“አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ” የትህነግ ባዶ ስልት
ሁሉም የትግራይ ህዝብ ህወሀት ነው ብላ በመመፃደቅ የምትታወቀው ትህነግ እስከነ አካቴው የመጥፊያ ጊዜዋን በማፋጠን ላይ ትገኛለችⵆከነሃሴ 18 2014 ዓ.ም ጀምሮ በትዕቢት ተወጥራ በአማራና አፋር ክልል አካባቢዎች ላይ ሶስተኛ ዙር ወረራ ፈፅማለች የአሁኑ ወረራዋ የመጥፊያዋ ጊዜ እጅግ በጣም የቀረበ መሆኑ እርግጥ የሆነበት ነው፡፡
ትናንትም ሆነ ዛሬ የትህነግ የውጊያ ስልት የታወቀ ነው፡፡ዘመኑ ያለፈበትን የውጊያ ስልት የሕዝብ ማዕበል በመጠቀም አንድን አካባቢ እንደ አንበጣ መውረርና ሳር ቅጠሉን ማውደም ነው፡፡ይህ ኋላቀር የውጊያ ስልት በባህሪው በማዕበል የመጣውን ህዝብ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ በቀላሉ የሚያስፈጅ በመሆኑ ጦርነትን ለማሸነፍ የሚያስችል አይደለም፡፡ ለ47 ዓመታት የትግራይን ህዝብ ለጦርነት እሳት እየማገደች የምትገኘው ትህነግ በህይወት ዘመኗ የተካነችበት አንድ ህዝብ የማሸበሪያ ዘዴ አላት፡፡አባሎቿን በለማኝነት፣ በቆራሌነት፣ በተፈናቃይነት….ስም እያደራጀች ወደ ከተሞችና የገጠር መንደሮች በመላክ ህዝብን ታሳስታለች ታሸብራለች፡፡ሞራልም፣ ህግም፣ትዝብትም፣ይሉኝታም ስለማይገዛት ያዋጣኛል የምትለውን የሀሰት ወሬ ታሰራጫለች፡፡በዚህም ተጠቃሚ ሆኗለች፡፡
ከአሁን በኅላ በለመደችው ስልት የመቀጠል ዕድል ግን የላትም አብቅቶላታል ምናልባት
ጭቂት ቀናት ብቻ ቀርተው ይሆናል የሶስተኛ ዙር ወረራዋን ከፈፀመች በጥቂት ቀናት ውስጥ ሰላም እንደምትፈልግ በአፈ ቀላጤዋ ጌታቸው ረዳ በኩል ትናንት ለፍፋለች ይህም ለጥቂት ጊዜ ያቀየኝ ይሆናል ብላ
የዘየደችው ሊሆን ይችላል
ትህነግ ተገለባባጭ ናት ቋሚ ባህሪ እንደሌላት ይታወቃል "ለማያውቅሽ ታጠኚ" ይላል የሀገሬ ሰው
ትህነግ እንኳን ለአማራና ለአፋር ክልል ሕዝብ ለራስዋ የትግራይ ክልል ሕዝብም ቅንጣት ታክል ማሰብ እንደማትችል ስፍር ቁጥር በሌለው መጥፎ ድርጊቶቿ አሳይታናለች
አሸባሪዋ ቡድን ለአማራና አፋር ሕዝብ አሳቢና ተቆርቋሪ መሆኗን በአፈ ቀላጤዋ ድንዙዝ ጌታቸው ረዳ አማካይነት ትናንት ባዝረከረከችው ለሃጭዋ ነው ይፋ ያደረገችው፤ትህነግ ለአማራና አፋር ሕዝብ ያላትን ፍቅር በገለማ አፍዋ ስትናገር ተሰማ ጉድ ነው
መሰሪዋ አሸባሪ ቡድን የአማራና አፋር ክልሎችን መሰረተ ልማቶች አውድማ፤እናቶችና ህፃናትን አስደፍራና ደፍራ እንስሳትን በጥይት ገድላ ሊጥና ሽሮ ሰርቃ ተነግሮ የማያልቅ ግፍ አድርሳ አሁን ወዳጅ መሆኗን ለመናገር ለምን ተገደደች?"ሁሉንም ስትገረፍ ታወራዋለህ"ሆኗል ነገሩ ገና ምን ተነካና!
ለማንኛውም የልመና መግለጫዋን ሰምተናል ነገር ግን ገለባ ነው ለትግራይ ክልል ሕዝብ የሚጠቅም፤ከአስከፊ ችግር የሚያወጣው ምንም ጠብ የሚል ነገር የለውም
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ