5 አዳዲስ መስሪያ ቤቶች በኦሮሚያ ተመሰረቱ
በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልል 5 አዳዲስ
መስሪያ ቤቶች ተመሰረቱ
በተጨማሪም በክልሉ የመንግስት
መስሪያ ቤቶች ላይ የስያሜና የአወቃቀር ማሻሻያም ተደርጓል።
እየተካሄደ ባለው የጨፌ ኦሮሚያ
መደበኛ ስብሰባ አባላቱ፥ የ2008 የጨፌ ፅህፈት ቤት የስራ አፈፃፀምና 5 መስሪያ ቤቶች በአዲስ መልክ እንዲዋቀሩ የቀረበውን ረቂቅ
አዋጅ ተወያይተው አጽድቀዋል።
በአዲስ መልክ የተቋቋሙት መስሪያ
ቤቶች፥ የአካባቢ ጥበቃ ደንና የአየር ንብረት ባለስልጣን፣ የእቅድና ኢኮኖሚ ልማት ኮሚሽን፣ የከተማ መሬት መረጃና ምዝገባ ኤጄንሲ፣
የኢንዱስትሪ ልማትና ማስፋፊያ ኤጄንሲ እንዲሁም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጄንሲ ናቸው።
የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው
ሃይል ልማት ቢሮ፣ የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ፣ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ፣ የቴክኒክና
ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ፣ የአደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽን፣ የከተማ የስራ እድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጄንሲ ደግሞ ስያሜያቸውና
አወቃቀራቸው እንዲሻሻል ተደርጓል።
የጨፌ ኦሮሚያ 4ኛ መደበኛ ስብሳባ
የክልሉን የ2009 በጀት እና የተለያዩ ሹመቶችን በማፅደቅ ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ