የተቀበሩ ቦምቦች እንዲመክኑ
እዚህም
እዚያም የተቀበሩ ቦምቦች መኖራቸው በተግባር እየተረጋገጠ መጥቷል።በተለይ በመብራት በውሃና ትራንስፖርት መስሪያ ቤቶች ውስጥ የተቀበሩ ቦምቦች የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአግባቡ እየተወጡ
ነው ማለት ይቻላል።
መንግስት
መልካም አስተዳደርን ከሕዝብ ጋር በመሆን አረጋግጣለሁ ሲል እሪ እያለ ነጋ ጠባ አቋሙን ፍላጎቱንና ቁርጠኝነቱን ይገልጣል፤የተቀበሩት
ቦምቦች ግን ይህን እየሰሙ ተግባራቸውን ያለ ምንም ስጋት እያከናወኑ ነው።
የአሸባሪው
ግንቦት ሰባት ሚዲያ ከውጭ በሚረጨው መርዛማ ፕሮፓንዳው የኢህአዴግ መንግስት ተገዝግዞ እንዲወድቅ የቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው።ኢህአዴግን
በጦርነት ማስወገድ እንደማይቻል የተረዱ የአሸባሪው ቡድን አመራሮች አገር ውስጥ ለሚገኙ ጀሌዎቻቸው ተልዕኮ እየሰጡ ነው።ውስጥ ሆናችሁ
ወያኔን ማዳካም ይቻላል ሲሉም ስልቶቹን ሲዘረዝሩ ተሰምቷል።
መጨናነቅ
በሌለበት ሰዓት ለዚያውም ማለዳ ላይ ዜጋው ቁርሱን አዘጋጅቶ ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት ልኮ ለራሱም ወደ ቀን ውሎው ለመሰማራት
በሚጣደፍበት ሰዓት መብራት በተደጋጋሚ የሚጠፋው ለምንድነው? መስሪያ ቤቱን የሚመሩ አመራሮችስ ይህ ችግር አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ
የአገራችን ክልሎች መኖሩን ያውቃሉ?ወይስ ያው የተለመደ የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ ምክንያታቸውን ይደረድራሉ?
በመብራት
ኃይል መስሪያ ቤት የተለያዩ ቅርንጫፎች የተቀበሩ ቦምቦች እዚያው ተቀብረው በየወሩ ደመወዛቸውን እመየዠረጡ ሕዝብን በማማረር ሕዝብ ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስታችንን
እንዲጠላና እንዲነሳሳ የማድረግ እንዲሁም የጠላትን የሃሰት ፕሮፓጋንዳ
አምኖ እንዲቀበል የማድረግ ተልዕኮአቸውን በትጋት በመወጣት ላይ መሆናቸውን በፍፁም አትጠራጠሩ።
በአዲስ
አበባም ሆነ በክልሎች መንግስት በቂ በጀት መድቦ የተለያዩ የውሃ ፕሮጀክቶች ተሰርተው ለአገልግሎት በቅተዋል፤ነገር ግን የውሃ ዘርፍ
አገልግሎት አሁንም የቅሬታ ምንጭ ሆኖ ቀጥሏል
በተለይ
በጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ እየታየ ያለው ችግር ነዋሪዎች እንዲያጉረምርሙ እያደረገ ነው።እንግዲህ የዘርፉ ሰራተኞችና
መሪዎች ችግሩ በዕድገቱ ምክንያት የተፈጠረ ነው የሚል ተቀባይነት የሌለው ምክንየታችሁን ከአሁን በኃላ ሰምቶ የሚቀበላችሁ እንደሌለ
ማወቃችሁ ጠቃሚ ነው።
በሌላም
በኩል በተጠናከረ ሁኔታ በመቀጠል የቅሬታ ምንጭ የሆነው የትራንስፖርት
ዘርፍ ውስጥም የተቀበሩ ቦንቦች ተልዕኮአቸውን በአግባቡ እየተወጡ ስለመሆናቸው በተጨባጭ ካለው ሁኔታ መረዳት ይቻላል ግን ለምን?
ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው ለምን ሕዝብ እንዲማረር ይደረጋል? የትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች በሚርመሰመሱባት አዲስ አበባ ላይ ሕዝብ
ለምን ተሰልፎ ይውላል?
ቦምቦቹ እነማን ናቸው?
ቦምቦቹ
ግለሰቦች ናቸው በተጠቀሱት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ጥቂት ተራ ሰራተኞች፤ባለሙያዎች ወይም የኃላፊነት ቦታ ይዘው ያሉም
ሊሆኑ ይችላሉ።እነዚህ ቦምቦች በተለያዩ ምክንያቶች በኢህአዴግ ላይ ጥላቻ ፈጥረው ያሉ ለማደር ሲሉ የሚኖሩ፤በአድርባይነት ችግር
የተተበተቡ ናቸው።ሕዝብ ኢህአዴግን ሲያማርር አንጀታቸው ቅቤ ይጠጣል፤በዚህ ምክንይትም ኢህአዴግ ሊወድቅ የቀረበላቸው ይመስላቸውና
ደስ ይላቸዋል፤ሞኞች ናቸው።
ቦምቦቹ
ባገኙት ምቹ ሁኔታ ሁሉ ወያኔ እንዲጠፋ ከመንቀሳቀስ ወደ ኃላ አይሉም።ለዚህ ሁሉ ያጋለጣቸው ደግሞ የኪራይ ሰብሳቢነት፤ትምክህትና
ጠባብነት በሽታ ነው ሁሉም ከእነዚህ ችግሮች የፀዱ ናቸው ማለት አይቻልም።ከእነዚህ ውስጥ ቢያንስ በአንዱ ብቻም ቢሆን በበሽታው
የተጠቁ ከሆኑ ተልዕኮአቸውን ከመወጣት ወደ ኃላ አይሉም።እናም ቦምቦቹ ስራቸውን እየሰሩ ነው።
ይህን መንገድ ለምን መረጡ?
ቦምቦቹ
በተለያዩ ምክንያቶች ኢህአዴግን የሚጠሉ ናቸው ከእነዚህ ምክንያቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቀሱት
- በኢህአዴግ የተሸነፈው የደርግ መንግስት ባላስልጣናት ቤተሰብና ዘር መሆናቸው
- ፅንፈኛ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች የሚነዙትን የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ማመናቸው
- በኢህአዴግ መዋቅር ውስጥ ሆነው በሙስና የተዘፈቁና እንዳይጠየቁ የሚፈልጉ መሆናቸው
- በሽብር ከተፈረጁት ድርጅቶችና ፅንፈኛ ዳያስፖራዎች የሚደረግላቸው የገንዘብ ድጋፍ
- ይመጣል ብለው የሚያስቡት ኃይል የሚሰጣቸው ስልጣን ከፊታቸው እየታየ በተስፈኝነት ይህን ለማድረግ የተገደዱ ናቸው።
አሁን
ቦምቦቹ ተልዕኮአቸውን መወጣት እንዳይችሉ የሚያደርግ ዘመቻ መጀመር አለበት እዚህ እዚያም የተቀበሩት ቦምቦች መምከን አለባቸው።ጎበዝ ዝምታ አያዋጣም ኢህአዴግም ከሕዝብ ጋር ሆኜ የማልፈታው ችግር የለም እያለ ነው፤በውስጡ ያሉ ኪራይ ሰብሳቢዎችም
በስጋት ላይ ናቸው።ፖለቲካና ኮሬንቲን በሩቁ ነው ብሎ ዝም ማለት የትም አያደርስም።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ