አቶ ሙክታር ከድር የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ
የጨፌ ኦሮሚያ አምስተኛ የስራ ዘመን አንደኛ አመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በአዳማ ከተማ ዛሬ ተጀምሯል።
ጨፌው በጉባኤው መክፈቻ አቶ ሙክታር ከድርን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ በድጋሚ መርጧል።
የክልሉ ሲቪል ሰርቪስና መልካም አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ እሸቴ ደሴ ደግሞ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሹመዋል።
አቶ ሙክታርን ለርዕሰ መስተዳድርነት ያቀረቡት የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ ሲሆኑ፥ አቶ ሙክታር ከተሃድሶ ወቅት ጀምሮ በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃ ላይ ያገለገሉና ክልሉን ለመምራት ብቃት እንዳለቸው በመግለፅ በድጋሚ እንዲመረጡ መቅረባቸውን ተናግረዋል።
ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙት አቶ ሙክታር፥ በአሜሪካ አገር ከሚገኝ አንድ ዩኒቨርስቲም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን እንዳገኙ ነው አቶ ዳባ የገለጹት።
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ደሞዜ ማሜ አማካኝነት ክልሉን በቅንነት ለማገልገል ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።
አቶ ሙክታር በዚሁ ወቅት በክልሉ መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥና በሁሉም ዘርፍ የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
ህዝቡም በድህነት ላይ የተጀመረውን ትግል አጠናክሮ ከዳር እንዲያደርስ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
ጉባኤው የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ያቀረቡትን የክልሉን መንግስት የካቢኔ አባላት ሹመትን አጽድቋል።
በዚህም መሰረት፡-
1.አቶ እሸቱ ደሴ፦ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስና መልካም አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
2.አቶ ዳባ ደበሌ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመንግስት ተጠሪ
3.አቶ ዘላለም ጀማነህ፦ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርና ቢሮ ኃላፊ
4.አቶ ኡመር ሁሴን፦ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢንዱስትሪና ከተሞች ልማት ቢሮ ኃላፊ
5. አቶ ሰለሞን ኩቹ፦ የአስተዳድርና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ
6.አቶ ሻሎ ዳባ፦ የጤና ቢሮ ኃላፊ
7.ወይዘሮ አዚዛ አብዲ፦ የወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
8. አቶ ፍቃዱ ተሰማ፦ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ
9. ወይዘሮ ሎሚ በዶ፦ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ
10. ወይዘሮ መሃቡባ አደም፦ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ
11.ወይዘሮ ሂሩት ቢራሳ፦ የሴችና ሕፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
12. አቶ ዳኛቸው ሽፈራው፦ የሕብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጄንሲ ኃላፊ
13. አቶ ድሪቡ ጀማል፦ የገጠር መሬትና አካባቢ ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ
14.አቶ ወርዲ ሃሺም፦ የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ
15. አቶ ኤሌማ ቃሜ፦ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ
16.አቶ ጌቱ ወዬሳ፦ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
17. አቶ መርጋ ፈይሳ፦ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
18. አቶ መሃመድ ጅሎ፦ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
19. ዶክተር ሳህሉ ሙሉ፦ የእንስሳትና አሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
20. አቶ ምልኬሳ ጃገማ፦ የጥቃቅንና አነስተኛ ስራዎች ልማት ኤጄንሲ ኃላፊ
21. አቶ አበራ ኦላና የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ኮሚሽነር
22. አቶ ጀማል አባሶ፦ የመንገዶች ባለስልጣን ሀላፊ
23. አቶ ዮሃንስ ድንቃየሁ፦ የገቢዎች ባለስልጣን ሀላፊ
24. አቶ ሙስጠፋ ከድር፦ የትራንስፖርት ባለስልጣን ሀላፊ
25. አቶ ጉታ ላንቾሬ፦ የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ