ቢወቅጡት እምቦጭ” የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ችግር



የአዲስ አበባ ከተማ የትራንፖርት ችግር  አሁንም መፍትሄ አለማግኘቱ በግልፅ እየተስዋለ ነው፤በተለይ ጠዋትና ማታ የሚታዩ ረጃጅም የሕዝብ ሰልፎች ችግሩ አሁንም አሳሳቢ እንደሆነ ማረጋገጫ ናቸው።

ለአመታት የቆየው ይህ ችግር አሁንም ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን ላይ ተገልጋዮች ቅሬታ እንዲያሰሙ ምክንያት ሆኖ እየቀጠለ መሆኑ ግልፅ ነው።


በአዲስ አበባ ትራንስፖርት መስሪያ ቤት በተለያዩ ወቅቶች የተመደቡ ሰዎችም ለችግሩ ምንም አይነት መፍትሄ ማስገኘት ሳይችሉ ከቦታው እንዲነሱ ሲደረግ ቆይቷል።ሞቅ ቀዝቀዝ የሚል የአንድ ሰሞን እርምጃና ቁጥጥራቸውም ባዶ ሆኖ የቀረ ይመስላል።

በትራንስፖርት አገልገሎት ላይ የተሰማሩ አካላትም ይህን ተረድተው ነው መሰል ከምንም እንደማይቆጥሯቸው፤ሰውን በሰው ላይ ቢጭኑም  ምንም የማይሰማቸው ደነዝ ሰዎች መሆናቸው ተረጋግጧል።በመሃል የትራንስፖርት ተጠቃሚ የሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ችግርና ሮሮ በርክቷል።
በቂ የመንገድ ልማት በከተማዋ እየታየ የትራንስፖርት ችግር ይህን ያህል መበራከቱ በፍፁም ተቃባይነት የለውም፤በኢህአዴግ የሚመራው መንግስትም ይህን ጉዳይ በጥሞና ተመልክቶ አስቸኳይ መፍትሄ ሊፈልግለት ይጠበቅበታል።

እውነት ነው የቀላል ባቡር ትራንስፖርት በአንድ አቅጣጫ መጀመሩ የችግሩ መፍትሄ እንደሚሆን የታወቀ ነገር ነው፤ሌሎች ባቡር የማይደርስባቸው አካባቢዎችስ እንዴት ይሆናሉ? ሊታሰብብት ይገባል።በጥቅምት ወር ይጀመራል የተባለው የሁለተኛው መስመር(ከጦር ኃይሎች ሃያት) የቀላል ባቡር ትራንስፖርትስ ለምን ዘገየ?

እረ እየተስተዋለ ሕዝብ ችግር ላይ ነው።በመንግስት ተሽከርካሪ የሚጠቀሙ የመንግስት ባለስልጣናት አዲስ አበባ እየኖሩ ይህን አስከፊ ችግር እየተመለከቱ ዝምታን የመረጡበት ምክንያት ምንድነው?


አሁንማ ከመሸና አንድ ሰዓት ካለፈ የትራንስፖርት አገልግሎት ማገኘት እንደማይቻል እየታየ ነው፤ከተገኘም በታክሲ ከታሪፍ በላይ እጥፍ ከፍሎ መጓዝ ግዴታ እየሆነ መጥቷል።የከተማዋ የትራንሰፖርት ስራ ኃላፊዎች ይህን ያውቃሉ?ወይስ የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ብለው ዝም ብለዋል?ለማንኛውም ማለዳና አመሻሽ ላይ ለገሃር፤አራት ኪሎ፤መገናኛና ሌሎችንም አካባቢዎች መቃኘት ይህን ሃቅ ለመረዳት በቂ ነው።

አንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎትስ ምን እያደረገ ነው?ሰራተኞቹስ በቅንነት እያገለገሉ ነው? ወይስ ሕዝብን እያማረሩ ነው?የድርጅቱ የስራ ኃላፊዎችስ ስለ እውነት እናገለግለዋለን ያሉትን ሕዝብ እያገለገሉ ነው?

በዚህ ፅሑፍ አቅራቢ ትዝብት መሰረት ምንም ነገር ያለ አይመስለም ነገሩ ሁሉ ባዶ ሆኗል።ዝም ተብሏል፤ዝምታው ኢህአዴግ ምርጫን አሸንፏል በቃ ምንም ነገር የለም ማንም የሚነካኝ የለም ዝም ማለት ይሻላልን  አስመስሏል።ዋ!!

ችግሩ አስቸኳይ መፍትሄ የሚፈልግ ነው፤የተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ሲጠየቁ ምክንያት ደርድሮ በማውራት የሰሩ የሚመስላቸው አካላት ካሉ እጅግ በጣም ተሳስተዋል።ዋ!!

ኢህአዴግ የተመረጠው ሕዝቡን ለማገልገል ነው።በኢህአዴግ ሕዝባዊ ድል ተከልሎ ሕዝብ እንዲማረር ማድረግ ከተጠያቂነት በፍፁም አያድንም።ይታሰብበት ዋ!!!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman