ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን 120 ነጋዴዎችን በቁጥጥር ሥር አዋለ

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በተያዘው መጋቢት ወር ውስጥ ብቻ 120 ነጋዴዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣኑ  መጋቢት 28 ቀን 2008 ዓ.ም. ከሕዝብ ክንፍ አባላት ጋር ባደረገው ውይይት እንዳስታወቀው፣ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ባካሄደው ዘመቻ 120 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡

ባለሥልጣኑ 85 አምራቾች፣ አስመጪዎችና የጅምላ አከፋፋይ ድርጅቶች ላይ ድንገተኛ ዘመቻ ማድረጉን ገልጾ፣ ከ85 የንግድ ድርጅቶች መካከል 77 የሚሆኑት ያለ ደረሰኝ ግብይት ሲፈጽሙ መገኘታቸውን አስታውቋል፡፡

ይህ በድንገት የተካሄደ ዘመቻ 90 በመቶ የሚሆኑት በሕገወጥ ተግባር ላይ መሰማራታቸውን የሚያሳይ በመሆኑ፣ ድርጊቱ አሳሳቢ እንደሆነ ባለሥልጣኑ አስረድቷል፡


Source:Reporter

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa