“አፍንጫ ሲመታ ዓይን ያለቅሳል”

 



“የመንግስት የፀጥታ ኃይሎችኦነግ ሸኔብለው የሰየሙት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትን ለማጥፋት ያቀደናዓሳውን ለማጥመድ ባህሩን ማድረቅበሚል መርህ የሚመራው ዘመቻ ከዓለም እይታ ተደብቆ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖችና የሃገሪቱ ክፍሎች በስፋት እየተካሄደ ይገኛል”ይላል ኦፌኮ ባለፈው እሁድ ሚያዝያ 23 2014 ዓም ያወጣው መግለጫ

ልብ በሉ “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት” የሚባል  ሃይል እንዳለ ኦፌኮ ያውቃል ያምናል፤ስለዚህ የኦፌኮ አባላት በ”ኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት” ውስጥ በመሳተፍ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ተነግሮ የማያልቅ ጉዳት እያደረሱ ነው ማለት ነውምክንያቱም አባላቱ ፓርቲያቸው የሚያምነውንና የሚያንቆጳጰሰውን ሰራዊት መደገፍና ዓላማው ከግብ እንዲደርስ ማድረግ የአባልነት ግዴታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋልና

ሆኖም የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እንደፈረሰ፤ከአራት ዓመታት በፊት ኦነግ ለሰላማዊ ትግል ወደ አገር ገብቶ የሰራዊቱ አባላትም የፈለገ ወደ ቤተሰቡ የተቀረው በፍላጎቱ በኦሮሚያ የፀጥታ አካላት አባል ሆኖ የተቀላቀለ እንደሆነ ቀደም ሲል በአደባባይ ተነግሯል፤ታዲያ ኦፌኮ ብቻ የሚያውቀው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከየት መጣ?

ለነገሩ ትህነግና ኦፌኮ ኦነግ ሸኔ ድባቅ ሲመታ እጅግ በጣም ያማቸዋልትህነግ ሰሞኑን “የኦሮሞን ህዝብ ትግል እደግፋለሁ”በማለት መግለጫ ማውጣቷ የታወቃልኦፌኮም ትህነግን በማጀብ ነው መንግስት ላይ እሪ ሲል መግለጫ ያወጣው

“አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል” ነው ነገሩትህነግና ኦፌኮ ኦነግ ሸኔ ሲመታ ጩኽታቸው ከፍ ይላል፤ምክንያቱም ኦሮሚያን በመበጥበጥ እነርሱ ወደ ስልጣን ኮርቻ እንዲወጡ ሊያደርግ ይችላል ብለው ተስፋ ያደረጉት ኦነግ ሸኔ በመሆኑ ነው

አሁን ተስፋቸው የተማጠጠ ይመስላል ኦፌኮ ኦነግ ሸኔ ላይ እይተካሄደ ያለውን ዘመቻ በመቃወም አለም አቀፍ ገለልተኛ አካል ጉዳዩን እንዲያጣራ እስከ መጠየቅ ደርሷልሸኔ ሲመታ ህዝብ እያለቀ ነው ማለት ምን ማለት ነው?በህዝብ ላይ እንግልት እያደረሰ ያለው ሽፍታ ቡድን አይነካ ማለት ነው?መንግስት የመረጠው ህዝብ በተላላኪ ሽፍታ ሲንገላታ፤ሲገደል፤ሲዘረፍ ዝም ብሎ ማየት አለበት ማለት ነው? ትህነግና ኦፌኮ ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጡትን ምላሽ አያጡም፤ምክንያቱም ሴራውን ሁሉ የሚጎነጉኑት በጋራ ስለሆነ የሚሉት ይታወቃል

የትህነግ እንኳ ቁርጡ ታውቋል ጠላት መሆኑን በተግባር አረጋግጣል፤ኦፌኮ ግን ሁለት ቦታ መቆሙ ይጎዳዋል እንጂ በፍፁም አይጠቅመውምህዝብ ዓይን አለው!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa