የቆሻሻው ፖለቲካ አጀንዳና ጀዋር መሃመድ
ከሰሞኑ ሰንዳፋና አካባቢዋ የሚገኙ አርሶ አደሮች የፊንፊኔ ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ በእኛ ላይ መጣል የለበትም በማለታቸው በየእለቱ ከፊንፊኔ መንደሮች ተሰባስቦ ወደ ሰንዳፋ ተወስዶ ይጣል የነበረው ቆሻሻ አዚሁ ፊንፊኔ ውስጥ ተጠራቅሞ እንዳለ አለ። በቅንነት ለሚያስብ ሰው የአርሶ አደሮቹ እምቢታ ተገቢና ትክክለኛ ነው፤ነገር ግን የሰንዳፋና አካባቢዋ አርሶ አደሮች ለፊንፊኔ ነዋሪዎች ክፉ ተመኝተው፤ፊንፊኔ በቆሻሻዋ ትግማማ፤ብክት ትበል የሚል አቋም እንደማይኖራቸው ይታወቃል በአርሶ አደሮቹ ክልከላ ማንም ቅር ሊሰኝ አይገባም አርሶ አደሮቹ ንፅህናው በተጠበቀ አካባቢ በነፃነት የመኖር ሕገ መንግስታዊ መብት አላቻውና ይህ ሁኔታ ከሰባት ወራት ቆይታ በኋላ የተከሰተ መሆኑ ግን ነገርየው ለፖለቲካ ትርፍ መጠቀሚያነት እየዋለ እንደሆነ ቁልጭ ብሎ ይታያል።የማስተር ፕላኑ ጉዳይ ምላሽ ሲገኝ ሌላ አጀንዳ ተገኘ(በዚህ ጉዳይ ላይ ቀጥሎ የምለው አለኝ) በአንድ ቢሊየን ብር ወጪ ተገነባ የተባለው የቆሻሻ ማስወጋጃ ላንድፊል እንደሚወራለትና ብዙ ገንዘብ ወጪ የተደረገለት መስሎ የማይታይ መሆኑን አካባቢውን ከሚያውቁ ሰዎች ጠይቄ ተረድቻለሁ።ለደረቅ ቆሻሻ ብቻ ታስቦ የተሰራው ላንድፊል የፍሳሽ፤የኬሚካል ነክ ነገሮች፤የቄራ ቅልጥምና ሌሎችም ቅንጥብጣቢዎችና ቅራቅንቦ መጣያ መሆኑ የአካባቢው ንፁህ አየር እንዲበከል ማድረጉ ይነገራል። ይህ ችግር የፊንፊኔም የሰንዳፋም ከባድ ችግር ነው መፍትሄውም የጋራ መሆን አለበት። የአዲስ አበባ መስተዳድርና የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ በመወያየት ላይ እንደሚገኙ እየተነገረ ቢሆንም ሁለቱም በዝምታ ውስጥ መቆየታቸው ተገቢ አይደለም።በጉዳዩ ላይ በቅርቡ ከአዲስ አበባ መስተዳድር ተገኘ በሚል ምንጭ በአንድ ...