የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ዛሬ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል፤ምስጋናም ቀርቧል

የፈተናውን መጠናቀቅ ምክንያት በማድረግ የትምህርት ሚኒሰቴር መግለጫ ሰጥቷል

ክቡር ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ዛሬ ከሰዓት ጋዜጠኞችን ጠርተው በሰጡት መግለጫ ፈተናው በሰላማዊና በተረጋጋ ሁኔታ መጠናቀቁን አረጋግጠው ለዚህም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሲያበረክቱ ለቆዩ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል
ፈተናው ዳግም ተሰርቆ ሁከት እንዳይፈጠር ከፍተኛ ጥንቃቄ የተደረገ ሲሆን መንግስት ፈተናው ከሚሰጥባቸው ቀናት ቀደም ብሎ ፌስ ቡክን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲቋረጡ በማድረግ ዛሬ ማህበራዊ ሚዲያዎቹ አገልግሎት እንዲሰጡ አድርጓል
ከፍተኛ የአጀንዳ ጥማት ያላቸው አንዳንድ ሃይሎች የመንግስትን ትክከለኛ እርምጃ በማዛባት የሃሰት ፕሮፓጋንዳቸውን ሲነዙበት ሰንብተዋል
አንዳንድ የዋህ ወገኖችም በመንግስት ውሳኔ ቅር መሰኘታቸውን ሲገልፁ የተሰማ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች ግን በሰጡት አስተያየት የመንግስት ውሳኔ ፈተናውን ተረጋግተው እንዲወስዱ ያገዛቸው መሆኑን ሲናገሩ ተሰምቷል
ለማንኛውም የመጀመሪያው ብሄራዊ ፈተና በአልጠግብ ባዮች ተሰርቆ ፀረ ሰላም ኃይሎች እጅ ገብቶ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከነመልሱ እንዲሰራጭ መደረጉ ለዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ ዳርጎን አፏል

ችግሩ ዳግም እንዳይከሰት ፈታኞችን ከመምረጥ ጀምሮ እስከ ማሰማራት ድረስ ከፍተኛ ጥንቃቄ የተደረገ ቢሆንም ጥንቃቄው አስተማማኝ እንዲሆን ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲዘጉ መደረጉ ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman