የነጥሎ መምታት ዘመቻው ዳር ድንበር

እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል አለች አሉ እንትን። ሕወሃትና ኦህዴድን ነጥሎ ለመምታትና ተቀባይነት ለማሳጣት ሲባል በውስጥና በውጭ የተጀመረው ዘመቻ እንዲቀጣጠል የመፈለግ አዝማሚያ ይታያል እስከ አሁንም  ብዙ ነገር ተደርጎ አይተናል ሰምተናል


ይህ ዘመቻ ሊሳካ ይችላል ብለው የሚያስቡ እንዳሉም መጠራጠር አያስፈልግም እነዚህ ተስፈኞችና ወደ ነፈሰበት ለመንፈስ የሚሹ ናቸውና ለራሳቸውም ሆነ ለሌላው የሚጥቅሙ አይደሉም ከንቱዎች ናቸው

ለማንኛውም የነጥሎ መምታት ስልቱ ውጤታማ ሆኖ እንዲታይ እዚህም እዚያ ማዶም የጠባቦችና ትምክህተኞች ብርቱ ፍላጎት እንዳለ መታወቅ አለበት

ይህ ነጥሎ የመምታት ስልት በሕወሃትና ኦህዴድ ላይ ብቻ የተወሰነ እንዳልሆነም ግንዛቤ ሊያዝ ይገባል ነገርየው ወደ ብአዴን ሰፈርም ጎራ እያለ መሆኑን የሚገባው ይገባዋል ከሰሞኑ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ተከስቶ ያየነውና የሰማነውም ይህን የሚያመለክት ነው ቀደም ሲልም የሕዝብን ጥያቄ ተገን በማድረግ የሆነው ሁሉ ይታወቃል

ኢህአዴግን ለዘመናት ወያኔ እያለ ጆሮው ቁርበት ያክላል ሲል ሲያጥላላ የቆየው ኃይል ይህቺ መላ ከግብ አላደርስ ብላ ስታስቸግር የመጣለት ስልት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችን በየተራ ተቀባይነት ወደማሳጣት ተሸጋግሮ የሚችለውን ያህል እየተፍጨረጨረ ነው

ሕወሃት ስልጣኑን ጠቅልሎ ያዘው፤ጀነራል ኮሎኔሉ ከሕወሃት ነው ኦህዴድ ምንም ድርሻ የለውም የሕወሃት ወላጅ ነው ክልሉን ማስተዳዳር አልቻለም ኦሮሚያ በወታደራዊ አገዛዝ እየተዳደረች ስምንት ወራት ተቆጠሩ ምንትሶ ቅብጥርሶ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ቀጥሏል

በቀጣይ ሰሞኑን ብዙ የተባለለት የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውጤታማ ሲሆን ደግሞ ደኢህዴን ምናባቱ የስምጥ ሸለቆ ውላጅ በማለት ማጥላላቱ እንደሚቀጥል አትጠራጠሩ
ለማንኛውም እኛም አውቀናል ጉድጓል ምሰናል ነው ነገሩ የእኛ ስልት ሕዝባችንን ከጎናችን በማሰለፍ የተጀመረው ልማትና እድገት ለአንድ ቀንም ቢሆን ሳይቋረጥ ቀጣይ እንዲሆን ማድረግ ነው

ልማትና እድገታችን አስተማማኝ ሆኖ ቀጣይነቱ ሲረጋገጥ ሁሉም ነገር ይስተካከላል እስከዚያው በየቀኑ ጥረት ማድረግና መልፋት ተገቢና ወሳኝ ነው እስኪያልፍ ያለፋል ዋነኛው ጠላታችን ደህነት እንደሆነ ለአፍታም መዘንጋ የለብንም


እየተደረገ እንዳለው ልማታችንን እያጧጧፍን ለከት በማጣት ድንበር የሚያልፉትን ኃይሎች እንደአስፈላጊነቱ በሕጋዊ መንገድ ጣታቸውን እየቆረጥን ከሕዝባችን ጋር መቀጥል የምንችልበት ምቹ ሁኔታ ነው ያለው ብሩ ተስፋ አለን The future is bright!!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman