የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል ሲሰነጣጠቅ
ክቡር
ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ባለፈው ሳምንት ለተወካዮች ምክር ቤት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ
ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከክቡር
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሾች ውስጥ ጎላ ብላ የወጣችውና እስከ አሁን እየተግለበለበች ያለችዋ አንድ ቃል መንግስት በተለያዩ የአገሪቱ
ክልሎች ለተፈጠሩ የተለያዩ ችግሮች ‘ይቅርታ’ ስለማለቱ ነው።
መንግስት
ባለፉት አመታት ከመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ አንፃር ባጋጠሙ አስከፊ ችግሮች ላይ በጨዋ ቋንቋ ይቅርታ ማለቱ አስፈላጊና
ተገቢ ነው።
የመንግስት
ይቅርታ መጠየቅ ለመረጠው ሕዝብ ከፍተኛ አክብሮት ያለው መሆኑን እንደሚያመለክትም ልብ ያለው ልብ ይላል።
የይቅርታዋ
ጉዳይ ጠባቦች ትምክህተኞችና ኪራይ ሰብሳቢዎች እዚህም እዚያም ለፈጠሩት ጥፋትና ውድመት መተኪያ ልትሆን አትችልም።እነ እንቶኔዎች
ራሳቸውን ለማሞኘት ካልፈለጉ በስተቀር ለፈፀሙት ጥፋትና ውድመት ተጠያቂነታቸው አይቀርም።
መንግስት
ይቅርታ ጠይቋል በሚል ምክንያት ራስን ከተጠያቂነት ለማሸሽና ሁሉንም ነገር አንተው ቻለው ማለት አያስኬድም።ምክንያቱም የተፈጠሩ
አጋጣሚዎችን በመጠቀም አራት ኪሎ ለመግባት የጎመዡ ሁሉም ፀረ ሰላም ኃይሎች የሚችሉትን ነገር ሁሉ ሲያደርጉ መቆየታቸው በይፋ ይታወቃልና።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ