አሁንም ጊዜ የለንም



ከአሳፋሪና ቅስም ሰባሪ ድህነታችን ለማምለጥና ተዛምዶን አብሮን የኖረውን ድህነት ከላያች አሽቀንጥረን ለመጣል የተያያዝነው የላቀ ጉዞ ወደ ኃላ እንዳይመለስ ግስጋሴያችን ተጠናክሮ ይቀጥላል።ጉዞአችን ሊቀለበስ የማይችል መሆኑን ከተረዳን ውለን አድረናል፤ሳምንታት ወራትን፤ወራት ደግሞ አመታትን ደራርበው እዚህ አድርሰውናል።


አሁንም ጉዞአችን ወደፊት እንጂ ወደኃላ እንዳይሆን ተጠንቅቀን መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል፤አዎን አስተማማኙ የድህነት ማምለጫ ጉዞአችን እንዳይደናቀፍ ብርቱ ጥንቃቄና ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል።


ዋነኛውን ጠላታችን ድህነትን ጨምሮ ብዙ ጠላቶች አሉን።በኢትዮጵያ ስኬታማ የዕድገት ጉዞ ሁል ጊዜ የሚነጫነጩ ጠላቶች አሉን፤እነዚህም በቅደም ተከተል የሚከተሉት ናቸው።

1.የሻዕቢያ መንግስትና መዋቅሮቹ

2.ሰላማዊ ትግልን ያልፈለጉ ወገኖች

3.በአገር ውስጥ ያሉ መሃል ሰፋሪዎችና አስመሳዮች

4.በኢህአዴግ ውስጥ የተሰገሰጉ ኪራይ ሰብሳቢዎች

5.የውጭ ኃይሎች ናቸው።እነዚህን እንደየቅደም ተከተላቸው በዝርዝር ማየት ያስፈልጋል

የሻዕቢያ ተንኮል

የሻዕቢያ መንግስት መቼም ቢሆን የኢትዮጵያን ሰላምና ልማት ለማየት የማይፈልግ መሆኑን በተግባር ሲያስመሰክሮ ቆይቷል።ሻዕቢያ በ1990ዎቹ ባድመን በኃይል ከወረረና በአይበገሬ የአገራችን ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ጀግና ልጆች ዋጋውን ካገኘ በኃላም አርፎ ሊቀመጥ አልቻለም።

ይህን የተገነዘበውና በኢህአዴግ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት ሻዕቢያ ከእኩይ ተግባሮቹ የማይታቀብ ከሆነ አንድ ቀን ተገቢውን ቅጣት እንደሚያገኝ ተደጋጋሚ መልዕክት አስተላልፏል።በአምስተኛው ዙር የኢትዮጵያ መንግስት ምስረታ ጉባኤ ላይም መልዕክቱ ጎላ ብሎ በመውጣት በክቡር ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ንግግር ተላልፏል።እንግዲህ ልብ ያለው ልብ ይበል ነው ነገሩ።

ሰላማዊ ትግልን ያልፈለጉ ወገኖች

ግንቦት ሰባት እና የአርበኞች ግንባር፤ኦነግ፤ኦብነግና ሌሎች አኩራፊ ቡድኖች የኢትዮጵያ ጠላቶች መሆናቸውን በተለያዩ ጊዜያት በፈፀሟቸው እኩይ ተግባሮች አስመስክረዋል።እነዚህ ቡድኖች አሁንም የአልሞት ባይ ተጋዳይ እንቅስቃሴአቸውን ለመቀጠልና ህልማቸውን ስኬታማ ለማድረግ ከሻዕቢያ ስር ተሸጉጠው የኢትዮጵያን ሰላም ለማደፍረስ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የቻሉትን ነገር ሁሉ አድርገዋል።

የሩቁን ትተን የቅርቡን እንኳ ብናይ የ2007 አጠቃላይ የኢትዮጵያ ምርጫ የተሳካ እንዳይሆን እነዚህ ተስፈኛ ቡድኖች ሻዕቢያ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈፀም መንቃሳቀሳቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በወቅቱ በሰጠው ሰፊ መግለጫ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።

በአገር ውስጥ ያሉ መሃል ሰፋሪዎችና አስመሳዮች

እነዚህ ህጋዊና ህገ ወጥ አካሄድን ደባልቀው በመጓዝ ላይ ያሉ ኃይሎች ናቸው።ለስም ሕገ መንግስቱን አክብረው የሚንቀሳቀሱ ለማስመሰል ኢህአዴግ በህገ መንግስቱ ላይ የተረጋገጡ መብቶችን እየጣሰ ነው፤የፖለቲካ ምህዳሩ ጠቧልና ሌሎች ምክንያቶችን በመደርደር ይከሳሉ።በጎን ደግሞ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ወግነው ሴራቸውን ይሸርባሉ።

በዚህ ረገድ አንዳንድ ታቃዋሚ ፓርቲዎች ባለፉት አመታት አልሳካ አላቸው እንጂ የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ የኢትዮጵያን ሰላም እስከ ወዲያኛው አደፍርሰው የኪራይ ሰብሳቢነት አላማቸውን ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል።እነዚህ ፀረ ልማትና ፀረ ሰላም ኃይሎች አሁንም አርፈው መቀመጥ እንደማይችሉ ይታወቃል።

በ2007 ምርጫ ኪሳራቸውን የተከናነቡት አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ሰላም እንዲደፈርስ ባገኙት ምቹ ሁኔታ ሁሉ ከመጠቀም ወደ ኃላ እንደማይሉ የኋላ ታሪካቸው በግልፅ ያስረዳል።

የራሳቸውን አጀንዳ ቀርፀው መንቀሳቀስ የማይችሉ የአገራችን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚፈጠሩ ክፍተቶችን ማጮህና በዚህም ተከታይ ለማግኘት ጥረት ማድረግ የተለመደ ተግባራቸው ሆኖ ቆይቷል፤ወደፊትም ይህን ከማድረግ ወደኋላ እንደማይሉ ይታወቃል።

በኢህአዴግ ውስጥ የተሰገሰጉ ኪራይ ሰብሳቢዎች

ኢህአዴግ የአባላቱን ቁጥር ለመጨመር ሲል በአንድ ወቅት ስህተት ሰርቷል(ይህ የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ እምነት ነው)፤በተለይ በተሃድሶ ወቅትና ከዚያ ወዲህ በነበረው የአባላት ምልመላ ስራ ግንባሩ የተሳካ ስራ አከናውኗል ማለት አይቻልም።

ይህ ጥንቃቄ የጎደለው አባላትን የማብዛት ስራ ውጤቱ መጥፎ በተግባር መታየት ከጀመረ አመታት እየተቆጠሩ ነው።

የግንበሩን አላማዎችና ምሰሶዎች በሚገባ ደረጃ መረዳት ሳይችሉ ወደ ኢህአዴግ የተቀላቀሉና ከተቀላቀሉ በኃላም መረዳት የማይፈልጉ  ዜጎች የአመለካከት ጥራት ችግር እንዳላቸው ይታወቃል።

ኪራይ ሰብሳቢነት የአመለካከትና የተግባር ችግር ነው።በአጋጣሚ ኢህአዴግን ለመቀላቀል እድል ያገኙ እነዚህ ዜጎች ባገኙት ምቹ  ሁኔታ ሁሉ የሕዝብንና የመንግስትን ገንዘብ ከመዝረፍ በፍፁም ወደኃላ እንደማይሉ በተግባር ተረጋግጧል፤በችግሩ ውስጥ ተዘፍቀው ጉዳያቸው በሕግ እየታየ ያሉ ግለሰቦችም እንዳሉ ይታወቃል።የእነዚህ ሰዎች መፈክር “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል”የሚለው አባባል እንደሆነ ተግባራቸው ይመሰክራል።እነዚህን ከኢትዮጵያ ጠላቶች ለይቶ ማየት አይቻልም አይገባም።

የውጭ ኃይሎች

የውጭ  ሃይሎች ኢትዮጵያ ከድህነት የወጣችና ራሷን የቻለች  አገር እንድትሆን አይፈልጉም።በዚህም ምክንያት በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ አገራችን ኢትዮጵያ እንድትጎዳና በድህነት ውስጥ ስትዳክር እንድትኖር የሚገልጉ በመሆናቸው የተለያዩ ተፅዕኖዎችን ለማድረግ ይሞክራሉ።ለምሳሌ ለኢትዮጵያን የዕድገት ፖሊሲዎች እውቅና ሲሰጡ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም።

የኢትዮጵያ መንግስት የቀረፃቸውን ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች ተግባራዊ እንዳይሆኑ በተወካዮቻቸው አማካይነት በግላጭ ሲቃወሙና ሲከራከሩ ተሰምቷል።ስለዚህ እነዚህም የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላቶች ናቸው።

እነዚህን ጠላቶች መመከት የሚቻለው የጀመርነውን የሰላም የልማትና የዴሞክራሲ ጉዞ አጠናክረን በመቀጠል የኢትዮጵያን ሕዳሴ ስናረጋግጥ ብቻ ነው።ለዚህ ደግሞ አሁንም ጊዜ እንደሌለን በመረዳት ሁሉም በየተሰማራበት የስራ ዘርፍ ውጤታማ ስራ ለማከናወን ብርቱ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል።ከጠላቶቻችን ማምለጥ የምንችለው በጊዜአችን ተጠቅመን ተግተን በመስራት  ውጤታማ መሆን ስንችል ብቻ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman