ጠ/ሚር ዶክተር ዓብይ አህመድ ከወጣቶች ጋር በተወያዩበት መድረክ ስለዩኒቨርስቲዎች እና ስለ መምህራን:




ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

" የዩኒቨርስቲ መምህራን እናንተም መገንዘብ ያለባችሁ ኢትዮጵያ ደሃ አገር ናት። አሜሪካ እንኳን ዩኒቨርስቲ ተማሪ አስገብታ አትቀልብም።  

ዩኒቨርስቲ ሰው ከደረሰ ራሱን ነው ማስተማር ያለበት እንጂ ለአስተማሪም ደመወዝ ፣ ለተማሪ ቀለብ አይነት ጥያቄ እንደኢትዮጵያ ላሉ ድሃ አገራት ኢኖቬተርስ አይፈጥርም። 

ዩኒቨርሲቲዎች አውቶነመስ ሆነው ራሳቸውን ማስተዳደር አለባቸው። ሃይስኩል ላይ ኢንቨስት ካደረግን እኛ እሱ እንደ በቂ መወሰድ አለበት። 

ዩኒቨርስቲ ሆኖ ገንዘብ አምጥቶ የራሱን ደመወዝ መክፈል የማይችል ከሆነ ኢትዮጵያን ማሳደግ አይችልም ማለት ነው። 

ሃርቫርድ መንግሥትን አይጠይቅም በጀት፣ ኦክስፎርድ አይጠይቅም በጀት፣ ኬንያም ዩጋንዳንም ብትሄድ አይጠይቅም በጀት፣ እዚህ ግን ቀለቡም፣ ደመወዙም ሁሉም ነገር የሚጠየቅ ከሆነ ችግር አለ።

ሁለተኛ የዩኒቨርስቲ መምህር ስታንዳርድ አለው። በሴሚስተር አራት ክሬዲት ሃወር፣ አምስት ክሬዲት ሃወር አስተምረህ የዩኒቨርስቲ መምህር ነኝ አይባልም። ተጋባዥ መምህር ነኝ ነው የሚባለው። ማነው ሙሉ ጊዜ መምህር ለመባል የሚያበቃ ስራ እየሰራ ያለው የሚለውን ማየት አለባችሁ።  ይሄ ብዙ ችግር አለ።

ሁሉም የዩኒቨርስቲ መምህር በርግጠኝነት የምነግራችሁ በቂ ደመወዝ አያገኝም። ደመወዙ ያንሳል ፣ ኑሮው ዝቅተኛ ነው ትክክል ነው። መቀየር አለበት። ነገር ግን ኢትዮጵያንም ማሰብ ጥሩ ነው። እዳ ተጭኖን፣ ዋጋ ግሽበት ሊገድለን፣ ጦርነት እያለብን፣ የዓለም ተጽዕኖ በዝቶብን ፕሮጀክቶች እዚህም፣ እዚያም፣ እዚያም ጥደን እያረሩብን፣ አያዋጣም ! 

የከፋው ደግሞ የዩኒቨርስቲ መምህር ሃላፊነቱን ዘንግቶ የፖለቲካ አጀንዳ መጫወቻ ሲሆን ደግሞ በጣም መጥፎ ነው። አሉ እንደዛ ምልክቶች! ይሄ መስተካከል አለበት። 

የዩኒቨርስቲ መምህራን በሃሳብ እንዲያግዙን እንፈልጋለን። አሁን ካለንበት ችግር ከዋጋ ግሽበቱ ፣ ከፕሮጀክቱም ፣ ከድህነቱም እንድንወጣ ፣ የምንጠብቀው እነሱን ነው። ይቺ አገር ከሌላት አንጡራ ሃብት ላይ መንዝራ  መቀነቷን ፈታ አስተምራቸዋለች፣ ያለችበትን ችግር መፍታት የእኔም የእነሱም እዳ ነው። "

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa