አጀንዳ የለሾች አጀንዳ ሲያገኙ
ከሊቢያ
ወደ ጣሊያን በሜዲትራኒያን ባህር ለመሻገር ሲሞክሩ ሰጥመው ከሞቱት
ሰዎች ውስጥ የሶማሊያ የኤርትራና የኢትዮጵያ ዜጎች እንደሚገኙ ሲዘገብ
የቆየ መሆኑ ይታወሳል።
ስደተኞች
በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ውጭ አገራት ሲሰደዱ የቆዩ መሆናቸውም ይታወቃል
የስደት
ችግር በፖለቲካ በኢኮኖሚና በሌሎች በርካታ ምክንያቶች ቀደም ሲልም ነበር ወደፊትም መኖሩ አይቀርም።
ኢትዮጵያዊያን
ብቻ ሳይሆኑ የየትኛውም አገር ዜጎች በስደት ምክንያት በሚያጋጥም አደጋ ምክንያት ህይወታቸው ሲያልፍ ያሳዝናል ሰው፤ሰው ነውና ማንኛውም
ሰው መሞት የለበትም።
በዚህ
አደጋ ክስተትና በሰዎች ሞት ምክንያት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሯሯጡ ከንቱዎች ደግሞ የበለጠ የሳዝናሉ እነዚህ እዚህም እዚያም አሉ።
ለአብነት
ሰሞኑን ከሞቱት ሰዎች ውስጥ አብዛኞቹ ባለፈው ጊዜ በኦሮሚያ ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ ሲሰደዱ የሞቱ ኦሮሞዎች ናቸው በሚል
ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ምን ማለት ነው?
እውነት
ነው ድሮውንም የራሳቸው አጀንዳ የሌላቸውና የትግል አጀንዳ የመፍጠር ብቃቱ የሌላቸው ቱልቱላ ጥቃቅን ቡድኖች የወገኖችን ሞት ለፖለቲካ
ትርፍ ማጋበሻነት ለመጠቀም መሯሯጣቸው የተለመደ ነው።
በዘንድሮው
የኦሮሚያ ተቃውሞ ምክንያት የኦነግን አፍራሽ አላማዎች በማራገብ ተቀባይነት ለማግኘት በመሞከር የሚችለውን ሁሉ ሲያደርግ የቆየው
ጀዋር መሃመድ ጥረቱ ከንቱ ሆኖ ቢቀርበትም መቼም ቢሆን ያገኘውን ቀዳዳ ከመጠቀም ወደ ኋላ እንደማይል በድጋሚ አረጋግጧል።
በባህር
ሰምጠው ከሞቱት ሰዎች ውስጥ ከ200 በላይ የሚሆኑት ከኦሮሚያ የተሰደዱ ሙስሊም ኦሮሞዎች መሆናቸውን በፌስ ቡከ ገፁ ላይ ያተመው
ጀዋር መሃመድ አሁንም በሙስሊም ኦሮሞዎች ደም ለመነገድ እየተመቻቸ መሆኑን በድርጊቱ ይፋ አድርጓል።
ይህ ሰው
ቀደም ሲልም በማህበራዊ ድረ ገፅ ተጠቅሞ ባራገባቸው በርካታ አሉባልታዎች ምክንያት ተነሳስተው በርካቶች ሞተዋል፤የሌሎችም ሰዎች
ህይወት እንዲያልፍ አድርገዋል፤የአገርና የህዝብ ሃብቶችም እንዲወድሙ አድርገዋል፤ጀዋር ግን በሞቀ ቤቱ ተቀምጦ ዘና በማለት የለመደ
ቀልዱን በጥበት አመለካከቱ ለውሶ ቀልዷል።
ስለዚህ
ሰው መፃፍ እንደውም የበለጠ እውቅና እንዲያገኝ ማድረግ ነው ብለው የሚከራከሩ ሰዎች አሉ።እኔ ግን በዚህ አልስማማም ይህ ክፉና ጨካኝ ሰው ሺህ ጊዜ እውቅና ቢያገኝም እኩይ
አካሄድና ድርጊቱን ማጋለጥ ተገቢና አስፈላጊ መሆኑን አምናለሁ።
እናም
ጀዋር መሃመድ ቀጣይ ጨወታውን ለመጫወት እያኮበኮበ መሆኑን እያየሁና
እየሰማሁ ዝም የምልበት ምክንያት አይኖርም ሊኖርም አይገባም።
“የዘፈን
ዳር ዳሩ እስክስታ ነው” እንዲሉ ከሜኒሶታ የተሰባሰቡ ጠባብ ሰዎች ወደ ዋሽንግተን በረዋል።የጎዞአቸውም ምክንያት ያው በተለመደው
ሁኔታ የተቃውሞ ሰልፍ በማካሄድ ወያኔን ማውገዝና ኦህዴድን ማጣጣል ነው።ይህን ዘመቻቸውን የሚቀባበሉ ስለሆነ በመንጫጫትና የተለያዩ
መፈክሮችን በማሰማት መላውን አውሮፓ ያዳርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በእነዚህ
ጀንዳ ቢሶች ጫጫታና መፈክር ተነሳስቶ አገርን እበጠብጣለሁ የሚል ካለ እርሱ ተስፋውን ይቁረጥ።እኛ ኢትዮጵያዊያን በአደጋ ላይ ነን
የድርቁን አደጋ እየተከላከልን እያለን ከደቡብ ሱዳን የመጡ ሰው በላዎች የዜጎቻችንን ህይወት ቀጥፈዋል።የጎርፍ አደጋውም አሳሳቢ
መሆኑ ተተንብዮአል።እናም ይህ ሁሉ አደጋ እያለብን በኢትዮጵያ ጫጫታ ለመፍጠር እሞክራለሁ የምትል ካለህ በራስህ ላይ የፈረድክ መሆንህን
አስቀድመህ ማወቁ አስፈላጊ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ