ልጥፎች

ከኦክቶበር, 2017 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የአሜሪካ፣ ካናዳ፣ ጃፓንና ሜክሲኮ አምባሳደሮች የሕዳሴውን ግድብ ጎበኙ

ምስል
ጥቅምት 21  2010 ዓ.ም(ቶለዋቅ ዋሪ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ፣ ካናዳ፣ ጃፓንና ሜክሲኮ አምበሳደሮች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ጎበኙ። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሀገሪቱ ከሌሎች ሀገራት ጋር ያላትን የኢኮኖሚ ትስስር የሚያሳድግ መሆኑን፥ አምባሳደሮቹ ገልፀዋል። የህዳሴው ግድብ ፕሮጀክት የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ እንዲሁም የተፋሰሱ ሀገራትን ምክንያታዊና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ከግምት ያስገባ መሆኑን አምባሳደሮቹ ከጉብኝቱ በኋላ ተናግረዋል። የአራቱም የበለፀጉ ሀገራት አምባሳደሮች በጉብኝታቸው የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ቁርጠኝነት ሀገሪቱን በቀጠናው የኤሌትሪክ ኃይል ማዕከል ወደ መሆን እያሸጋገራት ነው በማለት አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ለህብረተሰቡ ኑሮ መለወጥ ኤሌክትሪክ ኃይል ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት የገለጹት አምበሳደሮቹ፥ የህዳሴው ግድብ በዚሁ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር ፊሊፕ ቤከር ላለፉት ዓመታት በሀገሪቱ ህዝብ ተሳትፎ እየተገነባ ያለውን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለመጎብኘት ሲመኙ መቆየታቸውንና በጉብኝቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል። የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚደነቅ የምህንድና ጥበብ እና ሀገራዊ ስሜት የሚታይበት መሆኑን የተናገሩት ደግም፥ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምበሳደር ሚካኤል ራይኖር ናቸው። የኃይል ዕጥረት መሰረታዊ የልማት ፈተና መሆኑን የተናገሩት አምባሳደሩ "ግድቡ ሀገሪቷን ከጎረቤት አገሮች ጋር የሚያስተሳር ነው" ሲሉም ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የሜክሲኮ አምባሳደር ቪክቶር ትሬቪኖ፥ የህዳሴ ግድቡ ኃይል ከማመንጨት ባሻገር በአካባቢው ትልቅ የቱሪዝም ማዕከል እንደሚሆን ጠቁመው፥ በቱሪዝም ዘርፍ ሀገራቸው ልምድ ለማካፈልና ለመተባበር

በነቀምቴ ከተማ ተቀስቅሶ ስለነበረው ግጭት የሚወጡት ዘገባዎች እውነታውን የሚያሳዩ አይደሉም- የከተማዋ ፖሊስ

ምስል
ሰሞኑን በነቀምቴ ከተማ ተቀስቅሶ የነበረውን ግጭት በተመለከተ በተለያዩ የማህብራዊ ሚዲያዎች ላይ እየወጡ ያሉ ዘገባዎች እውነታውን የሚያሳዩ አይደሉም አለ የከተማዋ ፖሊስ። በከተማዋ የሚስተዋለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተለቀቁ የሚገኙ መረጃዎች ከእውነታው የራቁ እና ሆነ ተብሎ በአንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በማስመሰል የሚያቀርቡ መሆናቸውን ነው ፖሊስ የገለፀው። የከተማዋ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮማንደር ጌታቸው ይታና በተለይ ለነቀምቴ ፋና ኤፍ ኤፍ ኤም 96 ነጥብ 1 በሰጡት መግለጫ፥ ለግጭቱ መንስኤ ነው የተባለው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በግለሰቦች ቤት ተከማችቶ ተገኘ የሚለው መረጃ መሰረተ ቢስ ነው ብለዋል። እስካሁን ድረስ ከአንደ ፈቃድ ያለው ሽጉጥ ውጭ ተከማችቶ የተገኘ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ የለም ነው ያሉት። ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በተከሰተው ግጭት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉንም ኮማንደር ጌታቸው አረጋግጠዋል። በግጭቱ 10 ሰዎች ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው፥ በከተማዋ በሚገኙ ሁለት ሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ተናግረዋል። አንዳንድ ግለሰቦች ግጭቱን መነሻ በማድረግ የግለሰቦችን ሱቅ እና መጋዘኖች መዝረፋቸውንም ነው የጠቆሙት። ድብቅ አላማቸውን ሊያሳኩ መሰረተ ቢስ በሆነ ወሬ የከተማዋን ህዝብን ሲያሸብሩ እና ሰላም ሲነሱ የተገኙ 16 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርምር እየተደረገባቸው እንደሚገኙ ኮማንደሩ ገልፀዋል። ኮማንደር ጌታቸው እንደተናገሩት በግጭት ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ አምስቱ የኦሮሞ፣ ሶስት ጉራጌዎች እና ሁለት የትግራይ ብሄሮች ተወላጆች ናቸው። ትናንት እና ከትናንተ በፊት የሞቱት ደግሞ አንድ የኦሮሞ እና ሁለት የአማራ ብሄር ተወላጆች

ከአምባሳደር ትአትር ህንፃ ላይ ለሚንደቀደቁ ድምፆች!

አሁን በጣም መረን የለቀቃችሁ መሆናችሁን ኣሳይታችኋል ለከትም እንደሌላችሁ ታውቋል፤ሴትዮዋ ስቱዲዮ የምትገባው ከቃመች በኋላ ይመስላል እርስዋ ቀድማ በምታነሳቸው ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚያወሩ ብሎገር ተብዬዎችም ለበሉበት የሚጮሁ መሆናቸውን እያሳዩ ነው እውነት ነውር ነው! ድፍረት ነው! ባለፈው ሳምንት በተካሄደ ዘለፋዊ ውይይት ላይ ባልና ሚስት በአልጋቸው ላይ ተወያይተው ያፀደቁትን የመወያያ ርዕሰ ጉዳይ ይዘው ስቱዲዮ ገቡ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አመራሮችንም ጥበት ውስጥ የተሸሸጉ ሲሉ ወነጀሉ ሰዎቹ በሚጠብቁት ልክ የማስታወቂያ ገቢ ባይኖራቸውም የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል በጩኸት ላንቃው የሚሰነጠቅበት ድምፅ ገቢ ምንጭ ኪራይ ሰብሳቢዎች እንደሆኑ ግልጽ ነው እነዚህ ሰዎች የሚደመጡበት አካባቢ ውስን በመሆኑ ነው እንጂ እንደፍላጎታቸውማ ቢሆንነ ኖሮ አገር ተቃጥላ ብን ብላለች እግዚአብሔር “እባብን የልቡን አውቆ እግር ነሳው” አለ ያገሬ ሰው

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያካሄደውን ስብሰባ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቀቀ

ምስል
የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያካሄደውን ስብሰባ የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቀቀ። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከጥቅምት 18 እስከ 19 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ የደረሰበት ደረጃ እና ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታን በዝርዝር የገመገመበትን ስብሰባ አካሂዷል። በአሁኑ ወቅት በተወሰኑ የአገሪቱ አካባቢ የተከሰቱ ችግሮችና ግጭቶች ባህሪያቸውና ምክንያታቸው ምን እንደሆነም በዝርዝር ተመልክቷል፡፡ በመስከረም ወር መጀመሪያ በምስራቁ የሀገሪቱ አካባቢ በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱት ግጭቶች በዜጎች ህይወት እና በንብረት ላይ እጅግ ከፍተኛ ጉዳት ከማስከተላቸውም አልፎ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቤት ንብረታቸውና ከኑሮአቸው ተፈናቅለው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ነው የገመገመው። ይህ ድርጊት በምንም መልኩ መከሰት ያልነበረበት እንደሆነ በማንሳት የኪራይ ሰብሳቢነትን ችግሮች መድፈቅ ባለመቻሉ የተፈጠረ እንደሆነ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ለግጭቶቹ መፈጠር ምክንያት የሆኑ የኪራይ ሰብሳቢነት፣ የሙስናና የብልሹ አሰራሮች ከዚህ ጋር ተያይዞ ህገ ወጥነት እንዲስፋፋ እያደረጉ ያሉ የኮንትሮባንድ ትስስሮች በዝርዝር ተፈትሸው በአፋጣኝ እንዲቀረፉ የኢህአዴግ ምክር ቤት በወሰነው መሰረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስቧል። ከእነዚህ ችግሮች ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ህገ ወጥነቶች በምንም መልኩ እንዲቀጥሉ እንደማይፈቅድላቸው እና የህግ የበላይነት መረጋገጥ እንደሚገባ በአፅንኦት አስምሮበታል። ለሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ለመምህራን፣ ለሴቶችና ወጣቶች እንዲሁም ችግሩ በተከሰተባቸው

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ወጣቶች የክልሉን ሰላም እንዲጠብቁ ጥሪ አቀረበ

ምስል
የኦሮሚያ ክልል መንግስት ወጣቶች ከሁከት እና ብጥብጥ አካላት ቅስቀሳ በመራቅ የክልሉን ሰላም እንዲጠብቁ ጥሪ አቀረበ። የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ በአምቦ ከተማ የተከሰተው ግጭት ክልሉን የሁከት አውድማ ማድረግ የሚፈልጉ አካላት ባሰራጩት የሀሰት መረጃ ምክንያት የተፈጠረ ነው ብለዋል። ባለፉት ሁለት ቀናት በአምቦ ከተማ በተፈጠረ ግጭት በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። ከአምቦ ከተማ አስተዳደር ባገኘነው መረጃ መሰረትበግጭቱ ምክንያት የስምንት ሰዎች ህይወት አልፏል። ሶስት ተሽከርካሪዎችም ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ነው የተገለፀው። የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ፥ የክልሉ መንግስት በግጭቱ ምክንያት በደረሰው ሰብኣዊ እና ቁሳዊ ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገልፅዋል። ግጭቱ "ከፊንጫ ወደ አዲስ አበባ ህገ ወጥ ስኳር እየተጓጓዘ ነው” በሚል የሀሰት መረጃ ምክንያት የተፈጠረ ነው ብለዋል። የክልሉ መንግስት ግጭቱን ከመጠንሰስ እስከ መተግበር ድረስ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር አውሎ ለህግ እንድሚያቀርብም አረጋግጠዋል። አቶ አዲሱ ባለፈው ሳምንት በቡኖ በደሌ ዞን የተፈጠረውን ጨምሮ ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በአምቦ ከተማ የታየው ክስተት የኦሮሚያ ክልልን የሁከት እና ነውጥ ማእከል ማድረግ የሚፈልጉ አካላት ያቀነባበሩት ሴራ ውጤት ነው ብለዋል። አዲሱ የክልሉ መንግስት አመራር ከክልሉ ህዝብ ጋር ካደረጋቸው ምክክሮች በመነሳት የኪራይ ሰብሳቢነት መገለጫ በሆነ ሙስና፣ ምዝበራ፣ ህገ ወጥ ንግድ (ኮንትሮባንድ) እና በህገወጥ ገንዘብ ዝውውር ላይ ጠንካራ እርምጃ መወስድ መጀመሩን ሃላፊው ገልፀዋ

የብሮድካስት ባለሥልጣን ሚዲያው አደገኛ አዝማሚያዎች ይታዩበታል አለ

ምስል
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘርዓይ አስገዶም በብሮድካስት ሚዲያው የሚታይ አሳሳቢ ሁኔታ አለ አሉ፡፡  ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን ያሉት በአገሪቱ እየታየ ያሉ ግጭቶችን ሚዲያው የሚዘግብብትን መንገድ በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው፡፡ ሚዲያዎች ጠንካራ ባለመሆናቸው ለማኅበራዊ ሚዲ ያው የተጋለጡ ናቸው ብለው፣ ከግሉም ሆነ ከሕዝብ ሚዲያው የሚታዩ አደገኛ የሆኑ አዝማሚያዎች እየተስተዋሉ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡ ሰሞኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ የተሳሳተ ዘገባ ያቀረቡ የሚዲያ ተቋማትን በሕግ ለመጠየቅ እንቅስቃሴ ይጀመራል ያሉት የግል አስተያየታቸው ነው ያሉት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር፣ አንድ ሚዲያ እንዲህ አይነት ጥፋት ከተገኘበት እንዴት፣ በማንና ምን ይቀጣል የሚለው የሚወሰነው በፍርድ ቤት እንጂ በሌላ የመንግሥት ተቋም አይደለም ብለዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ኢኤንኤን የቴሌቪዥን ጣቢያንና ዛሚ ሬድዮ ጣቢያን የተሳሳተ ዘገባ በማስተላለፍ እንደወቀሷቸው ይታወሳል፡፡

Manni marichaa yaada mooshinii boru dhaggeeffata

ምስል
Onkololeessa 15,2010(Tolawaaq Waarii) Muummichi ministiraa Ob.Hayilamaariyaam Dassaalany kamisa boru mana maree bakka bu'oota ummataatti argamuudhaan mooshinii haasawaa pireezidaant Dr.Mulaatuu Tashooma irratti ejjennoo mootummaa ibsu. Pireezidaantiin Itiyoophiyaa Dr.Mulaatuu Tashooma haasawa miseensoota mana maree bakka bu'oota ummataafi mana maree federeeshiniitiif dhageessisaniin hojiiwwan siyaasaafi hawaas-diinagdee biyya keenyatti bara bajataa haarawaatti hojjetaman irratti akka xiyyeef fatan ni beekama. Dhimma qabiyyee haasawa pireezidaantichaa irratti hooggantoonni paartilee mormitootaa adda addaa yaada sab-quunnamtiilee adda addaa irratti kennaniin haasaan pireezidaantichaa haala qabatamaa biyyattiin irratti argamtu jiddu galeessa kan taasifate miti jechuudhaan qeeqaa akka turan ni beekama Turtiin muummichi ministiraa mana mareetti taasisan sab-quunnamtiileedhaan kallattiidhaan tamsa'a jedhamee eegama.hordofaa.

በኢትዮጵያ 16 በመቶው ህዝብ ጫት እንደሚቅም አንድ ጥናት አመላከተ

ምስል
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሀገሪቱ በሲጋራ፣ አልኮል መጠጦች እና ጫት ሱሶች የተጠመዱ ሰዎች ቁጥር አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን በጥናት ማረጋገጡን ገለፀ። ኢንስቲትዩቱ በ2007 ዓ.ም ከዓለም ጤና ድርጅት፣ ከአዲስ አበባ እና ጂማ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመሆን ባደረገው ጥናት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አጋላጭ ምክንያት እና ስርጭት ተዳሷል። እድሜያቸው ከ15 እስከ 69 የሚደርሱ 9 ሺህ 801 ሰዎች በተካተቱበት ጥናት፥ የተሳታፊዎቹ የደም ግፊት፣ የልብ ምት፣ ቁመት፣ የሰውነት ክብደት እና ሌሎች የጤና ሁኔታዎች ተቃኝተዋል። በዚህም ስር ለሰደዱ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አጋላጭ ናቸው የተባሉ ባህርያት የተለዩ ሲሆን፥ የመጀመሪያው ሲጋራ ማጨስ መሆኑን በኢንስቲትዩቱ የስርዓተ ጤና እና ስነ ተዋልዶ ምርምር ዳይሬክተሩ አቶ አበበ በቀለ ይገልፃሉ። ሌላው በጥናቱ አጋላጭ ባህሪ ነው ተብሎ የተጠቀሰው አልኮል መጠጣት ሲሆን፥ በጥናቱ 41 በመቶው የሀገሪቱ ዜጋ አልኮል እንደሚጠጣ ተረጋገጧል፤ ይሁን እንጂ አሃዙ ከክልል ክልል እንደሚለያይ ነው ዳይሬክተሩ ያነሱት። በሀገሪቱ 16 በመቶው ህዝብ ጫት እንደሚቅም ጥናቱ ያመላከተ ሲሆን፥ ይህ ሀገራዊ አማካዩ ቢሆንም በሀረር 61 በመቶው ህብረተሰብ ጫት ይቅማል። በሌላ በኩል በትግራይ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የጫት ቃሚዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን ጥናቱ ያሳያል ነው ያሉት አቶ አበበ። በዋናነት የሱስ ተጋላጭ የሆነው የህብረተሰብ ክፍል መጨመሩን ያሳየው ጥናቱ መንግስት ሊወስዳቸው የሚገቡ የቤት ስራዎችንም በግልፅ አሳይቷል። በአዲስ አበባ ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የአደንዛዥ እፅ እና አልኮል ሱስ ማገገሚያ ማዕከል ህክምናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ታካሚዎች ሱስ ሲገቡበት ቀላል ቢሆንም ለመው

ሰማያዊ ፓርቲ ሕዝባዊ ስብሰባ ጠራ

ምስል
ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹የአገራችን ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታና የፓርቲያችን ርዕዮተ ዓለም›› በሚል ርዕሰ ጉዳይ፣ በመጪው እሑድ ጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ክበብ አዳራሽ ሕዝባዊ ስብሰባ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ፓርቲው ይህን ያስታወቀው ማክሰኞ ጥቅምት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ዋና ጽሕፈት ቤት፣ ለአገር ውስጥና ለውጭ አገር መገናኛ ብዙኃን ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው፡፡ ሕዝባዊ ስብሰባውን ለማከናወን አስፈላጊውን ሒደት ማሟላታቸውንና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤትም ለሕዝባዊ ስብሰባው ዕውቅና መስጠቱን፣ የፓርቲው ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ አካሉ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ‹‹በዕለቱም ምሁራንንና አንጋፋ ፖለቲከኞችን ጋብዘናል፡፡ ለዚህች አገር በጋራ ተወያይተን ምን ማድረግ ይቻላል የሚለውን ነገር የምናነሳ ሲሆን፣ ሕዝቡም ከሰላማዊ ትግሉ ጎን እንዲቆምና ተስፋ እንዳይቆርጥ፣ እንዲሁም ሕዝቡን ማንቃትና ማደራጀት የሚያስፈልግ በመሆኑ ነው ይህን ስብሰባ የጠራነው፤›› በማለት፣ አጠቃላይ የሕዝባዊ ስብሰባው መንፈስ ምን እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ ‹‹ከሕዝቡ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች በሰፊውና በሚገባ እንወያያለን፡፡ ከሕዝቡ ጋር እንዲህ ባለ መድረክ የምንገናኘው ከስንት ዓመታት በኋላ እንደሆነ ልብ ሊባል ይገባዋል፤›› በማለት፣ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ጋር ለመወያየት መዘጋጀታቸውን አክለዋል፡፡ ፓርቲው አስፈላጊውን ዝግጅትና እንቅስቃሴ ማድረግ የጀመረ መሆኑን ጠቁመው፣ ከረቡዕ ጥቅምት 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ በከተማው የተለያዩ ሥፍራዎች በመኪና በመዘዋወ

Hirmaannaan keessan haacimu!

Hordoftoota fuula kanaa akkam jirtan?Dubbisoonni fuula kanaa biyya Ameerikaafi Itiyoophiyaa keessatti baayi'aan akka jiran hubadheera.Waanan ofiif barreessus ta'e maddawwan adda addaa irraa argadhu isiniif dhiyeessuuf cimeen hojjedha.kanas gochuu akkan danda'uuf dhimmicha sirritti xiinxaluudhaan murteesseera.Isin gama keessaniin  Afaan Oromoo Amaaraafi Ingiliiziitiin waanan gochuu qabuufi gorsa keessan naaf ergaa.Iddoo comment jedhutti afaanota sadeen kanaan kan dandeessaniin jechuukooti,nadhaqqaba,waanan sirreessuu qabuufi waan ida'amuu qabu natti himaa.Barumasaatikaa, teeknooloojii baraatti fayyadamuudhaan beekumsaan walijaarra!Fayyaa ta'aa

ግጭት ተከስቶባቸው የነበረባቸው የቡኖ በደሌ ዞን ሁለት ወረዳዎች ሙሉ በሙሉ ወደ መረጋጋትና ሰላም ተመልሰዋል

ምስል
በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን ሁለት ወረዳዎች ተከስቶ የነበረው ግጭት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ገለፀ። የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ  ትናንት ማምሻውን  በስጡት መግለጫ፥ ግጭቱ ተከስቶባቸው በነበሩ አካባቢዎች የፌደራል ፖሊስና የሃገር መከላከያ ስራዊት መግባታቸውን ተናግረዋል። ባለፉት ሁለት ቀናት በደረሰው ግጭትም የ14 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፥ “መንግስት በድርጊቱ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል፤ ለሟች እና ለተጎጂ ቤተሰቦችም መፅናናትን ይመኛል” ብለዋል። በግጭቱ 1 ሺህ 500 ሰዎች መፈናቀላቸውን የተናገሩት ዶክተር ነገሪ፥ የአካባቢው ህብረተሰብ፣ የፌደራል እና የክልል መንግስታት ድጋፍ እያደረጉላቸው ነው ብለዋል። የሀገሪቱን ህዝቦች አብሮ የመኖር እሴት ለመሸርሸር በሚፈልጉ እና የመንግስት እና የህዝብን ሀብት ሲመዘብሩ በነበሩ አካላት የተቀነባበረ መሆኑን ነው የተናገሩት። የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሃይሎች ግጭቱን ለመቆጣጠር ጥረት ማድረጋቸውን እና በአሁኑ ወቅትም በአካባቢው የፌደራል ፖሊስ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ሁኔታውን ለማረጋጋት በስፍራው እንደሚገኙ ገልፀዋል። የሰው ህይወት ሳይጠፋ እና የንብረት ጉዳት ሳይደርስ ግጭቱን መቆጣጠር ያልተቻለውም የግጭቱ ፈጣሪዎች የተደራጁ ሃይሎች በመሆናቸው ነው ብለዋል ሚኒስትሩ። በአሁኑ ወቅት በደረሰው ጉዳት እጃቸው አለበት በሚል የተጠረጠሩ 43 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን እርምጃው እንደሚቀጥል እና በአሁኑ ወቅት አካባቢው በተሻለ ሰላም ላይ እንደሚገኝ ነው ያነሱት። በግጭቱ የተፈናቀሉ ሰዎችም ንብረታቸውን የአካባቢው ህብረተሰብ እየጠበቀላቸው ሲሆን፥ ወደ መ

ቅንጅቱ ዋጋ እያጣ ነው

ምስል
ENN የተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ ሰሞኑን የቡኖ በደሌን ጉዳይ በዘገበበት ወቅት የተጠቀመበት የቃጠሎ ምስል ከስዊድን የተወሰደ መሆኑን ጠቅሶ ይቅርታ መጠየቁ እየተነገረ ነው በሌላ በኩል ዛሚ ኤፍ ኤምና ሆርን አፌርስ በቅንጅት በመስራት ላይ እንደሚገኙ የሚያመላክቱ ነገሮች ይፋ እየወጡ ነው የዛሚ ባለቤቶች ወይዘሮ ሚሚ ስብሃቱና አቶ ዘሪሁን ተሾመ ትናንት በቀጥታ ስልክ ውይይት በኦሮሚያ ክልል ጉዳይ ላይ አትኩረው ያካሄዱት ውይይት ወዲያኑ በሆርን አፌርስ ድረ ገፅ ላይ መጫኑ ይህንኑ የሚየመለክት ነው ተቋማት ለመልካም ነገር ተቀናጅተው መስራታቸው የሚደገፍ ነው በሴራ የተሸረበ ግንኑነት ግን ለራስም ሆነ ለአገር እንደማይጠቅም ሊታወቅ ይገባል

Qabsoon uummata Oromoo olola diinaatiin booda hin deebi’u

Uummanni Oromoo gaaffii siyaas-dinagdee yeroo dheeraaf gaafataa ture hoggantoonni haaromsaa uummata waliin ta'uun halkaniifi guyyaa kutannoon hojjechaa akka jiran beekamaadha. Kanaaf tokkummaan Oromoo biyya keessaafi alaa akkasitti kan finiinuu eegaleef. Tokkummaan kunimmoo diinota uummaata Oromoo baay’ee naasisee jira.   Ta’us, tokkummaafi sochii uummanni Oromoo kallattii hundaan eegalee jiru k an isaan birrachiise kiraassassabdonniifi kontorobaadonni faayidaa dhuunfaa isaaniif oliifi gad fiiguun carraa jiru hunda fayadamaa akka jiran argaa jirra. Uummata Oromoo sababa daangaan saboota biraa wajjin walitti buusuuf yaalii taasisaan jiran keessa isa tokko. Gama biraatiin Oromiyaa tasgabiifi nageenya dhowwachuun akka wanta hoggantoonni haaromsaa kunneen hanqina qabaniitti fakkeessuudhaan naannoo keenya humna nageenyaa jalatti akka isheen bultu taasisuun deebi’anii mataa olqabachuuf yaalaa jiru. Kunimmoo gonkumaa hin milkaa’uuf.  Tooftaan isaan geggeessaa jiran biroon carraawwa

Wal'aansoo cimaarra jirra,kokkee walqabuudhaan!

ምስል
VIA Addisuu Araggaa Oromiyaa keessatti yeroo ammaa wal’aansoo cimaatu geggeeffamaa jira. Waal’aansoon geggeeffamaa jiru kun wal’aansoo qaama kiraa sassaabdummaadhaan akka silmiitti dhiiga ummataa xuuxaa bara abaraan jiraadha jedhuu fi ummataa fi mootummaa fayyadamummaan haqa qabeessa ta’eef qabsaa'u gidduutti geggeeffamaa jira. - Mootummaan Naannoo Oromiyaa sochii haaromsaa keessatti qabsoo farra kiraa sassaabdummaa ilaalchise waadaa ummata isaatiif gale hojiitti hiikuu eegalee jira. La fa, albuuda, daldala seeraan alaa, naanneessa doolaara seeraan alaa irratti tarkaanfii ciciimaa fudhachuu egalee jira.  - Mootummaan Naannoo Oromiyaa bara bajataa 2009 keessaatti lafa seeraan ala maqaa invatimantiitiin qabamee ture heektaara kuma 70 oli, lafa albuudaa heektaara kuma 15 ol, deebsissuun faayidaa ummataatiif oolchee jira. Daldaltoota seeraan alaa kuma145, ol gara seera qabeessumaatti akka deebi’an taasisee jira. Daldala kontirobaandii hedduu to’annoo jala oolchee j

Ibsa Pirezidantiin MNO obbo Lammaa Magarsaa haala yeroorratti keennan-Kutaa 2ffaa

“Dargaggoofi ummanni Oromoo isa dibbee qabatee dibbee dhawu wajjiin dibbee dhawuun nurra hin jiraatu” P/t Lammaa Magarsaa  Ibsa haala yeroorratti keennan Namni waldhabdee, komii qabaate yoo jiraate bor wal gaafachuu danda’a jaarsummaadhaan, kana keessa dhaabbatanii miti garaa garummaa uumudhaaf kan hojjetamu,har’a miidhamnis yoo jiraate mufiinis yoo jiraate of keessatti qabatanii faayidaa waliiniif tumsuudha kan nama baasu,tokko tokko eessa akka jiru kan hin beekamne anatu kana gaggeessaa jira jedhee daaraasaa hurgufateet injifannoo saamuudhaaf injifannoo itti fakkaatee waan badii ta’aa jiru kana injifannoo itti fakkaatee warra anatu harka keessaa qaba jedhee abalu harka keessaa hin qabu jedhee, warra lallabaa jiruutu jira.Hundi keenya kan barbaannu gaaffiin ummata keenyaa akka deebi’u, mirgi saba Oromoo akka eeggamu hundi keenya kan barbaannu,eenyus haa hojjetu eenyu eenyus haa fidu eenyu eenyus kana keessatti caalmaa haa gumaachu eenyu faayidaan saba kanaa akka inni eegamu

Ibsa Pirezidantiin MNO obbo Lammaa Magarsaa haala yeroorratti keennan-Kutaa 1ffaa

ምስል
“Akka gareetti miti akka nama dhuunfaattuu Oromoo jidduutti garaagarummaa uumuuf kan hojjetu diina ummata Oromooti” Pirezidaati Lammaa Magarsaa. Rakkinoota waliin beeknuf fala dhumaa laachuuf jecha Mootummaan naannoo Oromiyaa hojii guddaa hojjeteera. hojjechaas jira. Keessattuu rakkinoonni furtuu ta’an ummata keenyarra jiran naannoo keessatti jiraniif gara kuteenyaan, hammeenyaafi nuffii tokko malee halkanii guyyaa hojjetaa jira. halkanii guyyaa xaaraa jirra, halkanii guyyaa humna keenyaan waan nama dhadhabsiisu hojjechuurra dabarree arsaa barbaachisaa hanga lubbuutti kan gaafatu yoo ta’ellee kanfallee feedhiifi faayidaa ummata keenyaa eegsiisuuf akka mootummaa naannoo Oromiyaatti gara kuteenyaan hojjetaa jirra.Waan nurraa gaafatu waan nurraa eegamu hundaa kamfallee faayidaa ummata keenyaa eegsisuun nurra jiraata jennee hojjetaa jirra.Kanaaf ammoo ummanni keenya ragaa baha jennee yaanna. -- Hundaa ol tokkummaan ummata keenyaa akka inni cimu ummanni keenya waldhagahee gara

ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል!

ምስል
  ዛሚ ኤፍ ኤም 90.7 ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል የተከሰቱ ሁከቶች እንዲስፋፋ ካደረጉ አካላት ጎን በመሰለፍ እየተንቀሳቀሰ ነውና ከዚህ ድ ር ጊቱ ይቆጠብ ካልሆነ በህግ  ይጠየቃል በሚል የኦሮሚያ ክልል ማሳሰቢያ መስጠቱ  ይታወሳል ዛሬ ማክሰኞ ረፋድ ላይ በተካሄደ የቀጥታ ስልክ ውይይት ጣቢያው በራሱ ያዘጋጃቸውን ሰዎች እያቀረበ እያስጮኸ ነው የሚገርመው የጣቢያው ባለቤቶች ወይዘሮ ሚሚ ስባቱና ባለቤቷ ዘሪሁን ተሾመ ስቱዲዮ ተቀምጠው እየተናገሩ ያሉበት ሁኔታና ቀድመው አዘጋጅተው የሚያወያይዋቸው ሰዎች አስተያየት የእነማን ወገን መሆናቸውን በግልፅ እያሳየን ነው አወያዮቹ ባልና ሚስት እንዲሁም ቀድሞ ተዘጋጅተው ለመወያየት በስልክ የገቡ ሰዎች አሰተያየት አንደምታም ከሰሞኑ ኦሮሚያን ለመበጥበጥ የተያዘው እቅድ በብልህ የኦሮሚያ አመራሮችና በሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ ተሳትፎ በመክሸፉ መቆጨታውን ያመለክታል በዚህ አይነት ሁኔታ መንጫጫት ተጨባጩን እውነታ መቀየር አይችልም! ለኪራይ ሰብሳቢዎች ሽንጥን ገትሮ ቃል አቀባይ መሆን ቢቻልም ከሰፊው ሕዝብ ትክከለኛ ትግል ፊት ለፊት መቆም በፍፁም አይቻልም

በአዳማ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ ከ11 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ተያዘ

ምስል
በአዳማ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ በአንድ ግለሰብ እጅ ሲዘዋወር የነበረ ከ11 ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላር መያዙን ፖሊስ አስታወቀ። የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ ዋና ሳጅን ወርቅነሽ ገልሜቻ እንደገለጹት፥ ገንዘቡ ዛሬ ጧት የተያዘው በአንድ ገልሰብ እጅ በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ነው። ግለሰቡ ማለዳ 2 ሰዓት ከ30 ላይ በአዳማ ከተማ ወረዳ አንድ ቀበሌ 09 ልዩ ስሙ አዳማ ራስ ሆቴል አካባቢ፥ 11 ሺህ 500 የአሜሪካን ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ ሕብረተሰቡ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የሆነው እና ገብረመድህን ይርጋው ገብረጊዮርጊስ የተባለው ይኸው ግለሰብ፥ እጅ ከፍንጅ የተያዘው ገንዘቡን ወደ ቶጎ-ውጫሌ ከተማ ለመጓጓዝ ሲዘጋጅ በነበረበት ወቅት ነው። በአሁኑ ወቅት ግለሰቡን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ማካሄድ መጀመሩንም፥ ዋና ሳጅን ወርቅነሽ ገልሜቻ ገልፀዋል። መንግስት ህገወጦችን ለማጥራት የጀመረው ዘመቻ ከዳር እንዲደርስ ሕብረተሰቡ እያሳየ ያለውን ትብብርና ርብርብ አጠናክሮ እንዲቀጥል፥ ዋና ሳጅን መጠየቃቸውን የኢዜአ ዘገባ ያሳያል።

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ለቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ዢንፒንግ የደስታ መግለጫ ላኩ

ምስል
የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሊቀመንበር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ዋና ፀሃፊ ሆነው በድጋሚ በመመረጣቸው የደስታ መግለጫ ደብዳቤ ላኩ። ከሰሞኑ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ 19ኛውን ድርጅታዊ ጉባኤ በማካሄድ ሺ ዢንፒንግን የፓርቲው ዋና ፀሀፊ አድርጎ ዳግም መርጧል። የፕሬዚዳንት ሺ ድጋሚ መመረጥን እና የ19ኛው የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ መካሄድን አስመልክቶ የደስታ መግለጫ የላኩት አቶ ኃይለማርያም፥ በኢትዮጵያ መንግስትና በድርጅታቸው እንዲሁም በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ለቻይና ህዝብ ሰላምና ብልፅግናን ለተመራጩ የፓርቲው ዋና ፀሃፊ ደግሞ ጤናና መልካም የስራ ዘመንን ተመኝተዋል። በፕሬዝዳንት ሺ ዢንፒንግ አመራር ቻይና ዘርፈ ብዙ አስደናቂ እድገት ማስመዝገቧን ጠቅሰው፥ ሀገሪቱ ለዓለም ብልፅግና እና ሰላም ሚናዋን እየተወጣች መሆኗን በደብዳቤያቸው ገልፀዋል። ቻይና በዓለም አቀፍ መድረኮች የምታቀርባቸውን ዘመናዊ አስተሳሰቦች ኢትዮጵያ ስትደግፍ መቆየቷን የገለፁት የኢህአዴግ ሊቀመንበር አቶ ኃይለማርያም፥ የ19ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ውሳኔዎችም በዓለም ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ የሚያግዙ እንደሚሆኑ እምነታቸውን ተናግረዋል። አቶ ኃይለማርያም እንዳሉት የሁለቱ መሪ ድርጅቶች እና የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መልካም ፍሬዎችን ሲያፈራ ቆይቶ አሁን ላይ ወደ ስትራቴጂያዊ የትብብር አጋርነት አድጓል። ይህ ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች የበለጠ እንዲጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን ለሺ በላኩት ደብዳቤ አረጋግጠዋል።

በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን በሰልፍ ምክንያት ተፈጠሮ የነበረው ሁከት በቁጥጥር ስር ዋለ

ምስል
በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን በሰልፍ ምክንያት ተፈጠሮ የነበረው ሁከት በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታወቁ። ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን ሲደረጉ የነበሩ ሰልፎች ወደ ሁከት እና ብጥብጥ አምርተው በሰዎች ህይወት አካል እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ሃላፊው አስታውሰው። በአሁኑ ወቅት የየወረዳዎቹ ህዝቦች፣ የክልሉ የፀጥታ አካላት እና የሀገር ሽማግሌዎች ባደረጉት ርብርብ ችግሩ ሙሉ በሙሉ ቁጥጥር ስር ውሎ በአካባቢው መረጋጋት ተፈጥሯል ብለዋል። በሁከቱ የተሳተፉ እና በሰው ህይወት አካል እና ንብረት ላይ ጉዳት በማሰድረስ የተጠረጠሩ በርካታ ግለሰቦችም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ገልፀዋል።  የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአካባቢው ዘላቂ መረጋጋት እንዲፈጠር ተመሳሳይ ችግሮች በድጋሚ እንዳይከሰቱ ለማድረግ ጠንክሮ በመስራት እንደሚገኝም አስታውቀዋል። የሁከቱን ተከትሎ ጉዳት እንዳይደርስባቸው በመፍራት ወደ 1 ሺህ 500 የሚጠጉ ዜጎች በጮራ፣ ዴጋ እና በደሌ ከተሞች ተጠልለው እንደሚገኙም ገልፀዋል። ህዝቡም ለእነዚህ ዜጎቻችን ምግብ፣ ውሃ እና አስፈላጊ ድጋፎችን በማድረግ ላይ ይገኛል ያሉት አቶ አዲሱ፥ በአሁኑ ወቅት የሀገር ሽማግሌዎች፣ የጸጥታ አካላት እና የመንግስት አመራሮች ከህዝቡ ጋር በመረባረብ ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ በማድረግ ላይ ይገኛሉ ብለዋል። አቶ አዲሱ አረጋ በትናንትው እለት እንደተናገሩት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፥ ፀረ ሰላም ሀይሎች ሰሞኑን በሁለቱ ወረዳዎች ሲደረግ የነበረዉ ሰልፍ ወደ ሁከት እና ብጥብጥ እንዲያመራ በማድርግ በሰዎች ህይወት፣ አካል እና ንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል። በጮራ እና በዴጋ ወረ

በኦሮሚያና የኢትዮጵያ ሱማሌ ክልሎች መካከል ለተፈጠረው ግጭት ዘላቂ መፍትሔ የሚሰጡ ህዝባዊ ጉባኤዎች ሊካሄዱ ነው

ምስል
በኦሮሚያና የኢትዮጵያ ሱማሌ ክልሎች ለተነሳው ግጭት ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት በአገር ሽማግሌዎችና በሃይማኖት አባቶች የሚመሩ ህዝባዊ ጉባዔዎች እንደሚካሄዱ መንግሥት አስታወቀ። በሁለቱ ክልሎች የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መሪነት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌደራልና የሁለቱ ክልሎች አመራር አባላትና የፀጥታ አካላት የተካፈሉበት የውይይት መድረክ ትናንት ተካሂዷል። ውይይቱን የተከታተሉት የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ እንደገለጹት፥ ግጭቱ ያለበትን ደረጃ የሚያመለክት ሪፖርት በውይይት መድረኩ ላይ ቀርቦ ለጉዳዩ ፈጣንና ዘላቂ እልባት ለመስጠት የሚያስችል አቅጣጫም ተቀምጧል። በዚሁ መሰረት በአገር ሽማግሌዎችና በሃይማኖት አባቶች የሚመሩ የሁለቱም ክልሎች ህዝቦች የሚሳተፉባቸው ህዝባዊ ጉባዔዎች እንዲደረጉ አቅጣጫ መቀመጡንም ነው የገለጹት። የሁለቱም ክልሎች አመራር አባላት ለግጭቱ መንስኤ የሆኑ አካላትን በማጋለጥ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ግጭቱን የሚያባብስና ህዝብን የሚያጋጭ መረጃ በማንኛውም መገናኛ ብዙሃን ሆነ ግለሰብ እንዳይተላለፍ አቅጣጫ መቀመጡን አስታውቀው፤ መመሪያውን ተላልፈው ግጭቱን የብሔር ግጭት አስመስለው የሚያናፍሱ የኮምዩኒኬሽን አካላትና መገናኛ ብዙሃን ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም አመልክተዋል። የሁለቱ ክልሎች ህዝቦች የተቀራረቡና በፍቅር የኖሩ መሆናቸውን ያስታወሱት ሚኒስትሩ፤ "ግጭቱ የህዝቦችንም ሆነ የተገነባውን ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የማይወክል መሆኑ" በውይይቱ መነሳቱንም ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል።