የተጋዳላይ ቄሶች ነገር
“አንድ የትግራይ አባት በውጭ የምትገኙ የትግራይ ዳያስፖራዎች የአለም አቀፉ ህብረተሰብ በፋሽስቱ የአብይ አህመድ አስተዳደር ላይ ጫና እንዲፈጥር ጠንክራችሁ መስራት ይጠበቅባችኋል”በማለት መልዕክት ሲያስተላልፉ ስታዩ ወይም ስትሰሙ ምን ይሰማችኋል?
ከአፍ
አውጥታችሁ ምንም ባትገሩም ቄሱ ባስተላለፉት መልዕክት ላይ ትንሽ ማሰባችሁ የሚቀር አይመስለኝም፤ማሰብ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ
ጥያቄዎችን መጠየቃችሁም አይቀርምⵆ
የሃይማኖት
አባት እንዴት እንዲህ ይናገራል?የአንድ አገር ልጆች በአንደኛው ወገን የማን አለብኝነት ችግር ምክንያት ወደ ጦርነት ሲገቡ
የሃይማኖት አባት ሚና ምንድነው?የሚሉና በርካታ ጥየቄዎች እየተግተለተሉ በአዕምሮአችን መመላለሳቸው የሚቀር አይሆንምⵆ
አሁን
የመጨረሻው ሰዓት ሲደርስ ቄሱ እንዲህ ማለታቸውን ሰማን እንጂ በአሸባሪው የህወሃት ቡድን የጦርነት ዝግጅት ወቅትም ተጋዳላይ
ቄሶች ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርጉ በተግባር አይተናልⵆ
ተጋዳላዮቹ
ቄሶች አሸባሪውን ቡድን በመደገፍ የትግራይን ክልል ሃገረ ስብከት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለመገንጠል መወሰናቸውን
ይህንንም በተግባር መፈፀማቸውን ቀደም ሲል በሰጧቸው መግለጫዎች አሳውቀዋልⵆተጋዳላዮቹ ቄሶች ይህን ሲያደርጉ ትክክል አይደለም ያላቸው አካልም ያለ አይመስለኝምⵆ
ተጋዳላይ
ቄሶች አሁን ደግሞ በውጭ አገራት የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ትግላቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ በማስተላለፍ ላይ ናቸውⵆቄሶቹ በዚህ ዓይነት ክላሽ ታጥቀው
ከመዋጋትም ወደኋላ እንደማይሉ አኳሃናቸው ያሳብቃል
ከእንግዲህ
ታላቋ ትግራይ አገር ሆና የምትመሰረትበት ሁኔታ የለም፤እርማችሁን አውጡ ይህን የሚያስብሉ ሁኔታዎች ተፈጥረዋልⵆትግራይ አገራችን ኢትዮጵያ ካሏት ክልሎች ውስጥ አንዷ ናት፤እውነቱ ይህ ብቻ ነው፤አሁን ተወደደም
ተጠላም ትግራይ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ አገር በመሆን የምትቀጥለበት ሁኔታ እንደሌለ፤የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመድፈር መኖር የሚችል
የትኛውም ኃይል እንደሌለ በአሸባሪው የሕወሃት ቡድን ላይ በቁርጠኝነት እየተወሰደ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ሕጋዊ እርምጃ
ተጨባጭ ማስረጃ ነውⵆወደፊት
ተጋዳላይ ቄሶች በፈፀሙት አስነዋሪ ድርጊቶች ላይ የሚሰጡትን አስተያየትና ምላሽ በቅርቡ የምንሰማው ይሆናልⵆየሆነውን ሁሉ ታሪክ መዝግቦ ይዞታልⵆ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ