብ ከየት እንደመጣ የማይታወቅ ይመስል በዚህ ጊዜ ይህን ማስረዳት ለምን አስፈለገ?የአገር ኢኮኖሚ እንዲጎዳ ራሱ አቅዶ
ሲሰራ እንደነበር እንዴት ረሳ? የሻሸመኔና አካባቢው ኢኮኖሚ የዳሸቀው በማን ሴራ ነው?
“እንደ
ጀዋር የጦርነቱ አካል መሆን አልፈልግም”ብሏል ወንድማችን እንደ ዜጋ የኢትዮጵያ ዜግነት ካለው(የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወስጃለሁ) ብሏልና
አገሩን ከጠላት የመከላከል ግዴታ እንዳለበት ጀዋር አያውቅም ማለት ነው?የፖለቲካ ምሁር ነኝ ከሚል ሰው እንዴት ሆኖ ነው እንዲህ
ዓይነት ትንታኔ የሚሰጠው?ወያኔ ከውጭ ጠላቶች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ታፍርስ ማለት ነው?ጀዋር የወያኔ ቁንጮዎች በእነ ማን
እየታገዙ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሌት ተቀን እየሰሩ እንዳሉ አያውቅም ማለት ነው?ለምን ይዋሻል?ይህ አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ
አይነት ነገር ነውⵆ
“ሕወሃት
ተገፍቷል”የሚለውን በተመለከተም ጀዋር ዋሽቷል አሸባሪው ቡድን ህወሃት የተገፋበት ሁኔታ የለም!እንደ ሰው ማሰብ ከተቻለ እናቶች
ለእርቅ ወደ መቀሌ ሄደው የቡድኑ ቆንጮዎች እግር ላይ ወድቀው እንባቸውን ያፈሰሱበት ሁኔታ መቼም ቢሆን የሚረሳ አይደለምⵆ
የለውጡ
አመራር “ይቅርታ፤ ፍቅር፤ሰላም፤መደመር እያለ ለበርካታ ጊዜ ሲለምናቸውና ገደብ የለሽ ትዕግስት ሲያሳያቸው የህወሃት ቁንጮዎች ግልፅ
ቅድመ ዝግጅት አድርገው የሰሜን እዝን ያረዱበትና የአገርን ሉአላዊነት የደፈሩበትን ሁኔታ እንዴት መርሳት ይቻላል?
ቀደም
ሲልም ወደ መቀሌ ሄደው ከተደበቁ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ላይ ያደረጓቸው የግድያ ሙከራዎች፤ወታደር አደራጅተው
ወደ ቤተ መንግስት የላኩበት ሁኔታ ለጀዋር ትዝ አይለውም፤ስለዚህ ህወሃት ተገፍቷል ብሎ ያስባልⵆ
አሸባሪው
የህወሃት ቡድን ታሪካዊ ጠላታችን ግብፅና ሌሎች የውጭ አጋዥ ሃይሎችን እገዛ ተመክቶ በእብሪት ኢትዮጵያን ለማፍረስ የአማራና
የአፋር ክልሎችን ከወረራቸው በኋላ የፈፀማቸውን ዘግናኝ ወንጀሎች ጀዋር እስር ቤት ውስጥ ሆኖም ቢሆን አላነበበም?ከሚዲያዎች አልሰማም?
የኢትዮጵያ
መንግስት የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ያለ ምንም ገደብ የሰብአዊ እርዳታ እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል፤አሁን በተለያዩ ቀናት ለህዝቡ የሚያስፈልገው
የሰብአዊ እርዳታ እየቀረበ እንደሆነ በአለም አቀፍ ተቋማት ጭምር እየተነገረ ነውⵆወያኔ ግን የሰብአዊ እርዳታውን ከህዝብ አፍ ነጥቃ ለታጣቂዎቿ
እየሰጠች እንደሆነም እየተነገረ ነው፤ይህን ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ማረጋገጥ አለባቸው
ስለዚህ
ወንድማችን ጀዋር ድንገት በማህበራዊ ሚዲያ ብቅ ብሎ የዘረዘራቸው ጉዳዮች ዋነኛ ምንጭ የተለመደው የሴራ ፖለቲካ ነው፤አጀንዳ ማስቀየሪያ
ነውⵆመንግስት የህግ የበላይነት እንዲከበር የጀመረው አገር አቀፍ እርምጃ ትኩረት እንዳያገኝ በቅንጅት የተሸረበች ሴራ መሆኗን
መገንዘብ ያስፈልጋልⵆእንደ
ፔንዱለም ከሚወዛወዝ ራስን መጠበቅ ያሻል!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ