የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሐረር ከተማ ያካሄደው የፓናል ውይይት ተጠናቀቋል ********************



"ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትሻገራለች" በሚል መሪ ሀሣብ በኢትዮጵያ የጋራ እሴቶች ዙሪያ በሐረር ከተማ የተካሄደው የፓናል ውይይት ተጠናቋል።
የፓናል ውይይቱን የመሩት የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም በማጠቃለያው ላይ እንደተናገሩት፤ በትውልድ ቅብብል ኢትዮጵያን ያስቀጠሉ ጠንካራ የጋራ እሴቶች ሳይንጠባጠቡ በአግባቡ ኢትዮጵያን ለማሻገር ሊውሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመድረኩ ተሳታፊ ለነበሩ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎችና የጋሞ የሠላም አባቶች ባስተላለፉት መልዕክት፤ የጋራ እሴቶቻችንን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ፤ እነዚህን እሴቶች ሊሸረሽሩ የሚችሉ ነገሮችን በማውገዝ ለቀጣዩ ትውልድ የዳበረ እሴትን ማውረስ አለባችሁ ሲሉ አደራ ብለዋል።
በመድረኩ ለተገኙ ተማሪዎችና ታዳጊ ወጣቶች ባስተላለፉት መልዕክትም፤ "ታሪካችሁን እወቁ፤ ታሪካችሁን ካላወቃችሁ ከየት እንደተነሳችሁ ወደየት እንደምትሄዱና የት እንደምትደርሡ ማወቅ አትችሉም" ብለዋል።
አዲሱ ትውልድ ብዝኃነትን አክብሮ ልዩነትን ተቀብሎ አገርን መገንባት ይገባዋል ያሉት አቶ ብናልፍ፤ ልዩነትን ማክበር ያልቻለ ህዝብ እንድ እርምጃ ወደፊት መጓዝ አይችልም ሲሉም ተማሪዎችን አደራ ብለዋል።
በቀድሞው እና በአዲሱ ትውልድ መካከል ሆኖ ኢትዮጵያን የሚያሻግረው የተማረው የህብረተሰብ ክፍል መሆኑን የጠቀሱት አቶ ብናልፍ፤ የአባቶችን እሴት ለአዲሱ ትውልድ በቅንነትና በእውነት ሊያሸጋግሩ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።
ጥሩ አሸጋጋሪ ለመሆን መጀመሪያ የተግባር ሰው መሆን ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ያላችሁን እውቀትና ልምድ ሳትታክቱ በቃልም በጽሁፍም ለቀጣዩ ትውልድ ልታስተላልፉ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
ጽሁፍ አቅራቢው ዶ/ር ወዳጄነህ መሀረነ፤ የእለቱ መድረክ በትክክልም ኢትዮጵያዊያን መነጋገር መደማመጥና መግባባት እንደሚችሉ ያሳዩበት ነው ብለዋል በማጠቃለያ መልዕክታቸው።
በተመሳሳይም ሌላው ጽሁፍ አቅራቢ አቶ ቀለምወርቅ ሚደቅሳ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያዊያን በጋራ እሴቶቻችን መሠረታዊ ልዩነት የሌለን ህዝቦች መሆናችንን እናውቃለን፤ የዛሬው መድረክም ያሳየው ይሄንኑ ነው በማለት፤ ወደፊትም እንደ አገር መመልከት ያለብን የዛሬውን አይነት መልካም ነገሮች ብቻ ሊሆን ይገባል ሲሉ ነው ሃሳባቸውን የቋጩት።
የሐረሪ ክልል ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወልደ አብዶሽም በማጠቃለያቸው፤ እንደ አገር አንድ አድርገው ያቆሙንን የጋራ እሴቶች በጥናትና ምርምር እያስደገፉ ጭምር ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይገባል ብለዋል።
የዛሬው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት መድረክ ሦስተኛው ሲሆን፤ ከዚህ አስቀድሞ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እና በድሬደዋ ከተማ "ስለኢትዮጵያ" የተሰኘ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይና የፓናል ውይይት ማዘጋጀቱ ይታወሳል።

Maddi:Dhaabbata Pireesii Itiyoophiyaa (ኢ.ፕ.ድ)

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman