ፓርላማችን መሳቂያ መሳለቂያ አይደለም



አምስተኛው የኢትዮጵያ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት መደበኛ ስራውን በይፋ የጀመረ መሆኑ ይታወቃል።

የምክር ቤቱ አባላት የመጀመሪያ ቀን ስብሰባ እንደመሆኑ መጠን ክንውኖቹን በንቃት ሲከታተሉ በቀጥታ ስርጭት ማንም መመልከት ችሏል።

ታዲያ የፓርላማውን ክብር ዝቅ ለማድረግ በፌስ ቡክ ላይ ያለው ሩጫና እሽቅድምድም ለምን ይሆን?

በዚህ ማህበራዊ ድረ ገፅ ላይ ከትናንት ጀምሮ  የሚረጨው አሉባልታ ወይ ጉድ ያስብላል።ትንሽ ትልቁ ይህን አሉባልታ እየተቀባበለ ምፀቱን ሲገልፅ አንብበናል።


መቼም ቢሆን ሁሉም የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ደብሮአቸው በአንድ ጊዜ እንቅልፋቸውን አይለጥጡም።

ከአምስት መቶ አርባ ሰባት የምክር ቤቱ አባላት ውስጥ አንድ ወይም ሁለት ሰው በተለያዩ ግላዊ ምክንያቶች ሊያንቃላፋ ይችላል፤ይህ ደግሞ መላውን የፓርላማ አባላት ሊያስወቅስ የሚችል ሳይሆን የግለሰቡን ወይም የግለሰቧን ደካማነት የሚያሳይ ነው።

ታዲያ ክቡር ፓርላማችንን ከወዲሁ ማጣጣልና ለማዋረድ መሯሯጥ መነሻውና መድረሻው ምን እንደሆነ በማወቅ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል።

ፓርላማውን የማጣጣል አጀንዳ ከምንም የመነጨ አይደለም።

ትናንት ምሽት በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የምሽት ዜና ላይ ብቅ ያሉት የሰማያዊ ሊቀመንበር  ይልቃል ጌትነት በሰጡት አስተያየት ምንም የተለየ አዲስ ነገር እንደሌለ ሲናገሩ ተሰምተዋል።

የፌስ ቡክ ዘመቻው መነሻም ከዚህ የሚርቅ አይደለም።በኢትዮጵያ ስኬት የበገኑና የከሰሩ ኃይሎች ገና ብዙ ነገር ይላሉ፤የዋህ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ለጊዜው የተከቷለቸው ይመስላቸውና ኪሳራቸውን የተከናነቡ የጥፋት ኃይሎቹም ደስተኛ ይሆናሉ፤በመጨረሻም ቆሽታቸው ድብን እስኪል ድረስ ዋጋቸውን ያገኙና አርፈው ይቀመጣሉ።

በቅርቡ የሆነውም ይኽው እንደሆነ ማስታወስ ተገቢ ነው፤የ2007 ጠቅላላ ምርጫ ላይ ለጥፋት ኃይሎቹ በህዝብ የተሰጠው ቅጣት ለዚህ ትልቅ ማሳያ ነው።

ማለት የተፈለገው እንኳ ግልፅ ነው ፓርላማው የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች ብቻ የተሰባሰቡበት ስለሆነ ምንም ዋጋ የለውም ለማለት ተፈልጎ ነው ሳይውል ሳያድር ዘመቻ ፌስ ቡክ የተጀመረው።

እና ውድና ክቡር  የፓርላማ አባላትን ለቀቅ በማድረግ የሰላማዊ ትግሉን ተቃውሞ ብቻ ማጠናከር ይሻላቸዋል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman