ጀዋርን የሚያስናፍቅ ሁኔታ አለ እንዴ?

 



ጀዋር መሃመድ ለውጡ እንዲመጣ ከአራት አመታት በፊት በነበረው ሁሉ አቀፍ ንቅናቄ የበኩሉን ሚና የተጫወተ እንደሆነ ይታመናል፤አስመሳዩና አመባገነኑ የትህነግ/ኢህአዴግ ስርዓት ከነ አብዮታዊ ዴሞክራሲው እንዲንኮታኮት ኢህአዴግ ውስጥ በነበሩ ቁርጠኛ የህዝብ ልጆች የተቀጣጠለው ትግል ከግቡ እንዲደርስ ጀዋር የኦሮሞ ወጣቶችን ቀሬና ቄሮን በማህበራዊ ሚዲያ በማንቃት ረገድ ሊካድ የማይችል ድርሻውን አበርክቷል፤ለዚህ አስተዋፅኦውም በአደባባይ ተመስግኗል

ለውጡ መሬት ረግጦ በሁለት እግሩ እንደቆመ ሲረጋገጥ ሌሎች በርካታ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ታዋቂ ሰዎች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ የለውጡ አመራር ባደረገው ጥሪ መሰረት  ጥሪውን ተቀብለው ወደ አገር ተመለሱ

ጀዋርም ዕድሉን አግኝተው ወደ አገር ከተመለሱ ሰዎች ውስጥ በመጀመሪያ ረድፍ ላይ የሚጠቀስ ነው።ጀዋር ሲራጅ መሃመድ ጥሪውን ተቀብሎ ወደ አገር ቤት ከተመለሰ በኋላ የሆነው ሁሉ የሚታወቅ ስለሆነ መዘርዘሩ ጊዜ የሚወስድና መፅሐፍ ሊወጣው የሚችል ስለሆነ ዘለልኩት

ጀዋር የአሜሪካ ዜግነቱን እንዲቀይር ተደርጎ የኢትዮጵያን የምርጫ ህግ ተቀብሎና አክብሮ ወደ አገር ተመልሶ አሁን የኦፌኮ ፓርቲ አባልና አመራር ነው፤በቅርቡ ደግሞ በመንግስት ውሳኔ መሰረት ይቅርታ ተደርጎላቸው ከእስር ቤት ለመውጣት ዕድሉን ከአገኙ ሰዎች ውስጥ አንዱ መሆን የቻለው ወንድማችን ጀዋር ሲራጅ መሃመድ በነፃነት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

ታዲያ አሁን ባለው ሁኔታ ጀዋርን ለመናፈቅ የሚያስገድድ ነገር ምን ተገኘ?

ይህን ጥያቄ እንድጠይቅ ያስገደደኝ ከሰሞኑ በአገራችን ከተፈጠሩ አሳፋሪ እንቅስቃሴዎቸ ጋር በተያያዘ በአንዳንድ ቦታዎች “ጀዋር ናፈቀን” እያሉ የሚሯሯጡ እጅግ በጣም ጥቂት ወጣቶችን መመልከቴ ነው፤ምንድነው ነገሩ ጀዋር አገር ውስጥ እያለ፤በሰላማዊ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ወደ ውጭ የመውጣት መብቱ ተከብሮለት ወጣ ገባ እያለ በሰላማዊ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ጀዋርን ለመናፈቅ የሚያስገድድ ሁኔታ ምን ተፈጠረ? ፓርቲው ኦፌኮስ ለምን ዝም አለ? ወጣቶች በጀዋር ናፍቆት ተሰቃይተው ሲሯሯጡ ለምን መግለጫ ማውጣት አቃተው? እስኪ በዚህ መንደር ለመፃፍ የምትደፍሩ፤የማትደፍሩም በውስጥ (inbox)ነገሩ የገባችሁ ወገኖች አስረዱኝ፤ጉዳዩ እንደተለመደው የአገር ውስጥ ጠላታችን ከሆነችው ትህነግ ሴራ ጋር የሚያያዝ ከሆነም ማወቁ መልካም ነው፤ያው እንደሚባለው ትንሽ ዕውቀት ጎጂ ናት ብዬ ነው፤ትንሽ ዕውቀት ጤዛ ናት ወዲያውኑ የምትጠፋ።

 

 

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman