ሕዳሴ ምንደነው? ለምን አስፈለገ?የዜጋ ግዴታስ?
ሕዳሴ የሚለው ቃል በእንግሊዝኛ “Renaissance”
በሚል የሚታወቀውን የአውሮፓውያን የሽግግር ጊዜ የሚገልፅ
ነው።ሕዳሴ ወይም Renaissance በአውሮፓ የስልጣኔ ሂደት በጣም ወሳኝ የነበረውን ወቅት የሚገልፅ ነው።
ይሁንና የኢትዮጵያ ሕዳሴ ምንን ይገልፃል?
የሀገራችንን የረዥም ጊዜ ታሪክ መለስ ብለን ስንቃኝ በአንድ
ወቅት በስልጣኔ ተጠቃሽ ሕዝቦች የነበራት መሆኑ አሁንም የዚያ ዘመን ትውልዶች ትተውልን ያለፉ በርካታ ቅርሶች የሚያረጋግጡት እውነታ
ነው።ይህን ጉዳይ በተመለከተ የሶስተኛውን ሚሌኒየም መጀመር ምክንያት በማድረግ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ
” ከአንደኛው ሚሌንየም መገባደጃ በኋላ አገራችን ኢትዮጵያ ቀድሞ
የነበራት ዝናና ገናናነት በማሽቆልቆል እንደተተካና በማያቋርጥ የኋልዮሽ ጉዞ ያለፈችበት ምዕራፍ እንደነበር ይታወቃል” ብለው ነበር።
የመካከለኛ ዘመን ታሪካችን በአብዛኛው የሀገርን ዳር ድንበር
የማስጠበቅ የጀግንነት ታሪክ የተመዘገበበት ቢሆንም እንደ አውሮፓዊያኑ የጨለማ ጊዜ (ከ15ኛው እስከ 18ኛው ክፍለ ዘመን) በችግር
የሚታወስ ዘመን ነው።
የአገራችን የስልጣኔ ታሪክ በእርስ በርስ ጦርነት፤በረሃብና በኋላ ቀርነት ተለውጦ አስከፊው አገራዊ ሁኔታ እስክ
20ኛው ክፍለ ዘመን የመጨረሻዎቹ አመታት ቀጥሎ ቆይቷል።የደርግ ስርዓት በሕዝቦች ትግል ከተደመሰሰ በኋላ ግን ስር ሰደው የቆዩትን
ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻችን ስር ነቀል በሆነ መልኩ ለመፍታት የሚያስችል ስርዓት ለመገንባት ሁለንተናዊ እንቅቃሴ ተጀምሮ በሂደት
ላይ ይገኛል።ይህ የለውጥ ትግል በወያኔ (ወያኔ ስድብ አይደለም) የተሃድሶና የህዳሴ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ አበረታች ውጤት በማስመዝገብ
ላይ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ሕዳሴ ስንልም ሀገራችንን ከድህነት በማውጣትና
ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በመገንባት የበለፀገች፤የሕዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጠችና ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር የሰፈነባት ሀገር
እንገነባለን ማለታችን ነው።ያ ገናና ስማችንን መልሰን እንቀዳጃለን ማለታችን ነው።
ሆኖም የሕዳሴ ጎዞአችንን ለማደናቀፍ የሚፈልጉ ኃይሎች ከውስጥና ከውጭ አሰፍስፈዋል።
ለዚህ ተጨባጭ ማሳያ የሚሆነው አገራችን በማስመዝገብ ላይ
ያለችው ልማትና እድገት ሕዝባችንና ዓለም አቀፍ ተቋማት ምስከር ሆነው እያለ ሁሉን ነገር በመካድ ፀረ ሰላምና ፀረ ልማት ኃይሎች
ጥላሸት በመቀባት ላይ ይገኛሉ።
ጎበዝ በአገራችን ጉዳይ ሁላችን ያገባናል ፤
አያገባኝም እያለ ያለው የአገሩ ዜጋም ያገባዋልና ለጉዳዩ አፅንኦት በመስጠት መንቀሳቀስ ይጠበቅበታል።አለበለዚያ ሰላም ሲደፈርስ
ወጥቶ መግባትም ብርቅ ሊሆን ይችላል ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር ሲባል የነበረበትን ወቅት ማስታወስና ወቅቱን ለማያውቁ ወጣቶችም
ጉዳዩን ማስረዳት፤ማስተማር የወቅቱ ዜግነታዊ ግዴታ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ