ለዘመናት ህገ መንግስቱን ሲጥስ የኖረ አካል ቡራ ከረዩ ሲል…….

ፊንፊኔ ሚያዝያ 28/2011(ቶለዋቅ ዋሪ) ለዘመናት ህገ መንግስቱን ሲጥስ የኖረ አካል አሁን ህገ መንግስቱ ተጥሶ አደጋ ላይ ነን ከባድ አደጋ ገጥሞናል ብሎ በተደጋጋሚ መግለጫ እየሰጠ የሚያላዝንበት ሁኔታ ነው ያለው
አውራምባ ታይምስ ለእርሱ በሚመች መንገድ ትንሽ ቀንጨብ አድርጎ ተርጉሞ አንደነገረን የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ከሰሞኑ በሰጡት መግለጫ ፌዴራል መንግስት አርሶ አደሮች ላይ ባለው ብድር ምክንያት በጀት እየቆረጠብን ነው በየጊዜው ሁለት ሚሊየን ብር አየቆረጠ ነው ይህ እስከ ሰኔ ከቀጠለ ከባድ ነው ሲሉ ከቢድ ወቀሳ አሰምተዋል
ወቀሳው የትግራይ ሰፊ አርሶ አደር በፌዴራል መንግስት ላይ ጥላቻ ፈጥሮ ለለውጡ አደናቃፊዎች ድጋፍ እንዲያደርግ የተሸረበ ሴራ ነው “እንኳን ይህቺን የዝንብ ጠንጋራ እናውቃለን”
እናማ ለአርሶ አደሮቹ ዋስ ሆኖ ከፌዴራል መንግስት ገንዘብ የተበደረ የክልል መንግስት የትግራይ ክልል መንግስት ብቻ አይመስለኝም
የዶክተር ደብረፅዮን አክሮባት ግን በጣም የሚገርም ሆኖብኛል የፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት በሚገኙበት መድረክ ላይ ቅልስልስ እያሉ መልካም መልካሟን ይናገራሉ በመቀሌ ደግሞ ይፎክራሉ ህገ መንግስቱ ተጣሰ ስብርብር አለ እያሉ ያለቃቅሳሉ ህገ መንግስቱማ አሁን ሳይሆን በአሁን አማካሪዎችዎ የስልጣን ዘመን በሰፊው ሲጣስ ሲሰባበር ኖሯል ለማንኛውም የዶክተርዬ መለስ ቀለስ ባህሪ ለትዝብት ተጋልጧል ምንድነው አንዲህ አቋመ ቢስ መሆን? እርስዎ ተጋዳላይ አይደሉም አንዴ? #Ethiopia #Oromiyaa #TPLF

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman