“አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ” የትህነግ ባዶ ስልት
ሁሉም የትግራይ ህዝብ ህወሀት ነው ብላ በመመፃደቅ የምትታወቀው ትህነግ እስከነ አካቴው የመጥፊያ ጊዜዋን በማፋጠን ላይ ትገኛለች ⵆ ከነሃሴ 18 2014 ዓ.ም ጀምሮ በትዕቢት ተወጥራ በአማራና አፋር ክልል አካባቢዎች ላይ ሶስተኛ ዙር ወረራ ፈፅማለች የአሁኑ ወረራዋ የመጥፊያዋ ጊዜ እጅግ በጣም የቀረበ መሆኑ እርግጥ የሆነበት ነው ፡፡ ትናንትም ሆነ ዛሬ የትህነግ የውጊያ ስልት የታወቀ ነው፡፡ዘመኑ ያለፈበትን የውጊያ ስልት የሕዝብ ማዕበል በመጠቀም አንድን አካባቢ እንደ አንበጣ መውረርና ሳር ቅጠሉን ማውደም ነው፡፡ይህ ኋላቀር የውጊያ ስልት በባህሪው በማዕበል የመጣውን ህዝብ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ በቀላሉ የሚያስፈጅ በመሆኑ ጦርነትን ለማሸነፍ የሚያስችል አይደለም ፡፡ ለ 47 ዓመታት የትግራይን ህዝብ ለጦርነት እሳት እየማገደች የምትገኘው ትህነግ በህይወት ዘመኗ የተካነችበት አንድ ህዝብ የማሸበሪያ ዘዴ አላት፡፡አባሎቿን በለማኝነት፣ በቆራሌነት፣ በተፈናቃይነት …. ስም እያደራጀች ወደ ከተሞችና የገጠር መንደሮች በመላክ ህዝብን ታሳስታለች ታሸብራለች ፡፡ሞራልም፣ ህግም፣ትዝብትም፣ይሉኝታም ስለማይገዛት ያዋጣኛል የምትለውን የሀሰት ወሬ ታሰራጫለች ፡፡በዚህም ተጠቃሚ ሆኗለች፡፡ ከአሁን በኅላ በለመደችው ስልት የመቀጠል ዕድል ግን የላትም አብቅቶላታል ምናልባት ጭቂት ቀናት ብቻ ቀርተው ይሆናል የሶስተኛ ዙር ወረራዋን ከፈፀመች በጥቂት ቀናት ውስጥ ሰላም እንደምትፈልግ በአፈ ቀላጤዋ ጌታቸው ረዳ በኩል ትናንት ለፍፋለች ይህም ለጥቂት ጊዜ ያቀየኝ ይሆናል ብላ የዘየደችው ሊሆን ይችላል ትህነግ ተገለባባጭ ...