የዓባይ ወንዝ ድልድይ የግንባታ ሂደቱ በመፍጠን ላይ ነው
በባሕር ዳር ከተማ እየተገነባ የሚገኘው አዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ የግንባታ ሂደቱ በመፍጠን ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ገለጸ።
በቀጣይ 3 ወራት ውስጥ የድልድዩ ዋነኛ አካል የሆነውን ጊርደር ሙሉ ለሙሉ ለመግጠም በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ገልጿል።
ባለስልጣኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ፡የድልድዩን ዋና ዋና ሥራዎች በእቅዱ መሰረት ለማከናወን አጠቃላይ የግንባታ ሂደቱ በመፍጠን ላይ ይገኛል።
ከ760 ሜትር ጊርደር ርዝማኔ ውስጥ በሁለትም መስመር 511 ሚትር የድልድይ ጊርደር ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል።
በግንባታው ፕሮጀክት ላይ በዋነኛነት የድልድይ ተሸካሚ ምሰሶዎች ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል ።
ከመሬት በታች የድልድዩ የቋሚ ተሸካሚ መሰረቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል ።
ለድልድዩ የሚያስፈልጉ 8 ቋሚ ተሸካሚ መሶሶዎች ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቋል።
ድልድዩን ወጥሮ ለመያዝ ከሚያግዙ 72 ስቴይ ኬብልስ 50ዎቹ የተጠናቀቀ ሲሆን የተቀሩትን በቅርብ ለመጨረስ እየተሠራ ነው።
በኢትዮጵያ መንግስት በተመደበ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ በተባለው ተቋራጭ ነው።
የማማከር እና ቁጥጥር ስራውን ደግሞ ቦቴክ ቦስፈረስ ኮንሰልቲንግ ከስታዲያ ኢንጅነሪንግ ጋራ በጣምራ እየሠሩት ይገኛሉ።
አዲሱ የአባይ ወንዝ ድልዲይ በባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ነባሩ የአባይ ወንዝ ድልድይ 2 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው እየተገነባ ያለው።
ይህ ዘመናዊ ድልድይ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ ከሚያበረክተው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ጎን ለጎን ምቹ የሆነ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ያደርጋል።
በተጨማሪም ባሕር ዳር ከተማ ተጨማሪ ውበት እንድትላበስ ይረዳታል።
ድልድዩ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ በግራና በቀኝ በአንድ ጊዜ 6 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ ይችላል፣
5 ሜትር የእግረኛ መንገድ እንዲሁም የብስክሌት ተጠቃሚዎችን መስመር ባካተተ መልኩ ነው እየተገነባ የሚገኘው ፡፡
@ባሕር ዳር፡ መስከረም 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ)
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ